Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ መሀመድ አለሙ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰበር መዝገብ ቁጥር 266395

ጉዳዩ የቀረበው የኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች 1ኛ ተከሳሽ አሁን የክርክሩ አካል ያልሆነው የትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ 2ኛ ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበው 1ኛ ክስ የወ/ህግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)፣ 34(1) እና 693(1) በመተላለፍ በትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ ውስጥ የፋብሪካው ኃላፊ እና ባለንብረት ሆኖ በሚሰሩበት ጊዜ ለግል ተበዳይ አቶ ሸምሱ አወል የብር አምስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የሚመነዘር ቼክ ሰጥቶ የግል ተበዳይ ገንዘቡን ለማውጣት ወደ ባንክ ሲሄድ በቂ ገንዘብ የለውም በመባሉ ገንዘቡን ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ስለዚህ በቂ ስንቅ ሳይኖር ቼክ በመስጠት ወንጀል ተከሷል የሚል ነው፡፡ አመልካች የወንጀሉን ድርጊት አልፈፀምኩም ብሎ ክዶ በመከራከሩ ተጠሪ የሰውና የሰነድ ማስረጃ አቅርቦ እንደ ክስ አቀራረቡ አስረድቷል፡፡ አመልካች እንዲከላከል ታዞ መከላከያ ማስረጃ ያቀረበ ሲሆን የአመልካች መከላከያ ምስክሮች ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቼክ መጥፋቱን አስረድተዋል፡፡መልካም ንባብ…. 

Previous Article ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594
Next Article ጨመሬ ቶሎሳ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰ/መ/ቁጥር 267231፣267230
Print
6470

Documents to download

  • 266395(.pdf, 849.74 KB) - 889 download(s)

«June 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
25262728293031
1234567
891011121314
15161718192021
22232425262728
293012345

በቻይና ሲካሄድ የቆየው የብሪክስ አገራት ዳኞች ሴሚናር ተጠናቀቀ

2591

በሁለት ዙር ተከፍሎ በቻይና የዳኝነት ስርዓት ኮሌጅ አዘጋጅነት የተካሄደው የብሪክስ አገራት ዳኞች ሴሚናር ሕዳር 25 ቀን 2016 ዓ.ም ተጠናቋል፡፡ በሴሚናሩ ላይ የኢትዮጵያ፤ የግብፅ እና የብራዚል ልዑካን የተሳተፉ ሲሆን በተለይም በሁለተኛው እና በመጨረሻው ዙር የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ፉአድ ኪያርን ጨምሮ 11 የፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች እንዲሁም ከፍትህ ሚኒስቴር 9 ዓቃቢያነ ህጎች ተሳትፈዋል፡፡

 

ፍርድ ቤቱ ከወርልድ ባንክ ስታር ኢኒሺዬቲቭ ጋር...

2372

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከወርልድ ባንክ ስታር ኢኒሺዬቲቭ (World Bank Star Initiative) ጋር በመተባበር በሶስቱም ደረጃ ለሚገኙ የፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች ያዘጋጀው የ3 ቀን ሥልጠና ተጠናቀቀ፡፡

የፌደራል ፍ/ቤቶች የ2016 በጀት አመት እቅድና...

1836

በሪፖርቱ በእቅድ ዝግጅት ምዕራፍ ላይ የተከናወኑ ተግባራት፣ የዳኝነት ነጻነትና ተጠያቂነት መርሆዎችን ከማጠናከር፣ ቅልጥፍናና ጥራትን ከማሳደግ ፣የፍ/ቤቶችን ተደራሽነት ከማስፋፋት፣ አገራዊና አለምአቀፋዊ አጋርነትን እንዲሁም የመምራትና የመፈጸም ብቃት ከማሳደግ አኳያ የተከናወኑ ተግባራት የተዘረዘሩ ሲሆን በተጨማሪነትም የኢኮቴ አጠቃቀም እና የፋይናንስና ንብረት ውጤታማነትን ለማሳደግ የተከናወኑ ተግባራት በሰፊው ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

First5051525355575859Last