Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ቀበሌ 11/12/08 ሸማቾች ኃ/የተ/ሕ/ሥ/ማ እና አቶ እንኮሳ አመንቴ ሱፋ(9ሰዎች)የሰ.መ.ቁ 249104

የክሱ ይዘት በአጭሩ፡- በየካ አውራጃ ከፍተኛ 16 ቀበሌ 08 የቀድሞው የቀበሌ አመራሮች የተጠሪዎችን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ በማሰብ ከህብረት ሥራ ማህበር ብር 29.000 (ሃያ ዘጠኝ ሺህ ብር) በብድር መልክ ወጪ ተደርጎ ቤት እንድንገነባ ተፈቅዶልን ቤቶቹን በመገንባት የብድር ገንዘብም  ተመልሷል፤ ተጠሪዎችን ጨምሮ ሌሎች ነዋሪዎች በራሳችን ገንዘብ ቤቶቹን አፍርሰን እንደሰራን በወቅቱ የነበሩ የአመልካች አመራሮች አረጋግጠው በሰነድ ማስረጃ ሰጥተውናል፤ ተጠሪዎች ከ1982/1983 ጀምሮ በሰነድ አልባ በመኖሪያ ቤቶቹን ገንብተን እየኖርን እያለን ከ20 ዓመታት በኋላ አመልካች ለተጠሪዎች ያሰበ በማስመሰል ከፊሎቹን የተጠሪዎች ቤቶች ለልማት ሊፈርሱ ስለሚችሉ የጋራ መኖሪያ ቤት መንግስት እንዲሰጣችሁ እና ቀበሌው እንዲያውቃችሁ በማለት ከሱ ጋር የቤት ኪራይ ውል እንድንዋዋል ሲጠይቀን ተጠሪዎችም የአመልካች ህብረት ሥራ ማህበር አባላት በመሆናቸን እና መንግስታዊ ተቋም ነው ብለን በማመን ከ2ኛ ተጠሪ በስተቀር ከአመልካች ጋር የቤት ኪራይ ውል ልንፈርም ችለናል፤ተጠሪዎች የይዞታ ማረጋገጫ ለመቀበል በሂደት ላይ እያለን አመልካች ከህግም ሆነ ከውል የመነጨ መብት ሳይኖረው እንዳይፈጸም አድርጓል፤ አመልካች ተጠሪዎችን በማታለል ባስፈረመን የኪራይ ውል መነሻነት ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኪራዩን ከፍለው ቤቱን ያስረክቡኝ በማለት ክስ አቅርቦ ተጠሪዎች ቤቱን እንድናስረክብ ተወስኗል፤ ሆኖም ከመነሻው ቦታው በጎርፍ ምክንያት ለህይወታችን እስጊ በመሆኑ ልዋጭ ቦታ እንዲሰጠን የሚመለከተውን አካል ጠይቀን ሲሰጠን በቦታው ላይ ቀበሌው ቤት መስራት ካልቻለ ነዋሪዎች በራሳችን ወጪ እንድንሰራ በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት በራሳችን ወጪ ቤት ገንብተን በስማችን ውሃ፣ መብራት እና መሰል መሰረታዊ አገልግሎቶችን አስገብተን የምንኖርበት ቤት በመሆኑ ቤቶቹ የተጠሪዎች ናቸው ተብሎ ይወሰንልን በማለት ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡መልካም ንባብ….

Previous Article አቶ ታዬ ከተማ ደጋጋ እናእነ አቶ ሙሉጌታ ታደሰ (3ሰዎች) የሰ/መ/ቁጥር---244417
Next Article እስጢፋኖስ /ዩቡና/ ዲራጎ እና የሲዳማ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሠ/መ/ቁጥር 251519
Print
4771

Documents to download

  • 249104(.pdf, 865.58 KB) - 559 download(s)

«July 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
293012345
6789101112
13141516171819
20212223242526
272829303112
3456789

የህጸናትን መብት እና የላቀ ጥቅም ከማስጠበቅ አንጻር...

1512

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከUNFPA እና Save The Children International ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ የህጻናትን መብት እና የላቀ ጥቅም ከማስጠበቅ አንጻር በፍርድ ቤት መር አስማሚነት እና የማስማማት ክህሎት ላይ ለዳኞች ፤ረዳት ዳኞች እና የሶሻል ወርክ ባለሙያዎች የካቲት 27 እና 28 ቀን 2018 ዓ.ም 2ተኛ ዙር ስልጠና ሰጥቷል፡፡

123468910Last