Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ መሀመድ አለሙ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰበር መዝገብ ቁጥር 266395

ጉዳዩ የቀረበው የኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች 1ኛ ተከሳሽ አሁን የክርክሩ አካል ያልሆነው የትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ 2ኛ ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበው 1ኛ ክስ የወ/ህግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)፣ 34(1) እና 693(1) በመተላለፍ በትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ ውስጥ የፋብሪካው ኃላፊ እና ባለንብረት ሆኖ በሚሰሩበት ጊዜ ለግል ተበዳይ አቶ ሸምሱ አወል የብር አምስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የሚመነዘር ቼክ ሰጥቶ የግል ተበዳይ ገንዘቡን ለማውጣት ወደ ባንክ ሲሄድ በቂ ገንዘብ የለውም በመባሉ ገንዘቡን ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ስለዚህ በቂ ስንቅ ሳይኖር ቼክ በመስጠት ወንጀል ተከሷል የሚል ነው፡፡ አመልካች የወንጀሉን ድርጊት አልፈፀምኩም ብሎ ክዶ በመከራከሩ ተጠሪ የሰውና የሰነድ ማስረጃ አቅርቦ እንደ ክስ አቀራረቡ አስረድቷል፡፡ አመልካች እንዲከላከል ታዞ መከላከያ ማስረጃ ያቀረበ ሲሆን የአመልካች መከላከያ ምስክሮች ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቼክ መጥፋቱን አስረድተዋል፡፡መልካም ንባብ…. 

Previous Article ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594
Next Article ጨመሬ ቶሎሳ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰ/መ/ቁጥር 267231፣267230
Print
6489

Documents to download

  • 266395(.pdf, 849.74 KB) - 895 download(s)

«June 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
25262728293031
1234567
891011121314
15161718192021
22232425262728
293012345

የፌደራል ፍርድ ቤቶች አረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ...

3404

(ሐምሌ 15/2015 ዓ.ም፣) የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ክቡራን ፕሬዚዳንቶች ፣ ክቡራን ዳኞች እና የሥራ ኃላፊዎች የተሳተፉበት የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሐግብር በአዲስ አበባ ጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል ሐምሌ 15 ቀን 2015 ዓ.ም ተከናወነ፡፡

በቤተሰብ አስማሚነት ላይ የተዘጋጀ የሥልጠና እና የውይይት...

2876

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሕጻናት ፍትሕ ፕሮጀክት ጽ/ቤት በፍርድ ቤት መር አስማሚነት በተለይም በቤተሰብ አስማሚነት (Family mediation) ላይ ለፌደራል ፍርድ ቤት ረዳት ዳኞች እና ለሶሻል ወርክ ባለሙያዎች ያዘጋጀው የሥልጠና እና የውይይት መድረክ በኢንተር ኮንቲኔታል ሌግዢሪ ሆቴል ተካሄዷል፡፡

ለፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች እና የሥራ ኃላፊዎች በአመራር...

3112

ከፌደራል ፍርድ ቤቶች ለተውጣጡ ዳኞች እና የሥራ ኃላፊዎች በአመራር ክህሎት (Leadership) ላይ የተዘጋጀ ሥልጠና በአሜሪካ አገር ከሚገኘውና ችክፍሌ (Chick-fil-A) ከተሰኘው ድርጅት በመጡ ስድስት ባለሙያዎች ሰኔ 19 ቀን 2015 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል ተሰጠ፡፡

ሥልጠናው የመሪነት ጽንሰ-ሐሳብ እና የጥሩ መሪ ስብዕናዎች የተዳሰሱበት ሲሆን በኃላፊነት ላይ የተቀመጡና በሥራቸው ውጤታማ የሆኑ ግለሰቦች ሁሉ መሪ (Leader) ሊሆኑ እንደማይችሉም ተገልጿል፡፡

በፌደራል ፍርድ ቤቶች የለውጥ ፍኖተ-ካርታ ላይ ውይይት ተካሔደ

3179

በፌደራል ፍርድ ቤቶች የለውጥ ፍኖተ ካርታ ላይ በጥብቅና ሙያ ተሰማርተው አገልግሎት በመስጠት ላይ ለሚገኙ ጠበቆች በፌደራል ፍርድ ቤቶች ከፍተኛ አመራሮች ሰኔ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ገለጻ ተደርጓል፡፡

First5354555658606162Last