Selam Warga / Tuesday, June 17, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation ጨመሬ ቶሎሳ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰ/መ/ቁጥር 267231፣267230 የአሁን አመልካች በምዕራብ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ/መ/ቁ 47863 እና በመ/ቁ በመ/ቁ 47862 በሁለቱም መዝገቦች ላይ 2ኛ ተከሳሽ ሲሆን ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበው የክስ ይዘትም አመልካች የኢትዮጵያ የፌዴራል ቡና እና ሻይ ባለስልጣን ግምቢ ቅርንጫፍ የቡና ላኪ ሸኚ ስምሪት ጣቢያ ላይ ቋሚ ሰራተኛ ሆኖ በባለሙያነት ተቀጥሮ እየሰራ እያለ በቡና ንግድ ውስጥ የማጭበርበር ድርጊት በመፈጸም ለራሱ የማይገባውን ጥቅም ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ በምዕራብ ወለጋ ዞን ግምቢ ከተማ ቀበሌ 05 በኢትዮጵያ ምርት ገበያ ግምቢ ቅርንጫፍ ግቢ ውስጥ ጥቅምት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ለማዕከላዊ ገበያ የሚቀርብ የተቀሸረ ቡና ዓይነቱ እና የሰሌዳ ቁጥሩ 3-A02958 A.A በሆነ ኤፍ.ኤስ፣አር መኪና ከነጆ ከተማ ተጭኖ በፕሎምፕ ታሽጎ የቡናው ፕሎምፕ ቁጥር GM-7 በሚባል የታሸገውን በሚልክበት ጊዜ የቡናውን መጠን አጣርቶ መላክ እያለበት የተቀሸረ 129 ኩንታል ተጭኖ እያለ 100 ኩንታል በሚል እንዲሁም ከአይራ ወረዳ በሲኖ ትራክ 210 ኩንታል ቡና የተጫነ ነዉ ተብሎ የተላከዉን ተቀብሎ በቡናው የይለፍ ወረቀት ላይ ይህንኑ መጠን በማረጋገጥ የይለፍ ወረቀት ከሰጠ በኋላ በዚሁ ቀን የተጠቀሱት መኪናዎች በጊምቢ ከተማ ልዩ ስሙ ሰርጤ ኬላ ቦታ ላይ በቁጥጥር ስር ውለዉ ሲፈተሹ 29 እና 70 ኩንታል ቡና እንደቅደም ተከተላቸዉ ከህግ ውጭ ጥራት በሌለው የማዳበሪያ ከረጢት ተጨምሮ እሱ በይለፍ ወረቀት ላይ ጽፎ ከሰጠው በላይ በተጨማሪ ተጭኖ ስለተገኘ የአዋጅ 1051/2009 አንቀጽ 19/5/ የሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 433/2007 አንቀጽ 41(1)(ቀ) በመተላለፍ የማይገባ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት አስቦ በቡና ንግድ ውስጥ የማጭበርበር ወንጀል ድርጊት ፈጽሟል የሚል ነው፡፡ መልካም ምንባብ… Previous Article አቶ መሀመድ አለሙ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰበር መዝገብ ቁጥር 266395 Next Article ወ/ሮ የማርውሃ ወርቅነህ እና እነ ወ/ሮ ዓለም ወርቅነህ የሰ.መ.ቁ 242314 Print 6334 Documents to download 267231(.pdf, 1.08 MB) - 1345 download(s)
የህጸናትን መብት እና የላቀ ጥቅም ከማስጠበቅ አንጻር... የህጸናትን መብት እና የላቀ ጥቅም ከማስጠበቅ አንጻር... Monday, March 9, 2026 863 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከUNFPA እና Save The Children International ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ የህጻናትን መብት እና የላቀ ጥቅም ከማስጠበቅ አንጻር በፍርድ ቤት መር አስማሚነት እና የማስማማት ክህሎት ላይ ለዳኞች ፤ረዳት ዳኞች እና የሶሻል ወርክ ባለሙያዎች የካቲት 27 እና 28 ቀን 2018 ዓ.ም 2ተኛ ዙር ስልጠና ሰጥቷል፡፡ Read more
በኢትዮጵያ የዴንማርክ አምባሳደር ክቡር ሱን ክሮግስትረፕ... በኢትዮጵያ የዴንማርክ አምባሳደር ክቡር ሱን ክሮግስትረፕ... Thursday, March 5, 2026 580 በኢትዮጵያ የዴንማርክ አምባሳደር ክቡር ሱን ክሮግስትረፕ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት በቀን 26/06/2018 ዓ.ም ጉብኝት አድርገዋል። Read more
የዳኝነትና የዴሞክራሲ ተቋማት እምርታ፤ ለሀገረ መንግስት... የዳኝነትና የዴሞክራሲ ተቋማት እምርታ፤ ለሀገረ መንግስት... Wednesday, March 4, 2026 686 የካቲት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ''የዳኝነትና የዴሞክራሲ ተቋማት እምርታ ለተሳካ ሀገረ መንግሥት ግንባታ" በሚል መሪ ቃል በዳኝነትና የዴሞክራሲ ተቋማት የለውጥ ስራዎች ላይ በማተኮር ሲካሄድ የቆየው የምክክር መድረክ ተጠናቋል። Read more
ከምርጫ ጉዳዮች ጋር በተያያዙ ቅሬታዎች እና አፈታት ላይ... ከምርጫ ጉዳዮች ጋር በተያያዙ ቅሬታዎች እና አፈታት ላይ... Friday, February 27, 2026 690 ከምርጫ ጉዳዮች ጋር በተያያዙ ቅሬታዎች እና አፈታት ላይ ለፌዴራል እና ለክልል ዳኞች ከቀን 09/06/2018 ዓ.ም ጀምሮ በ3 ዙር ለ9 ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና በቀን18/5/2018 ዓ.ም ተጠናቀቀ፡፡ Read more
10Mar2026 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Tuesday, March 10, 2026 Read more