Selam Warga / Tuesday, June 17, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation አቶ መሀመድ አለሙ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰበር መዝገብ ቁጥር 266395 ጉዳዩ የቀረበው የኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች 1ኛ ተከሳሽ አሁን የክርክሩ አካል ያልሆነው የትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ 2ኛ ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበው 1ኛ ክስ የወ/ህግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)፣ 34(1) እና 693(1) በመተላለፍ በትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ ውስጥ የፋብሪካው ኃላፊ እና ባለንብረት ሆኖ በሚሰሩበት ጊዜ ለግል ተበዳይ አቶ ሸምሱ አወል የብር አምስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የሚመነዘር ቼክ ሰጥቶ የግል ተበዳይ ገንዘቡን ለማውጣት ወደ ባንክ ሲሄድ በቂ ገንዘብ የለውም በመባሉ ገንዘቡን ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ስለዚህ በቂ ስንቅ ሳይኖር ቼክ በመስጠት ወንጀል ተከሷል የሚል ነው፡፡ አመልካች የወንጀሉን ድርጊት አልፈፀምኩም ብሎ ክዶ በመከራከሩ ተጠሪ የሰውና የሰነድ ማስረጃ አቅርቦ እንደ ክስ አቀራረቡ አስረድቷል፡፡ አመልካች እንዲከላከል ታዞ መከላከያ ማስረጃ ያቀረበ ሲሆን የአመልካች መከላከያ ምስክሮች ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቼክ መጥፋቱን አስረድተዋል፡፡መልካም ንባብ…. Previous Article ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594 Next Article ጨመሬ ቶሎሳ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰ/መ/ቁጥር 267231፣267230 Print 6470 Documents to download 266395(.pdf, 849.74 KB) - 889 download(s)
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከወርልድ ባንክ ስታር... የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከወርልድ ባንክ ስታር... Monday, November 20, 2023 1940 የስልጠናው አላማ ዳኞችን በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ በሙስና ወንጀሎች ሀብት ማስመለስ እና ሌሎች ተያያዥ የወንጀል ጉዳዬች እና የፍርድ ሂደቶች ላይ በአለም አቀፍ ተሞክሮዎች ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ እና በጉዳዩ ዙሪያ የኢትዬጵያ ህግ ምን ይላል የሚለውን በተመለከተ ውይይት ለማድረግ ሲሆን ስልጠናው ከህዳር 7 እስከ ህዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም የሚሰጥ ይሆናል፡፡ Read more
በፍርድ ቤት በማስረጃነት ሲቀርቡ ቴምብር ቀረጥ... በፍርድ ቤት በማስረጃነት ሲቀርቡ ቴምብር ቀረጥ... Tuesday, November 14, 2023 2871 የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ገቢዎች ቢሮ በፍርድ ቤት በማስረጃነት በሚቀርቡ ሠነዶች ላይ የቴምብር ቀረጥ ለማስለጠፍ እና ቀረጥ በተመን ለማስከፈል ባለጉዳዮች ክርክራቸውን በሚያቀርቡበት ምድብ ችሎቶች አቅራቢያ አገልግሎቱን ለመስጠት ጥቅምት 15 ቀን 2016 ዓ.ም የመግባቢያ ስምምነት የተፈራረሙ መሆኑ ይታወቃል፡፡ Read more
የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የዳኝነት ስርዓት የውጭ አማካሪ... የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የዳኝነት ስርዓት የውጭ አማካሪ... Friday, November 3, 2023 2956 የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 53 መሰረት ከቀድሞ ዳኞች፣ ከፍተኛ ልምድ እና ብቃት ካላቸው የህግ ባለሙያዎች እና ከዩኒቨርሲቲ ምሁራን ከተውጣጡ አካላት የአማካሪ ምክር ቤት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ አበባ እምቢአለ በተገኙበት ጥቅምት 19 ቀን 2016 ዓ.ም አቋቋመ፡፡ Read more
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የአዲስ አበባ ከተማ... የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የአዲስ አበባ ከተማ... Friday, November 3, 2023 2369 የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ገቢዎች ቢሮ በፍርድ ቤቶች በማስረጃነት በሚቀርቡ ሠነዶች ላይ የቴምብር ቀረጥ ለማስለጠፍ እና ቀረጥ በተመን ለማስከፈል ባለጉዳዮች ክርክራቸውን በሚያቀርቡበት ምድብ ችሎቶች አቅራቢያ አገልግሎቱን ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡ Read more
10Mar2026 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Tuesday, March 10, 2026 Read more