Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ መሀመድ አለሙ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰበር መዝገብ ቁጥር 266395

ጉዳዩ የቀረበው የኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች 1ኛ ተከሳሽ አሁን የክርክሩ አካል ያልሆነው የትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ 2ኛ ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበው 1ኛ ክስ የወ/ህግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)፣ 34(1) እና 693(1) በመተላለፍ በትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ ውስጥ የፋብሪካው ኃላፊ እና ባለንብረት ሆኖ በሚሰሩበት ጊዜ ለግል ተበዳይ አቶ ሸምሱ አወል የብር አምስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የሚመነዘር ቼክ ሰጥቶ የግል ተበዳይ ገንዘቡን ለማውጣት ወደ ባንክ ሲሄድ በቂ ገንዘብ የለውም በመባሉ ገንዘቡን ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ስለዚህ በቂ ስንቅ ሳይኖር ቼክ በመስጠት ወንጀል ተከሷል የሚል ነው፡፡ አመልካች የወንጀሉን ድርጊት አልፈፀምኩም ብሎ ክዶ በመከራከሩ ተጠሪ የሰውና የሰነድ ማስረጃ አቅርቦ እንደ ክስ አቀራረቡ አስረድቷል፡፡ አመልካች እንዲከላከል ታዞ መከላከያ ማስረጃ ያቀረበ ሲሆን የአመልካች መከላከያ ምስክሮች ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቼክ መጥፋቱን አስረድተዋል፡፡መልካም ንባብ…. 

Previous Article ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594
Next Article ጨመሬ ቶሎሳ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰ/መ/ቁጥር 267231፣267230
Print
7375

Documents to download

  • 266395(.pdf, 849.74 KB) - 972 download(s)

«July 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
293012345
6789101112
13141516171819
20212223242526
272829303112
3456789

የወንጀል ህጉ ለህጻናት ትኩረት አለመስጠቱ ከህጻናት ጋር...

2773

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስር የተቋቋመዉ የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ጽ/ቤት የካቲት 17 ቀን 2015 ዓ.ም በሕጻናት ጉዳይ ላይ ለሚሰሩ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት፣ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት፣ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ዳኞችና ለሶሻል ወርክ ባለሙያዎች ባዘጋጀዉ የሥልጠና መድረክ ላይ ከህጻናት ጋር ተያያዥነት ላላቸዉ ወንጀሎች መበራከት ዋነኛ መንስኤዉ የወንጀል ህጉ ለህጻናት ትኩረት አለመስጠቱ መሆኑ ተገለጸ፡፡

በፍርድ ቤቶች መልስ ሰጪን ሳያስቀርቡ ይግባኝን መዝጋት...

3050

በመደበኛ ይግባኝ ፍ/ቤቶች እንዲሁም በሰበር ችሎቶች ያለው መልስ ሰጪን ሳያስቀርቡ ይግባኙን መዝጋት ወይም «አያስቀርብም» የሚለው አሠራር በበርካታ የሕግ ባለሙያዎች ቅሬታ የሚቀርብበት አሠራር መሆኑን በመጥቀስ በዘርፉ የተካሔደ አጭር የዳሰሳ ጥናት በፌደራል ጠ/ፍ/ቤት የሕግ ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ አሮን ደጎል ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

ለቀድሞዎቹ የፍ/ቤቱ ፕሬዚደንት እና ም/ፕሬዚደንት...

3168

ለቀድሞዎቹ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት እና ም/ፕሬዚደንት ለክብርት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊና ለክቡር አቶ ሰለሞን አረዳ የካቲት 11 ቀን 2015 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል አሸኛኘት ተደረገላቸው፡፡

አሸኛኘቱን ያደረጉት አዲስ የተሾሙት የፍ/ቤቱ ፕሬዚደንት እና ም/ፕሬዚደንትነት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምሕረት እና ክብርት ወ/ሮ አበባ እምቢአለን ጨምሮ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞችና የሶስቱም የፌደራል ፍ/ቤቶች አመራሮች ናቸው፡፡

First6162636466686970Last