Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ ተስፋዬ ደገፋ እና ዶ/ር ትዕዛዙ ተፈራ ፤የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ጽ/ቤት፤የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት የሰ/መ/ቁ 259947

ለዚህ የሰበር ክርክር ምክንያት የሆነዉ ክርክር የተጀመረዉ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን በከፍተኛዉ ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ፣ ተጠሪዎች ደግሞ ተከሳሾች በመሆን መከራከራቸዉን የሥር ፍ/ቤቶች ዉሳኔ ያመለክታል፡፡ ክርክሩ በማህበር በመደራጀት ከተገኘዉ ይዞታ ጋር የተያያዘ ሲሆን አመልካች በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተጠሪዎች ላይ ባቀረቡት  ክስ በ03/08/1990 ዓ/ም ተመዝግቦ በፀደቀዉ የመተዳደሪያ ደንብ መሠረት የተደራጀ ታቦር የመኖሪያ ቤቶች ኅብረት ሥራ ማኅበር አባል በመሆን ተደራጅተዉ ማኅበሩ በሕጋዊ መንገድ ከመንግሥት ካገኘዉ ጠቅላላ ይዞታ ላይ መጠኑ 203.67 ካሬ ሜትር የሆነዉን የክርክሩን ይዞታ   በድርሻ እንደሰጣቸዉና የዚሁ ይዞታ ሕጋዊ ባለመብት ስለመሆናቸዉም በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 281839 በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ኅብረት ሥራ ጽ/ቤትና በኮልፌ  ቀራኒዮ ክለ ከተማ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት ላይ ክስ አቅርበዉ መብታቸዉ ተረጋግጦ ዉሳኔ እንዲያገኝ የሚል ነው፡መልካም ንባብ…

Previous Article ወ/ሮ ሙርሽዳ ሁሴን እና ወ/ሮ አልፊያ ሁሴን (13) ሰዎች የሰ/መ/ቁ 257243
Next Article ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594
Print
6686

Documents to download

  • 259947(.pdf, 828.26 KB) - 781 download(s)

«August 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
272829303112
3456789
10111213141516
17181920212223
24252627282930
31123456

ለፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች እና የሥራ ኃላፊዎች በአመራር...

3725

ከፌደራል ፍርድ ቤቶች ለተውጣጡ ዳኞች እና የሥራ ኃላፊዎች በአመራር ክህሎት (Leadership) ላይ የተዘጋጀ ሥልጠና በአሜሪካ አገር ከሚገኘውና ችክፍሌ (Chick-fil-A) ከተሰኘው ድርጅት በመጡ ስድስት ባለሙያዎች ሰኔ 19 ቀን 2015 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል ተሰጠ፡፡

ሥልጠናው የመሪነት ጽንሰ-ሐሳብ እና የጥሩ መሪ ስብዕናዎች የተዳሰሱበት ሲሆን በኃላፊነት ላይ የተቀመጡና በሥራቸው ውጤታማ የሆኑ ግለሰቦች ሁሉ መሪ (Leader) ሊሆኑ እንደማይችሉም ተገልጿል፡፡

በፌደራል ፍርድ ቤቶች የለውጥ ፍኖተ-ካርታ ላይ ውይይት ተካሔደ

3712

በፌደራል ፍርድ ቤቶች የለውጥ ፍኖተ ካርታ ላይ በጥብቅና ሙያ ተሰማርተው አገልግሎት በመስጠት ላይ ለሚገኙ ጠበቆች በፌደራል ፍርድ ቤቶች ከፍተኛ አመራሮች ሰኔ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ገለጻ ተደርጓል፡፡

ለፌደራል ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የተገነባው...

3836

ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት በከፍተኛ ፍርድ ቤት ቅጥር ግቢ አዲስ የተገነባው ባለሶስት ወለል (G+2) ሕንጻ ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ.ም በፍርድ ቤቱ ፕሬዚደንት በክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በይፋ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡

ተወላጅነትን በማረጋገጥ እና በመካድ ክርክር እንዲሁም...

4314

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሕጻናት ፍትሕ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ተወላጅነትን በማረጋገጥ እና በመካድ ክርክር እንዲሁም በዘረመል ምርመራ አጠቃቀም ላይ ለፌደራል ፍርድ ቤት ዳኞች ያዘጋጀው የሥልጠና እና የውይይት መድረክ ከሰኔ 10-11 ቀን 2015 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ ተካሒዷል፡፡

First5657585961636465Last