Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ መሀመድ አለሙ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰበር መዝገብ ቁጥር 266395

ጉዳዩ የቀረበው የኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች 1ኛ ተከሳሽ አሁን የክርክሩ አካል ያልሆነው የትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ 2ኛ ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበው 1ኛ ክስ የወ/ህግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)፣ 34(1) እና 693(1) በመተላለፍ በትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ ውስጥ የፋብሪካው ኃላፊ እና ባለንብረት ሆኖ በሚሰሩበት ጊዜ ለግል ተበዳይ አቶ ሸምሱ አወል የብር አምስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የሚመነዘር ቼክ ሰጥቶ የግል ተበዳይ ገንዘቡን ለማውጣት ወደ ባንክ ሲሄድ በቂ ገንዘብ የለውም በመባሉ ገንዘቡን ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ስለዚህ በቂ ስንቅ ሳይኖር ቼክ በመስጠት ወንጀል ተከሷል የሚል ነው፡፡ አመልካች የወንጀሉን ድርጊት አልፈፀምኩም ብሎ ክዶ በመከራከሩ ተጠሪ የሰውና የሰነድ ማስረጃ አቅርቦ እንደ ክስ አቀራረቡ አስረድቷል፡፡ አመልካች እንዲከላከል ታዞ መከላከያ ማስረጃ ያቀረበ ሲሆን የአመልካች መከላከያ ምስክሮች ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቼክ መጥፋቱን አስረድተዋል፡፡መልካም ንባብ…. 

Previous Article ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594
Next Article ጨመሬ ቶሎሳ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰ/መ/ቁጥር 267231፣267230
Print
7489

Documents to download

  • 266395(.pdf, 849.74 KB) - 976 download(s)

«July 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
293012345
6789101112
13141516171819
20212223242526
272829303112
3456789

የህገ መንግስት ትርጉም፤ የሰበር ስልጣንና ዉሳኔ እንዲሁም...

2969

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትና ጀስቲስ ፎር ኦል ፕሪዝን ፌሎዉሽፕ ኢትዮጵያ የጋራ ትብብር በፌደራል ጠቅላይ ፍድር ቤት የሰበር ስልጣንና ዉሳኔ፤ የህገ-መንግስት አተረጓጎም እንዲሁም ምቹ የህጻናት ፍርድ ቤቶች የአሰራር ረቂቅ መመሪያን የሚያዳብር ወርክሾፕ በርካታ የፌደራል ፍርድ ቤቶች ክቡራን ዳኞችና ሌሎች ከተለያየ የምርምርና የትምህርት ተቋማት የመጡ የህግ ምሁራን በተገኙበት ታህሳስ 19 ቀን 2016 ዓ/ም አዲስ አበባ በሚገኘዉ ኃይሌ ግራንድ ሆቴል ተካሄደ፡፡ 

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ፍኖተ ካርታ መልካም እመርታ...

2523

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ተወካዮች ታህሳስ 18 ቀን 2016 ዓ/ም በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቅጥር ጊቢ በመገኘት ባደረጉት የመስክ ምልከታ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፌደራል ፍርድ ቤቶችን ፍኖተ ካርታ ተከትሎ በማከናወን ላይ የሚገኙ ተግባራት የሚበረታቱና የሚደነቁ መሆናቸዉን ገልጸዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ጋር...

3309

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሚሰጣቸውን ውሳኔዎችን በመጽሐፍ መልክ አትሞ ለማሰራጨት ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ጋር ታህሳስ 9 ቀን 2016 ዓ.ም የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡

First4950515254565758Last