Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ መሀመድ አለሙ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰበር መዝገብ ቁጥር 266395

ጉዳዩ የቀረበው የኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች 1ኛ ተከሳሽ አሁን የክርክሩ አካል ያልሆነው የትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ 2ኛ ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበው 1ኛ ክስ የወ/ህግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)፣ 34(1) እና 693(1) በመተላለፍ በትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ ውስጥ የፋብሪካው ኃላፊ እና ባለንብረት ሆኖ በሚሰሩበት ጊዜ ለግል ተበዳይ አቶ ሸምሱ አወል የብር አምስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የሚመነዘር ቼክ ሰጥቶ የግል ተበዳይ ገንዘቡን ለማውጣት ወደ ባንክ ሲሄድ በቂ ገንዘብ የለውም በመባሉ ገንዘቡን ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ስለዚህ በቂ ስንቅ ሳይኖር ቼክ በመስጠት ወንጀል ተከሷል የሚል ነው፡፡ አመልካች የወንጀሉን ድርጊት አልፈፀምኩም ብሎ ክዶ በመከራከሩ ተጠሪ የሰውና የሰነድ ማስረጃ አቅርቦ እንደ ክስ አቀራረቡ አስረድቷል፡፡ አመልካች እንዲከላከል ታዞ መከላከያ ማስረጃ ያቀረበ ሲሆን የአመልካች መከላከያ ምስክሮች ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቼክ መጥፋቱን አስረድተዋል፡፡መልካም ንባብ…. 

Previous Article ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594
Next Article ጨመሬ ቶሎሳ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰ/መ/ቁጥር 267231፣267230
Print
7349

Documents to download

  • 266395(.pdf, 849.74 KB) - 971 download(s)

«July 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
293012345
6789101112
13141516171819
20212223242526
272829303112
3456789

በፌደራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ነጻነት፣ ተጠያቂነትና...

2827
በፌደራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ነጻነት፣ ተጠያቂነትና የሕግ ማዕቀፎች ዙሪያ ከሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሕግና ፍትሕ ቋሚ ኮሚቴ እና ከሰው ሐብት ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር መጋቢት 1 ቀን 2015 ዓ.ም የምክክር መድረክ ተካሔደ፡፡

በፌደራል ፍርድ ቤቶች የሴቶችን ተሳትፎና እኩልነት...

2461

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በፌደራል ፍርድ ቤቶች የሴቶችን ተሳትፎና እኩልነት ለማረጋገጥ የሚረዱ የተለያዩ የፖሊሲ እርምጃዎችን እየወሰደ እንደሚገኝ የፍ/ቤቱ ም/ፕሬዚደንት ክብርት ወ/ሮ አበባ እምቢአለ ገለጹ፡፡

የፍርድ ቤቱ ዳኞች የሰበር ሂደት በሚመራበት ረቂቅ...

2698

የሰበር የዳኝነት አሰጣጥ ስርዓት ግልጽ፣ ቀልጣፋ፣ ተገማች እና ውጤታማ ለማድረግ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በተዘጋጀ ረቂቅ የሰበር የሥነሥርዓት መመሪያ ረቂቅ ላይ ግብአት ለማሰባሰብ የፍርድ ቤቱ ዳኞች ውይይት አካሔዱ፡፡

First6061626365676869Last