Selam Warga / Tuesday, June 17, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation አቶ መሀመድ አለሙ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰበር መዝገብ ቁጥር 266395 ጉዳዩ የቀረበው የኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች 1ኛ ተከሳሽ አሁን የክርክሩ አካል ያልሆነው የትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ 2ኛ ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበው 1ኛ ክስ የወ/ህግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)፣ 34(1) እና 693(1) በመተላለፍ በትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ ውስጥ የፋብሪካው ኃላፊ እና ባለንብረት ሆኖ በሚሰሩበት ጊዜ ለግል ተበዳይ አቶ ሸምሱ አወል የብር አምስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የሚመነዘር ቼክ ሰጥቶ የግል ተበዳይ ገንዘቡን ለማውጣት ወደ ባንክ ሲሄድ በቂ ገንዘብ የለውም በመባሉ ገንዘቡን ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ስለዚህ በቂ ስንቅ ሳይኖር ቼክ በመስጠት ወንጀል ተከሷል የሚል ነው፡፡ አመልካች የወንጀሉን ድርጊት አልፈፀምኩም ብሎ ክዶ በመከራከሩ ተጠሪ የሰውና የሰነድ ማስረጃ አቅርቦ እንደ ክስ አቀራረቡ አስረድቷል፡፡ አመልካች እንዲከላከል ታዞ መከላከያ ማስረጃ ያቀረበ ሲሆን የአመልካች መከላከያ ምስክሮች ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቼክ መጥፋቱን አስረድተዋል፡፡መልካም ንባብ…. Previous Article ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594 Next Article ጨመሬ ቶሎሳ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰ/መ/ቁጥር 267231፣267230 Print 7379 Documents to download 266395(.pdf, 849.74 KB) - 972 download(s)
በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ምድብ... በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ምድብ... Friday, June 16, 2023 3226 በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ስር የተደራጀው የሕጻናት ፍትሕ ፕሮጀክት ከሕጻናት አድን ድርጅት (Save the Children) በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ምድብ ችሎት ያደራጀው የሕጻናት ማስመስከሪያ ማዕከል ሰኔ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ተመርቆ ተከፈተ፡፡ Read more
በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ምድብ... በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ምድብ... Friday, June 16, 2023 2712 በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ስር የተደራጀው የሕጻናት ፍትሕ ፕሮጀክት ከሕጻናት አድን ድርጅት (Save the Children) በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ምድብ ችሎት ያደራጀው የሕጻናት ማስመስከሪያ ማዕከል ሰኔ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ተመርቆ ተከፈተ፡፡ Read more
በሀገር አቀፍ የሕግ አውጪዎች የጋራ ምክክር መድረክ ላይ... በሀገር አቀፍ የሕግ አውጪዎች የጋራ ምክክር መድረክ ላይ... Tuesday, June 13, 2023 2558 የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ያዘጋጁት የለውጥ ፍኖተ ካርታ በሀገር አቀፍ የህግ አውጪዎች የጋራ መድረክ ላይ ቀረበ፡፡ Read more
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አመራሮች በድሬደዋ ከተማ ውጤታማ... የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አመራሮች በድሬደዋ ከተማ ውጤታማ... Tuesday, June 13, 2023 2892 በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የተመራ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ክብርት ወ/ሮ አበባ እምቢአለ፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክብርት ወ/ሮ ለሊሴ ደሳለኝ እና የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ፉአድ ኪያር እና የከፍተኛ እና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንቶች ያካተተ ልዑካን ቡድን አባላት በድሬዳዋ ከተማ ለሁለት ቀናት ያካሔዱት ውጤታማ የሆነ ጉብኝት ተጠናቋል፡፡ Read more
10Mar2026 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Tuesday, March 10, 2026 Read more