Selam Warga / Tuesday, June 17, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation የፌደራል ዐቃቤ ህግ እና አቶ አበበ ወንድሙ ኤጋ የሰ/መ/ቁጥር 251759 አመልካች በስር ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ ባቀረበው ክስ ተጠሪ የወ/ህ/ቁ.539(1)(ሀ) ን ተላልፈው ሰው ለመግደል አስቀድሞ በነበረው ሀሳብ ጨካኝነቱንና ነውረኝነቱን በሚያሳይ ሁኔታ ወንድሙን ሟች ጀንበሩ ወንድሙን ከአሁን በፊት ሰድቦኛል እንዲሁም በሚያሽከረክረው መኪና ሊገጨኝ ሞክሯል በማለት በቂም በቀል በመነሳት ሽጉጥ ተኩሶ ማጅራቱን ሲመታው ሲወድቅ በተደጋጋሚ ሶስት ጊዜ ተኩሶ ግንባሩን በቀኝ በኩል አንገቱንና በግራ በኩል አንገቱን በመምታት የጥይት እርሳስ ጉዳት በራስ ቅሉ የኋለኛው ክፍል፤የክብ ቅርፅ ያለው ጥይት እርሳስ የገባበት ቁስል በራስ ቅሉ የኋለኛው ክፍል፤ሳተላይት ቅርጽ ያለው የጥይት እርሳስ የወጣበት ቁስል፤በግራ ግንባሩ የፊተኛው ክፍል ላይ የአጥንት መሰበር ጉዳት፤በራስ ቅሉ ፊተኛው የታችኛው ክፍል ላይ እንዲደርስበት፤የመበሳት ጉዳት በአንገቱ ላይ እንዲደርስበት ፤በአንጎሉ የላይኛው ሽፋን ክፍል የተሰራጨ የደም መፍሰስ እንዲሁም የአየር ባንቧው የመበለዝ ጉዳት እና በዙሪያው ከፍተኛ ደረጃ ያለው የውስጥ ደም መፍሰስ ጉዳት እንዲደርሰበት እና ህይወቱ እንዲያልፍ አድርጓ በዚህም ከባድ የሆነ የሰው ግድያ ወንጀል ፈፅሟል በማለት ከሷል፡፡መልካም ንባብ…. Previous Article ህብረት ኢንሹራንስ አ.ማ እና ኤም.ኢ.ኤስ.ፒ. አፍሪካ ኃ.የተ.የግ. ማህበር ፤የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጀት የሠ/መ/ቁጥር 251398 Next Article አቶ ኃይለ ጊዮርግስ ይልማ ወልደአብ እና እነ አቶ አዲስ እሸቱ (4) ሰዎች የሰ/መ/ቁ 252056 Print 4790 Documents to download 251759(.docx, 142.83 KB) - 591 download(s)
የህጸናትን መብት እና የላቀ ጥቅም ከማስጠበቅ አንጻር... የህጸናትን መብት እና የላቀ ጥቅም ከማስጠበቅ አንጻር... Monday, March 9, 2026 862 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከUNFPA እና Save The Children International ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ የህጻናትን መብት እና የላቀ ጥቅም ከማስጠበቅ አንጻር በፍርድ ቤት መር አስማሚነት እና የማስማማት ክህሎት ላይ ለዳኞች ፤ረዳት ዳኞች እና የሶሻል ወርክ ባለሙያዎች የካቲት 27 እና 28 ቀን 2018 ዓ.ም 2ተኛ ዙር ስልጠና ሰጥቷል፡፡ Read more
በኢትዮጵያ የዴንማርክ አምባሳደር ክቡር ሱን ክሮግስትረፕ... በኢትዮጵያ የዴንማርክ አምባሳደር ክቡር ሱን ክሮግስትረፕ... Thursday, March 5, 2026 580 በኢትዮጵያ የዴንማርክ አምባሳደር ክቡር ሱን ክሮግስትረፕ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት በቀን 26/06/2018 ዓ.ም ጉብኝት አድርገዋል። Read more
የዳኝነትና የዴሞክራሲ ተቋማት እምርታ፤ ለሀገረ መንግስት... የዳኝነትና የዴሞክራሲ ተቋማት እምርታ፤ ለሀገረ መንግስት... Wednesday, March 4, 2026 685 የካቲት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ''የዳኝነትና የዴሞክራሲ ተቋማት እምርታ ለተሳካ ሀገረ መንግሥት ግንባታ" በሚል መሪ ቃል በዳኝነትና የዴሞክራሲ ተቋማት የለውጥ ስራዎች ላይ በማተኮር ሲካሄድ የቆየው የምክክር መድረክ ተጠናቋል። Read more
ከምርጫ ጉዳዮች ጋር በተያያዙ ቅሬታዎች እና አፈታት ላይ... ከምርጫ ጉዳዮች ጋር በተያያዙ ቅሬታዎች እና አፈታት ላይ... Friday, February 27, 2026 689 ከምርጫ ጉዳዮች ጋር በተያያዙ ቅሬታዎች እና አፈታት ላይ ለፌዴራል እና ለክልል ዳኞች ከቀን 09/06/2018 ዓ.ም ጀምሮ በ3 ዙር ለ9 ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና በቀን18/5/2018 ዓ.ም ተጠናቀቀ፡፡ Read more
10Mar2026 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Tuesday, March 10, 2026 Read more