Selam Warga / Tuesday, June 17, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation አቶ ተስፋዬ ደገፋ እና ዶ/ር ትዕዛዙ ተፈራ ፤የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ጽ/ቤት፤የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት የሰ/መ/ቁ 259947 ለዚህ የሰበር ክርክር ምክንያት የሆነዉ ክርክር የተጀመረዉ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን በከፍተኛዉ ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ፣ ተጠሪዎች ደግሞ ተከሳሾች በመሆን መከራከራቸዉን የሥር ፍ/ቤቶች ዉሳኔ ያመለክታል፡፡ ክርክሩ በማህበር በመደራጀት ከተገኘዉ ይዞታ ጋር የተያያዘ ሲሆን አመልካች በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተጠሪዎች ላይ ባቀረቡት ክስ በ03/08/1990 ዓ/ም ተመዝግቦ በፀደቀዉ የመተዳደሪያ ደንብ መሠረት የተደራጀ ታቦር የመኖሪያ ቤቶች ኅብረት ሥራ ማኅበር አባል በመሆን ተደራጅተዉ ማኅበሩ በሕጋዊ መንገድ ከመንግሥት ካገኘዉ ጠቅላላ ይዞታ ላይ መጠኑ 203.67 ካሬ ሜትር የሆነዉን የክርክሩን ይዞታ በድርሻ እንደሰጣቸዉና የዚሁ ይዞታ ሕጋዊ ባለመብት ስለመሆናቸዉም በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 281839 በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ኅብረት ሥራ ጽ/ቤትና በኮልፌ ቀራኒዮ ክለ ከተማ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት ላይ ክስ አቅርበዉ መብታቸዉ ተረጋግጦ ዉሳኔ እንዲያገኝ የሚል ነው፡መልካም ንባብ… Previous Article ወ/ሮ ሙርሽዳ ሁሴን እና ወ/ሮ አልፊያ ሁሴን (13) ሰዎች የሰ/መ/ቁ 257243 Next Article ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594 Print 6686 Documents to download 259947(.pdf, 828.26 KB) - 781 download(s)
በፌደራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ነጻነት፣ ተጠያቂነትና... በፌደራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ነጻነት፣ ተጠያቂነትና... Monday, March 13, 2023 3120 በፌደራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ነጻነት፣ ተጠያቂነትና የሕግ ማዕቀፎች ዙሪያ ከሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሕግና ፍትሕ ቋሚ ኮሚቴ እና ከሰው ሐብት ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር መጋቢት 1 ቀን 2015 ዓ.ም የምክክር መድረክ ተካሔደ፡፡ Read more
የሰበር ሂደት በሚመራበት ረቂቅ የሥነሥርዓት መመሪያ ላይ... የሰበር ሂደት በሚመራበት ረቂቅ የሥነሥርዓት መመሪያ ላይ... Friday, March 10, 2023 3269 በረቂቅ ደረጃ በሚገኘው የሰበር ረቂቅ የሥነሥርዓት መመሪያ ላይ ግብአት ለማሰባሰብ የተዘጋጀ የውይይት መድረክ የካቲት 30 ቀን 2015 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል ተካሔደ፡፡ Read more
በፌደራል ፍርድ ቤቶች የሴቶችን ተሳትፎና እኩልነት... በፌደራል ፍርድ ቤቶች የሴቶችን ተሳትፎና እኩልነት... Thursday, March 9, 2023 2753 የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በፌደራል ፍርድ ቤቶች የሴቶችን ተሳትፎና እኩልነት ለማረጋገጥ የሚረዱ የተለያዩ የፖሊሲ እርምጃዎችን እየወሰደ እንደሚገኝ የፍ/ቤቱ ም/ፕሬዚደንት ክብርት ወ/ሮ አበባ እምቢአለ ገለጹ፡፡ Read more
የፍርድ ቤቱ ዳኞች የሰበር ሂደት በሚመራበት ረቂቅ... Monday, March 6, 2023 3046 የሰበር የዳኝነት አሰጣጥ ስርዓት ግልጽ፣ ቀልጣፋ፣ ተገማች እና ውጤታማ ለማድረግ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በተዘጋጀ ረቂቅ የሰበር የሥነሥርዓት መመሪያ ረቂቅ ላይ ግብአት ለማሰባሰብ የፍርድ ቤቱ ዳኞች ውይይት አካሔዱ፡፡ Read more