Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ ተስፋዬ ደገፋ እና ዶ/ር ትዕዛዙ ተፈራ ፤የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ጽ/ቤት፤የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት የሰ/መ/ቁ 259947

ለዚህ የሰበር ክርክር ምክንያት የሆነዉ ክርክር የተጀመረዉ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን በከፍተኛዉ ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ፣ ተጠሪዎች ደግሞ ተከሳሾች በመሆን መከራከራቸዉን የሥር ፍ/ቤቶች ዉሳኔ ያመለክታል፡፡ ክርክሩ በማህበር በመደራጀት ከተገኘዉ ይዞታ ጋር የተያያዘ ሲሆን አመልካች በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተጠሪዎች ላይ ባቀረቡት  ክስ በ03/08/1990 ዓ/ም ተመዝግቦ በፀደቀዉ የመተዳደሪያ ደንብ መሠረት የተደራጀ ታቦር የመኖሪያ ቤቶች ኅብረት ሥራ ማኅበር አባል በመሆን ተደራጅተዉ ማኅበሩ በሕጋዊ መንገድ ከመንግሥት ካገኘዉ ጠቅላላ ይዞታ ላይ መጠኑ 203.67 ካሬ ሜትር የሆነዉን የክርክሩን ይዞታ   በድርሻ እንደሰጣቸዉና የዚሁ ይዞታ ሕጋዊ ባለመብት ስለመሆናቸዉም በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 281839 በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ኅብረት ሥራ ጽ/ቤትና በኮልፌ  ቀራኒዮ ክለ ከተማ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት ላይ ክስ አቅርበዉ መብታቸዉ ተረጋግጦ ዉሳኔ እንዲያገኝ የሚል ነው፡መልካም ንባብ…

Previous Article ወ/ሮ ሙርሽዳ ሁሴን እና ወ/ሮ አልፊያ ሁሴን (13) ሰዎች የሰ/መ/ቁ 257243
Next Article ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594
Print
6570

Documents to download

  • 259947(.pdf, 828.26 KB) - 779 download(s)

«August 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
272829303112
3456789
10111213141516
17181920212223
24252627282930
31123456

የፍርድ ቤቱ አዲስ ተሿሚ ፕሬዝዳንቶች እና በቀድሞ...

3380
መጋቢት 27ቀን 2015 ዓ.ም፡- የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አዲስ በተሾሙ ፕሬዝዳንቶች እና በቀድሞ ፕሬዝዳንቶች መካከል የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳነት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምሕረት (ረዳት ፕሮፌሰር) በተገኙበት የስራ ርክክብ ስነስረዓት ተፈጸመ፡፡

ፍርድ ቤቱ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ያደረገው ስምምነት የፍርድ...

2733
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከኢትዮጵያ ቴሌኮም ጋር የተፈራረመው የመግባቢያ ስምምነት (Memorandum of Understanding) በዳኝነት አገልግሎት አሠጣጥ ዘርፍ የተሰማሩ የፍርድ ቤቱን ዳኞችና ሌሎች ባለሙያዎች ጫና ለመቀነስና የፍ/ቤቱን አገልግሎት ለተጠቃሚዎች ተደራሽ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ገለጹ፡፡

የፍርድ ቤት ተገልጋዮችን እንግልት የሚቀንሱ እና የፍትሕ...

3071
የፍርድ ቤት ተገልጋዮችን ጊዜ፣ ጉልበት እና የገንዘብ ወጪ የሚቀንሱ እና የፍትሕ እርካታ የሚጨምሩ የማሻሻያ ሥራዎች የሚከናወኑ መሆኑን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ገለጹ፡፡

ፍርድ ቤቱ እና የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት...

3213
የፈደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንሰቲትዩት በቴክኖሎጂ ዘርፍ አብሮ ለመስራት የሚያስችልላቸውን የመግባቢያ ስምምነት በፍርድ ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ መጋቢት 14 ቀን 2015 ዓ.ም ተፈራረሙ።
First6061626365676869Last