Selam Warga / Tuesday, June 17, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation አቶ መሀመድ አለሙ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰበር መዝገብ ቁጥር 266395 ጉዳዩ የቀረበው የኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች 1ኛ ተከሳሽ አሁን የክርክሩ አካል ያልሆነው የትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ 2ኛ ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበው 1ኛ ክስ የወ/ህግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)፣ 34(1) እና 693(1) በመተላለፍ በትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ ውስጥ የፋብሪካው ኃላፊ እና ባለንብረት ሆኖ በሚሰሩበት ጊዜ ለግል ተበዳይ አቶ ሸምሱ አወል የብር አምስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የሚመነዘር ቼክ ሰጥቶ የግል ተበዳይ ገንዘቡን ለማውጣት ወደ ባንክ ሲሄድ በቂ ገንዘብ የለውም በመባሉ ገንዘቡን ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ስለዚህ በቂ ስንቅ ሳይኖር ቼክ በመስጠት ወንጀል ተከሷል የሚል ነው፡፡ አመልካች የወንጀሉን ድርጊት አልፈፀምኩም ብሎ ክዶ በመከራከሩ ተጠሪ የሰውና የሰነድ ማስረጃ አቅርቦ እንደ ክስ አቀራረቡ አስረድቷል፡፡ አመልካች እንዲከላከል ታዞ መከላከያ ማስረጃ ያቀረበ ሲሆን የአመልካች መከላከያ ምስክሮች ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቼክ መጥፋቱን አስረድተዋል፡፡መልካም ንባብ…. Previous Article ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594 Next Article ጨመሬ ቶሎሳ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰ/መ/ቁጥር 267231፣267230 Print 7937 Documents to download 266395(.pdf, 849.74 KB) - 1013 download(s)
በዳኝነት ሥርዓቱ በሚታዩ ችግሮችና ሊወሰዱ በሚገባቸው... በዳኝነት ሥርዓቱ በሚታዩ ችግሮችና ሊወሰዱ በሚገባቸው... Tuesday, January 31, 2023 3080 የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚደንት እና ም/ፕሬዚደንት በዳኝነት ሥርዓቱ ዙሪያ በሚታዩ ችግሮችና ሊወሰዱ በሚገባቸው የመፍትሔ አቅጣጫዎች ላይ ከሶስቱም የፌደራል ፍርድ ቤቶች ከተውጣጡ 150 ከሚሆኑ የፍ/ቤቶቹ አመራሮችና ዳኞች ጋር ውይይት አካሂደዋል፡፡ Read more
በዳኝነት ዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ከተለመደው... በዳኝነት ዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ከተለመደው... Thursday, January 26, 2023 2786 የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አዲሱ አመራር በፍ/ቤቱ ሥራ የጀመረው የነበረውን አሠራር ለማስቀጠል ብቻ ሳይሆን በዳኝነት ዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ከተለመደው አሠራር ወጣ ያሉ አዳዲስ አሠራሮችን ተግባራዊ ለማድረግ መሆኑን የፍ/ቤቱ ፕሬዚደንት ሆነው የተሾሙት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምሕረት ገለጹ፡፡ Read more
በፍርድ ቤቱ አዲስ ተሿሚ ፕሬዚደንቶች እና በቀድሞ... በፍርድ ቤቱ አዲስ ተሿሚ ፕሬዚደንቶች እና በቀድሞ... Monday, January 23, 2023 2935 ለፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት አዲስ በተሾሙ ፕሬዚደንቶች እና በቀድሞ ፕሬዚደንቶች መካከል የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ በተገኙበት በፍርድ ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ጥር 15 ቀን 2015 ዓ.ም በተካሔደ ሥነሥርዓት የሥራ ርክክብ ተካሔደ፡፡ Read more
"ፍርድ ቤቱ አገልግሎት ፈላጊዎችን በተሻለ ለማስተናገድ... "ፍርድ ቤቱ አገልግሎት ፈላጊዎችን በተሻለ ለማስተናገድ... Monday, January 16, 2023 3140 የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አገልግሎት ፈላጊዎችን በተሻለ መልኩ ለማስተናገድ የሚረዱ የለውጥ ስራዎች ላይ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሳሰበ። Read more