Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ መሀመድ አለሙ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰበር መዝገብ ቁጥር 266395

ጉዳዩ የቀረበው የኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች 1ኛ ተከሳሽ አሁን የክርክሩ አካል ያልሆነው የትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ 2ኛ ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበው 1ኛ ክስ የወ/ህግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)፣ 34(1) እና 693(1) በመተላለፍ በትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ ውስጥ የፋብሪካው ኃላፊ እና ባለንብረት ሆኖ በሚሰሩበት ጊዜ ለግል ተበዳይ አቶ ሸምሱ አወል የብር አምስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የሚመነዘር ቼክ ሰጥቶ የግል ተበዳይ ገንዘቡን ለማውጣት ወደ ባንክ ሲሄድ በቂ ገንዘብ የለውም በመባሉ ገንዘቡን ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ስለዚህ በቂ ስንቅ ሳይኖር ቼክ በመስጠት ወንጀል ተከሷል የሚል ነው፡፡ አመልካች የወንጀሉን ድርጊት አልፈፀምኩም ብሎ ክዶ በመከራከሩ ተጠሪ የሰውና የሰነድ ማስረጃ አቅርቦ እንደ ክስ አቀራረቡ አስረድቷል፡፡ አመልካች እንዲከላከል ታዞ መከላከያ ማስረጃ ያቀረበ ሲሆን የአመልካች መከላከያ ምስክሮች ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቼክ መጥፋቱን አስረድተዋል፡፡መልካም ንባብ…. 

Previous Article ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594
Next Article ጨመሬ ቶሎሳ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰ/መ/ቁጥር 267231፣267230
Print
6470

Documents to download

  • 266395(.pdf, 849.74 KB) - 889 download(s)

«June 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
25262728293031
1234567
891011121314
15161718192021
22232425262728
293012345

የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2016 በጀት ዓመት መደበኛ...

3904

የፌደራል ፍርድ ቤቶች በነሐሴ እና መስከረም ወራት በከፊል ዝግ ሆነው መቆየታቸውን ተከትሎ የ2016 በጀት ዓመት መደበኛ የዳኝነት አገልግሎት ለማስጀመር ጥቅምት 1 ቀን 2016 ዓ.ም በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተዘጋጀ ሥነ ሥርዓት ተካሔደ፡፡ መደበኛ የዳኝነት አገልግሎት ለማስጀመር የተካሔደውን ሥነ ሥርዓት ተከትሎ የፌደራል ፍርድ ቤቶች መደበኛ የዳኝነት አገልግሎታቸውን በይፋ ጀምረዋል፡፡

በስነ-ስርዓቱ ላይ የሶስቱ የፌደራል ፍርድ ቤቶች ፕሬዝደንቶችና ምክትል ፕሬዝደንቶች እንዲሁም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞችን ጨምሮ የስራ ክፍል ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ታዳሚ ሆነዋል፡፡

በሽግግር ፍትሕ ሂደት የዳኞች ሚና በሚል ርዕስ ሀገራዊ...

4230

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከኢጋድ ጋር በመሆን ለሶስት ቀናት በሽግግር ፍትሕ የዳኞች ሚና በሚል ርዕስ በቢሾፍቱ ከተማ ሲካሄድ የቆየው ወርክሾፕ ተጠናቀቀ፡፡

ወርክሾፑን በንግግር የከፈቱት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ክብርት ወ/ሮ አበባ እምቢአለ እንደገለጹት ዳኞች አድካሚ የዳኝነት ስራ አጠናቀው በሚገኙበት በአሁኑ የእረፍት ጊዜ የዳኞችን አቅም ለማገንባት የሚያስችል፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ ትኩረት በተሰጠው የሽግግር ፍትሕ ጉዳይ ላይ ወርክሾፕ መዘጋጀቱ በቀጣይ የሚቀርቡ የሽግግር ፍትሕ ጉዳዮች ላይ በቂ ግንዛቤ እና እወቀት በመያዝ ለመስራት የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ጽ/ቤት...

3065

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ጽ/ቤት የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አዲስ ለሚያሰራው የህጻናት ማቆያ የሚሆን ግምታቸው ብር 35,000 (ሰላሳ አምስት ሺህ) ብር የሚያወጡ የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ፡፡

ዜና መግለጫ

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከነሐሴ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 30/2016 ዓ.ም ድረስ በከፊል ዝግ ይሆናሉ፡፡

3573

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በሕገ መንግስቱ እና በሕግ በተሰጣቸው ስልጣንና ኃላፊነት መሰረት የሚቀርቡ ጉዳዮችን በማስተናገድ የሕግ የበላይነት እንዲሰፍን፣ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች እንዲጠበቁ ሰላም እና ስርዓት እንዲከበር የማድረግ ተግባራትን እየተወጡ ይገኛሉ፡፡

በዚህ መሰረት በ2015 በጀት ዓመት በነበረዉ የመዛግብት አፈጻጻም አንጻር ለፌዴራል ፍርድ ቤቶች በአጠቃላይ 213,116 መዛግብት ቀርበዋል። ከእነዚህም ዉስጥ ለ184,467 (86.56%) መዛግብት እልባት መስጠት የተቻለ ሲሆን 28,675 (13.44%) መዛግብት ደግሞ ወደ 2016 በጀት ዓመት ተሻግረዋል፡፡ የበጀት ዓመቱ አፈጻጸም ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ2014 በጀት ዓመት ለፌ/ፍ/ቤቶች የቀረቡት 209,317 መዛግብት ሲሆኑ ዕልባት ያገኙት ደግሞ 176,767 ነበሩ፡፡ በዚህም መሠረት በ2015 በጀት ዓመት የቀረቡት መዛግብት በ2014 በጀት ዓመት ከቀረቡት በ3,799 (1.8%) ከፍ ያሉ ሲሆን በተመሳሳይ ዕልባት ያገኙትም በ7,670 (4.3%) መዛግብት ከፍ ያሉ ናቸው፡፡

የፍርድ ቤቶቹ አፈጻጸም በተናጠል ሲታይ ለፌ/ጠ/ፍ/ቤት በ2015 በጀት ዓመት 26,185 መዛግብት ቀርበው ለ19,201 ዕልባት የተሰጠ ሲሆን 6,984 መዛግብት ወደ 2016 በጀት ዓመት ተሻግረዋል፡፡ በተመሳሳይ በ2015 በጀት ዓመት ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረቡት የመዛግብት ብዛት 33,721 ሲሆን 26,301 መዛግብት ዕልባት አግኝተዋል፡፡ ወደ 2016 የተሻገሩት መዛግብት ብዛትም 7,420 ሆኗል፡፡ እንዲሁም ለፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በ2015 በጀት ዓመት የቀረቡት 153,210 መዛግብት ሲሆኑ 138,965 ዕልባት በማግኘታቸው 14,245 ወደ 2016 በጀት ዓመት ተላልፈዋል፡፡

First5253545557596061Last