Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ ሰለሞን አርአያ እናእነ ህፃን ዳንኤል ቴውድሮስ ሞግዚት ወ/ሮ የሺ መንግስቱ(5ሰዎች)የሰ/መ/ቁጥር፡- 255592

ጉዳዩ የውርስ ማጣራትን የሚመለከት ሆኖ አቤቱታው በቀረበበት የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት አመልካች 5ኛ ጣልቃ ገብ ፣ 2ኛ ተጠሪ የስር ተጠሪ፤1ኛ ተጠሪ የስር አመልካች፤  ከ3ኛ እስከ 5ኛ ያሉ ተጠሪዎች ደግሞ 3ኛ፤4ኛ እና 6ኛ ጣ/ገቦች ነበሩ፡፡ የክርክሩ አመጣጥ በአጭሩ፡- የአሁን 1ኛ ተጠሪ  ባቀረቡት አቤቱታ የሟች ባለቤታቸው ቴውድሮስ አርአያ ወላጆች የልጃቸው አያት የሆኑት ጀነራል አርአያ ዘርዓይ ጥር 25 ቀን 2003 ዓም እናቱ ወ/ሮ ሰነዳይ ሀይሌ ጥር 04 ቀን 2004 ዓም ከዚህ አለም በሞት የተለዩ መሆኑን፤ባለቤታቸው ከወንድሞቹና እህቶቹ ጋር በመሆን በ29/08/2005 ዓም ወራሽነታቸውን ያረጋገጡ ቢሆንም ውርሱ ሳይጣራ መኖሪያ ቤቱን ሳይከፋፈሉ በጋራ ይዘው ሲጠቀሙበት ቆይተው ከ2006 ዓም ጀምሮ ቤቱን አከራይተው የኪራዩን ገንዘብ እኩል እየተካፈሉ መሆኑን ገልጠው ድርሻቸውን ለይተው ለማወቅና ለማረጋገጥ እንዲችሉ የውርስ ሀብት እንዲጣራ ጠይቀዋል፡፡ መልካም ንባብ…..

Previous Article ወ/ሮ በላይነሽ ጫላእና አቶ ሸዋንግዛው ሽብሩ/ቁጥር የሰ/መ/ቁ 254862
Next Article አቶ ዮሀንስ ካሳዬ እና የፍትህ ሚኒስቴር ዓቃቤ ሕግ የሠ/መ/ቁጥር 273594
Print
2618

Documents to download

  • 255592(.pdf, 834.83 KB) - 395 download(s)

«January 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
2930311234
567891011
12131415161718
19202122232425
2627282930311
2345678

የአፍሪካ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤቶችና ጠቅላይ ፍርድ ቤት...

281

4ኛውን የአፍሪካ ህገመንግሥታዊ ፍርድ ቤቶች እና መሰል ተቋማት ዓለም አቀፍ ሲምፖዝየም ‘ህገ መንግሥታዊነት እና ሀገረ መንግሥት ግንባታ’ በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ መካሄዱን ተከትሎ የመርሃግብሩ ተሳታፊ እንግዶች በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 20/03/2018 ዓ.ም በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል።

ለፌደራል ፍርድ ቤቶች የቤተሰብ ችሎት ዳኞች የልምድ...

403

የኢንግላንድ እና ዌልስ ጠበቆች ማህበር ፕሬዚዳንት የሆኑት ክብርት ባርባራ ሚልስ በቀን 19/03/2018 ዓ.ም በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ለፌደራል ፍርደ ቤቶች የቤተሰብ ችሎት ዳኞች ልምዳቸውን አካፈሉ፡፡

የላይቤሪያ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንትና ልዑክ...

332

የላይቤሪያ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ጄሚ ኩዊኪ (Honorable Jamie Quiqui Gbeisay) እና ልዑክ ቡድናቸው በቀን 17/03/2018 ዓ.ም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት እና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉብኝት አድርገዋል፡፡

በዲጂታል የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ በዋነኝነትም ...

383

በስልጠናው የማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ ድሪባ ፈዬራ ክቡራን ዳኞች ላደረጉት ንቁ ተሳትፎና በመድረኩ ለተነሱት ገንቢ ሀሳብ አስተያየቶች አመስግነው ቴክኖሎጂው በቅርቡ ወደ ትግበራ ስለሚገባ ለትግበራው ውጤታማነት ስልጠናው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

123468910Last