Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ ተስፋዬ ደገፋ እና ዶ/ር ትዕዛዙ ተፈራ ፤የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ጽ/ቤት፤የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት የሰ/መ/ቁ 259947

ለዚህ የሰበር ክርክር ምክንያት የሆነዉ ክርክር የተጀመረዉ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን በከፍተኛዉ ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ፣ ተጠሪዎች ደግሞ ተከሳሾች በመሆን መከራከራቸዉን የሥር ፍ/ቤቶች ዉሳኔ ያመለክታል፡፡ ክርክሩ በማህበር በመደራጀት ከተገኘዉ ይዞታ ጋር የተያያዘ ሲሆን አመልካች በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተጠሪዎች ላይ ባቀረቡት  ክስ በ03/08/1990 ዓ/ም ተመዝግቦ በፀደቀዉ የመተዳደሪያ ደንብ መሠረት የተደራጀ ታቦር የመኖሪያ ቤቶች ኅብረት ሥራ ማኅበር አባል በመሆን ተደራጅተዉ ማኅበሩ በሕጋዊ መንገድ ከመንግሥት ካገኘዉ ጠቅላላ ይዞታ ላይ መጠኑ 203.67 ካሬ ሜትር የሆነዉን የክርክሩን ይዞታ   በድርሻ እንደሰጣቸዉና የዚሁ ይዞታ ሕጋዊ ባለመብት ስለመሆናቸዉም በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 281839 በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ኅብረት ሥራ ጽ/ቤትና በኮልፌ  ቀራኒዮ ክለ ከተማ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት ላይ ክስ አቅርበዉ መብታቸዉ ተረጋግጦ ዉሳኔ እንዲያገኝ የሚል ነው፡መልካም ንባብ…

Previous Article ወ/ሮ ሙርሽዳ ሁሴን እና ወ/ሮ አልፊያ ሁሴን (13) ሰዎች የሰ/መ/ቁ 257243
Next Article ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594
Print
6686

Documents to download

  • 259947(.pdf, 828.26 KB) - 781 download(s)

«August 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
272829303112
3456789
10111213141516
17181920212223
24252627282930
31123456

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የዳኝነት ስርዓት የውጭ አማካሪ...

3526

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 53 መሰረት ከቀድሞ ዳኞች፣ ከፍተኛ ልምድ እና ብቃት ካላቸው የህግ ባለሙያዎች እና ከዩኒቨርሲቲ ምሁራን ከተውጣጡ አካላት የአማካሪ ምክር ቤት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ አበባ እምቢአለ በተገኙበት ጥቅምት 19 ቀን 2016 ዓ.ም አቋቋመ፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የአዲስ አበባ ከተማ...

2919

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ገቢዎች ቢሮ በፍርድ ቤቶች በማስረጃነት በሚቀርቡ ሠነዶች ላይ የቴምብር ቀረጥ ለማስለጠፍ እና ቀረጥ በተመን ለማስከፈል ባለጉዳዮች ክርክራቸውን በሚያቀርቡበት ምድብ ችሎቶች አቅራቢያ አገልግሎቱን ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2016 በጀት ዓመት መደበኛ...

4592

የፌደራል ፍርድ ቤቶች በነሐሴ እና መስከረም ወራት በከፊል ዝግ ሆነው መቆየታቸውን ተከትሎ የ2016 በጀት ዓመት መደበኛ የዳኝነት አገልግሎት ለማስጀመር ጥቅምት 1 ቀን 2016 ዓ.ም በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተዘጋጀ ሥነ ሥርዓት ተካሔደ፡፡ መደበኛ የዳኝነት አገልግሎት ለማስጀመር የተካሔደውን ሥነ ሥርዓት ተከትሎ የፌደራል ፍርድ ቤቶች መደበኛ የዳኝነት አገልግሎታቸውን በይፋ ጀምረዋል፡፡

በስነ-ስርዓቱ ላይ የሶስቱ የፌደራል ፍርድ ቤቶች ፕሬዝደንቶችና ምክትል ፕሬዝደንቶች እንዲሁም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞችን ጨምሮ የስራ ክፍል ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ታዳሚ ሆነዋል፡፡

በሽግግር ፍትሕ ሂደት የዳኞች ሚና በሚል ርዕስ ሀገራዊ...

5014

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከኢጋድ ጋር በመሆን ለሶስት ቀናት በሽግግር ፍትሕ የዳኞች ሚና በሚል ርዕስ በቢሾፍቱ ከተማ ሲካሄድ የቆየው ወርክሾፕ ተጠናቀቀ፡፡

ወርክሾፑን በንግግር የከፈቱት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ክብርት ወ/ሮ አበባ እምቢአለ እንደገለጹት ዳኞች አድካሚ የዳኝነት ስራ አጠናቀው በሚገኙበት በአሁኑ የእረፍት ጊዜ የዳኞችን አቅም ለማገንባት የሚያስችል፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ ትኩረት በተሰጠው የሽግግር ፍትሕ ጉዳይ ላይ ወርክሾፕ መዘጋጀቱ በቀጣይ የሚቀርቡ የሽግግር ፍትሕ ጉዳዮች ላይ በቂ ግንዛቤ እና እወቀት በመያዝ ለመስራት የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

First5455565759616263Last