Selam Warga / Wednesday, June 4, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation አቶ ዮሀንስ ካሳዬ እና የፍትህ ሚኒስቴር ዓቃቤ ሕግ የሠ/መ/ቁጥር 273594 ጉዳዩ የዋስትና መብት አተገባበር የሚመለከት ነው፡፡ክርክሩ የተጀመረው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን ተጠሪ በአመልካች ላይ በመሰረተዉ ክስ አመልካች በኢፌዲሪ ወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1/ሀ) እና 590(1/ሀ እና 2/ሐ) ስር የተደነገገዉን በመተላለፍ በዋና ወንጀል አድራጊነት በሚፈፀም የሰው ማገት(መጥለፍ) ወንጀል በመፈጸሙ ተከሷል የሚል ነው፡፡ ይህንን ተከትሎ አመልካች የዋስትና መብቱ እንዲከበርለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡ፍርድ ቤቱም የዋስትና መብት ጥያቄውን በተመለከተ በሰጠው ትዕዛዝ አመልካች የተከሰሰበት ክስ በመርህ ደረጃ ዋስትና የማያስከለክል ቢሆንም እንጂ በክሱ ላይ የተጠቀሰውን ድርጊት አፈፃፀም በተመለከተ አመልካች የመከላከያ ሰራዊት የደንብ ልብስ ለብሰው እና የጦር መሳሪያ ይዘው ፈፀመ ተብሎ በክስ ዝርዝር ላይ ባይገለፅም ድርጊቱን ፈፅሞ ከሆነ ተሳትፎዉ ወደ ፊት ማስረጃ በመስማት ጊዜ የሚታይ ሆኖ በአጠቃላይ ከክሱ ዝርዝር ፍርድ ቤቱ የወንጀሉ አፈፃፀሙ ከባድ ሆኖ ስለአገኘዉ አመልካች ምን አልባት ወደፊት የወንጀል ድርጊቱን መፈፀሙ ተረጋግጦ ጥፋተኛ የሚባል ከሆነ ሊጣልበት የሚችለው ቅጣት ከባድ ሊባል የሚችል በመሆኑ ይህን ፈርቶ ቀጠሮ አክብሮ ይመጣል የሚል እምነት የለንም በማለት የአመልካችን የዋስትና መብት ጥያቄ ዉድቅ አድርጓል፡፡መልካም ንባብ….. Previous Article አቶ ሰለሞን አርአያ እናእነ ህፃን ዳንኤል ቴውድሮስ ሞግዚት ወ/ሮ የሺ መንግስቱ(5ሰዎች)የሰ/መ/ቁጥር፡- 255592 Next Article አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ እና የማነ ግርማይ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ የሰ.መ.ቁ 246233 Print 4943 Documents to download 273594(.pdf, 1.05 MB) - 790 download(s)
የህጸናትን መብት እና የላቀ ጥቅም ከማስጠበቅ አንጻር... የህጸናትን መብት እና የላቀ ጥቅም ከማስጠበቅ አንጻር... Monday, March 9, 2026 863 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከUNFPA እና Save The Children International ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ የህጻናትን መብት እና የላቀ ጥቅም ከማስጠበቅ አንጻር በፍርድ ቤት መር አስማሚነት እና የማስማማት ክህሎት ላይ ለዳኞች ፤ረዳት ዳኞች እና የሶሻል ወርክ ባለሙያዎች የካቲት 27 እና 28 ቀን 2018 ዓ.ም 2ተኛ ዙር ስልጠና ሰጥቷል፡፡ Read more
በኢትዮጵያ የዴንማርክ አምባሳደር ክቡር ሱን ክሮግስትረፕ... በኢትዮጵያ የዴንማርክ አምባሳደር ክቡር ሱን ክሮግስትረፕ... Thursday, March 5, 2026 580 በኢትዮጵያ የዴንማርክ አምባሳደር ክቡር ሱን ክሮግስትረፕ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት በቀን 26/06/2018 ዓ.ም ጉብኝት አድርገዋል። Read more
የዳኝነትና የዴሞክራሲ ተቋማት እምርታ፤ ለሀገረ መንግስት... የዳኝነትና የዴሞክራሲ ተቋማት እምርታ፤ ለሀገረ መንግስት... Wednesday, March 4, 2026 686 የካቲት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ''የዳኝነትና የዴሞክራሲ ተቋማት እምርታ ለተሳካ ሀገረ መንግሥት ግንባታ" በሚል መሪ ቃል በዳኝነትና የዴሞክራሲ ተቋማት የለውጥ ስራዎች ላይ በማተኮር ሲካሄድ የቆየው የምክክር መድረክ ተጠናቋል። Read more
ከምርጫ ጉዳዮች ጋር በተያያዙ ቅሬታዎች እና አፈታት ላይ... ከምርጫ ጉዳዮች ጋር በተያያዙ ቅሬታዎች እና አፈታት ላይ... Friday, February 27, 2026 690 ከምርጫ ጉዳዮች ጋር በተያያዙ ቅሬታዎች እና አፈታት ላይ ለፌዴራል እና ለክልል ዳኞች ከቀን 09/06/2018 ዓ.ም ጀምሮ በ3 ዙር ለ9 ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና በቀን18/5/2018 ዓ.ም ተጠናቀቀ፡፡ Read more
10Mar2026 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Tuesday, March 10, 2026 Read more