Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ መሀመድ አለሙ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰበር መዝገብ ቁጥር 266395

ጉዳዩ የቀረበው የኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች 1ኛ ተከሳሽ አሁን የክርክሩ አካል ያልሆነው የትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ 2ኛ ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበው 1ኛ ክስ የወ/ህግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)፣ 34(1) እና 693(1) በመተላለፍ በትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ ውስጥ የፋብሪካው ኃላፊ እና ባለንብረት ሆኖ በሚሰሩበት ጊዜ ለግል ተበዳይ አቶ ሸምሱ አወል የብር አምስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የሚመነዘር ቼክ ሰጥቶ የግል ተበዳይ ገንዘቡን ለማውጣት ወደ ባንክ ሲሄድ በቂ ገንዘብ የለውም በመባሉ ገንዘቡን ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ስለዚህ በቂ ስንቅ ሳይኖር ቼክ በመስጠት ወንጀል ተከሷል የሚል ነው፡፡ አመልካች የወንጀሉን ድርጊት አልፈፀምኩም ብሎ ክዶ በመከራከሩ ተጠሪ የሰውና የሰነድ ማስረጃ አቅርቦ እንደ ክስ አቀራረቡ አስረድቷል፡፡ አመልካች እንዲከላከል ታዞ መከላከያ ማስረጃ ያቀረበ ሲሆን የአመልካች መከላከያ ምስክሮች ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቼክ መጥፋቱን አስረድተዋል፡፡መልካም ንባብ…. 

Previous Article ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594
Next Article ጨመሬ ቶሎሳ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰ/መ/ቁጥር 267231፣267230
Print
8048

Documents to download

  • 266395(.pdf, 849.74 KB) - 1020 download(s)

«August 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
272829303112
3456789
10111213141516
17181920212223
24252627282930
31123456

ፍ/ቤቶች የሕጻናትን መብቶችና ጥቅሞች ከማስከበር አንጻር...

3914

የፌደራል ፍ/ቤቶች የሕጻናትን መብቶችና ጥቅሞች ከማስከበር አንጻር ያለባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት የተለያዩ ጥረቶችን በማድረግ ላይ እንደሚገኙ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ክብርት ወ/ሮ ሌሊሴ ደሳለኝ ገለጹ፡፡

በመቀሌ ስካሄድ የነበረዉ የፌደራል እና የክልል ፍርድ...

3850
(ግንቦት 19/2015 ዓ.ም) በአዉሮፓ ህብረት ቴክኒካዊ ድጋፍ በኢትዮጵያ የወንጀል ፍትህ አስተዳደር ሪፎርም የሚደግፍ ፕሮጀክት ተቀርጾ እየተከናወነ የመሚገኘኝ ሲሆን ፕሮጀክቱ በአጠቃላይ የኢትዮጵያ መንግስት የወንጀል ፍትህ አስተዳደር ሪፎርም ሥራዎች የሚደግፍና የፌደራል ፍርድ ቤቶች እና የክልል ፍርድ ቤቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነዉ።

በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የዘጠኝ ወር ዕቅድ አፈጻጸም ላይ...

3821
በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአስተዳደር ዘርፍ የ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት የዘጠኝ ወር ዕቅድ አፈጻጸም ላይ የተዘጋጀ ውይይት በፍ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ግንቦት 12 ቀን 2015 ዓ.ም ተካሔደ፡፡

የሕጻናት ፍትሕ ፕሮጀክት ጽ/ቤት በሕጻናት የቅብብሎሽ...

7053
በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሕጻናት ፍትሕ ፕሮጀክት ጽ/ቤት በፍትሕ ሥርዓቱ ውስጥ የሚያልፉ ሕጻናት የዘርፈ-ብዙ አገልግሎት ተጠቃሚ በሚሆኑበት የቅብብሎሽ ሥርዓት ዙሪያ ያዘጋጀው የውይይት መድረክ ግንቦት 8 ቀን 2015 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ ጎልድ ማርክ ሆቴል ተካሂዷል፡፡
First5859606163656667Last