Selam Warga / Tuesday, June 17, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation አቶ መሀመድ አለሙ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰበር መዝገብ ቁጥር 266395 ጉዳዩ የቀረበው የኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች 1ኛ ተከሳሽ አሁን የክርክሩ አካል ያልሆነው የትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ 2ኛ ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበው 1ኛ ክስ የወ/ህግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)፣ 34(1) እና 693(1) በመተላለፍ በትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ ውስጥ የፋብሪካው ኃላፊ እና ባለንብረት ሆኖ በሚሰሩበት ጊዜ ለግል ተበዳይ አቶ ሸምሱ አወል የብር አምስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የሚመነዘር ቼክ ሰጥቶ የግል ተበዳይ ገንዘቡን ለማውጣት ወደ ባንክ ሲሄድ በቂ ገንዘብ የለውም በመባሉ ገንዘቡን ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ስለዚህ በቂ ስንቅ ሳይኖር ቼክ በመስጠት ወንጀል ተከሷል የሚል ነው፡፡ አመልካች የወንጀሉን ድርጊት አልፈፀምኩም ብሎ ክዶ በመከራከሩ ተጠሪ የሰውና የሰነድ ማስረጃ አቅርቦ እንደ ክስ አቀራረቡ አስረድቷል፡፡ አመልካች እንዲከላከል ታዞ መከላከያ ማስረጃ ያቀረበ ሲሆን የአመልካች መከላከያ ምስክሮች ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቼክ መጥፋቱን አስረድተዋል፡፡መልካም ንባብ…. Previous Article ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594 Next Article ጨመሬ ቶሎሳ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰ/መ/ቁጥር 267231፣267230 Print 7937 Documents to download 266395(.pdf, 849.74 KB) - 1013 download(s)
በፌደራል ፍርድ ቤቶች የለውጥ ፍኖተ-ካርታ ላይ ውይይት ተካሔደ በፌደራል ፍርድ ቤቶች የለውጥ ፍኖተ-ካርታ ላይ ውይይት ተካሔደ Monday, June 26, 2023 3703 በፌደራል ፍርድ ቤቶች የለውጥ ፍኖተ ካርታ ላይ በጥብቅና ሙያ ተሰማርተው አገልግሎት በመስጠት ላይ ለሚገኙ ጠበቆች በፌደራል ፍርድ ቤቶች ከፍተኛ አመራሮች ሰኔ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ገለጻ ተደርጓል፡፡ Read more
ለፌደራል ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የተገነባው... ለፌደራል ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የተገነባው... Tuesday, June 20, 2023 3813 ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት በከፍተኛ ፍርድ ቤት ቅጥር ግቢ አዲስ የተገነባው ባለሶስት ወለል (G+2) ሕንጻ ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ.ም በፍርድ ቤቱ ፕሬዚደንት በክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በይፋ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡ Read more
ተወላጅነትን በማረጋገጥ እና በመካድ ክርክር እንዲሁም... ተወላጅነትን በማረጋገጥ እና በመካድ ክርክር እንዲሁም... Monday, June 19, 2023 4287 የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሕጻናት ፍትሕ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ተወላጅነትን በማረጋገጥ እና በመካድ ክርክር እንዲሁም በዘረመል ምርመራ አጠቃቀም ላይ ለፌደራል ፍርድ ቤት ዳኞች ያዘጋጀው የሥልጠና እና የውይይት መድረክ ከሰኔ 10-11 ቀን 2015 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ ተካሒዷል፡፡ Read more
በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ምድብ... በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ምድብ... Friday, June 16, 2023 3507 በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ስር የተደራጀው የሕጻናት ፍትሕ ፕሮጀክት ከሕጻናት አድን ድርጅት (Save the Children) በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ምድብ ችሎት ያደራጀው የሕጻናት ማስመስከሪያ ማዕከል ሰኔ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ተመርቆ ተከፈተ፡፡ Read more