Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ ተስፋዬ ደገፋ እና ዶ/ር ትዕዛዙ ተፈራ ፤የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ጽ/ቤት፤የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት የሰ/መ/ቁ 259947

ለዚህ የሰበር ክርክር ምክንያት የሆነዉ ክርክር የተጀመረዉ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን በከፍተኛዉ ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ፣ ተጠሪዎች ደግሞ ተከሳሾች በመሆን መከራከራቸዉን የሥር ፍ/ቤቶች ዉሳኔ ያመለክታል፡፡ ክርክሩ በማህበር በመደራጀት ከተገኘዉ ይዞታ ጋር የተያያዘ ሲሆን አመልካች በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተጠሪዎች ላይ ባቀረቡት  ክስ በ03/08/1990 ዓ/ም ተመዝግቦ በፀደቀዉ የመተዳደሪያ ደንብ መሠረት የተደራጀ ታቦር የመኖሪያ ቤቶች ኅብረት ሥራ ማኅበር አባል በመሆን ተደራጅተዉ ማኅበሩ በሕጋዊ መንገድ ከመንግሥት ካገኘዉ ጠቅላላ ይዞታ ላይ መጠኑ 203.67 ካሬ ሜትር የሆነዉን የክርክሩን ይዞታ   በድርሻ እንደሰጣቸዉና የዚሁ ይዞታ ሕጋዊ ባለመብት ስለመሆናቸዉም በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 281839 በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ኅብረት ሥራ ጽ/ቤትና በኮልፌ  ቀራኒዮ ክለ ከተማ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት ላይ ክስ አቅርበዉ መብታቸዉ ተረጋግጦ ዉሳኔ እንዲያገኝ የሚል ነው፡መልካም ንባብ…

Previous Article ወ/ሮ ሙርሽዳ ሁሴን እና ወ/ሮ አልፊያ ሁሴን (13) ሰዎች የሰ/መ/ቁ 257243
Next Article ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594
Print
6570

Documents to download

  • 259947(.pdf, 828.26 KB) - 779 download(s)

«August 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
272829303112
3456789
10111213141516
17181920212223
24252627282930
31123456

በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ምድብ...

2972
በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ስር የተደራጀው የሕጻናት ፍትሕ ፕሮጀክት ከሕጻናት አድን ድርጅት (Save the Children) በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ምድብ ችሎት ያደራጀው የሕጻናት ማስመስከሪያ ማዕከል ሰኔ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ተመርቆ ተከፈተ፡፡

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አመራሮች በድሬደዋ ከተማ ውጤታማ...

3185
በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የተመራ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ክብርት ወ/ሮ አበባ እምቢአለ፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክብርት ወ/ሮ ለሊሴ ደሳለኝ እና የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ፉአድ ኪያር እና የከፍተኛ እና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንቶች ያካተተ ልዑካን ቡድን አባላት በድሬዳዋ ከተማ ለሁለት ቀናት ያካሔዱት ውጤታማ የሆነ ጉብኝት ተጠናቋል፡፡

ፍ/ቤቶች የሕጻናትን መብቶችና ጥቅሞች ከማስከበር አንጻር...

3901

የፌደራል ፍ/ቤቶች የሕጻናትን መብቶችና ጥቅሞች ከማስከበር አንጻር ያለባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት የተለያዩ ጥረቶችን በማድረግ ላይ እንደሚገኙ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ክብርት ወ/ሮ ሌሊሴ ደሳለኝ ገለጹ፡፡

First5758596062646566Last