Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ መሀመድ አለሙ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰበር መዝገብ ቁጥር 266395

ጉዳዩ የቀረበው የኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች 1ኛ ተከሳሽ አሁን የክርክሩ አካል ያልሆነው የትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ 2ኛ ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበው 1ኛ ክስ የወ/ህግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)፣ 34(1) እና 693(1) በመተላለፍ በትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ ውስጥ የፋብሪካው ኃላፊ እና ባለንብረት ሆኖ በሚሰሩበት ጊዜ ለግል ተበዳይ አቶ ሸምሱ አወል የብር አምስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የሚመነዘር ቼክ ሰጥቶ የግል ተበዳይ ገንዘቡን ለማውጣት ወደ ባንክ ሲሄድ በቂ ገንዘብ የለውም በመባሉ ገንዘቡን ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ስለዚህ በቂ ስንቅ ሳይኖር ቼክ በመስጠት ወንጀል ተከሷል የሚል ነው፡፡ አመልካች የወንጀሉን ድርጊት አልፈፀምኩም ብሎ ክዶ በመከራከሩ ተጠሪ የሰውና የሰነድ ማስረጃ አቅርቦ እንደ ክስ አቀራረቡ አስረድቷል፡፡ አመልካች እንዲከላከል ታዞ መከላከያ ማስረጃ ያቀረበ ሲሆን የአመልካች መከላከያ ምስክሮች ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቼክ መጥፋቱን አስረድተዋል፡፡መልካም ንባብ…. 

Previous Article ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594
Next Article ጨመሬ ቶሎሳ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰ/መ/ቁጥር 267231፣267230
Print
7375

Documents to download

  • 266395(.pdf, 849.74 KB) - 972 download(s)

«July 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
293012345
6789101112
13141516171819
20212223242526
272829303112
3456789

ፍርድ ቤቱ እና የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት...

2949
የፈደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንሰቲትዩት በቴክኖሎጂ ዘርፍ አብሮ ለመስራት የሚያስችልላቸውን የመግባቢያ ስምምነት በፍርድ ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ መጋቢት 14 ቀን 2015 ዓ.ም ተፈራረሙ።

በፌደራል ፍርድ ቤቶች የአስተዳደር ሠራተኞች ረቂቅ ደንብ...

2768
ለኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቀረበው የፌደራል ፍርድ ቤቶች የአስተዳደር ሠራተኞች ረቂቅ ደንብ ይዘት ላይ በፌደራል ፍርድ ቤቶች የሥራ ኃላፊዎች አማካኝነት ለም/ቤቱ የሕግና ፍትሕ ቋሚ ኮሚቴ እና ለሰው ሐብት ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት መጋቢት 11 ቀን 2015 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ማብራሪያ ተሰጠ፡፡

ለፍትሕ ሥርዓቱ ውጤታማነት የዳኞች፣ የአቃቢያነ-ሕግ እና...

2931
የፍትሕ ሥርዓቱ ውጤታማነት እንዲረጋገጥ ዳኞች፣ አቃቢያነ-ሕግ እና ጠበቆች ሙያዊ ነጻነት ኖሮአቸው በፍትሕ ሥርዓቱ ሊሳተፉ እንደሚገባ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምሕረት ገለጹ፡፡

ለቋሚ ኮሚቴ አባላት በፌደራል ፍርድ ቤቶች አስተደደር...

2703
በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚፀድቅ በሚጠበቀው የፌደራል ፍርድ ቤቶች አስተዳደር ሠራተኞች ረቂቅ ደንብ ይዘት ላይ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ለሕግና ፍትሕ ቋሚ ኮሚቴ እና ለሰው ሐብት ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች እና አባላት መጋቢት 2 ቀን 2015 ዓ.ም ገለጻ ተደረገ፡፡
First5960616264666768Last