Selam Warga / Wednesday, June 4, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ቀበሌ 11/12/08 ሸማቾች ኃ/የተ/ሕ/ሥ/ማ እና አቶ እንኮሳ አመንቴ ሱፋ(9ሰዎች)የሰ.መ.ቁ 249104 የክሱ ይዘት በአጭሩ፡- በየካ አውራጃ ከፍተኛ 16 ቀበሌ 08 የቀድሞው የቀበሌ አመራሮች የተጠሪዎችን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ በማሰብ ከህብረት ሥራ ማህበር ብር 29.000 (ሃያ ዘጠኝ ሺህ ብር) በብድር መልክ ወጪ ተደርጎ ቤት እንድንገነባ ተፈቅዶልን ቤቶቹን በመገንባት የብድር ገንዘብም ተመልሷል፤ ተጠሪዎችን ጨምሮ ሌሎች ነዋሪዎች በራሳችን ገንዘብ ቤቶቹን አፍርሰን እንደሰራን በወቅቱ የነበሩ የአመልካች አመራሮች አረጋግጠው በሰነድ ማስረጃ ሰጥተውናል፤ ተጠሪዎች ከ1982/1983 ጀምሮ በሰነድ አልባ በመኖሪያ ቤቶቹን ገንብተን እየኖርን እያለን ከ20 ዓመታት በኋላ አመልካች ለተጠሪዎች ያሰበ በማስመሰል ከፊሎቹን የተጠሪዎች ቤቶች ለልማት ሊፈርሱ ስለሚችሉ የጋራ መኖሪያ ቤት መንግስት እንዲሰጣችሁ እና ቀበሌው እንዲያውቃችሁ በማለት ከሱ ጋር የቤት ኪራይ ውል እንድንዋዋል ሲጠይቀን ተጠሪዎችም የአመልካች ህብረት ሥራ ማህበር አባላት በመሆናቸን እና መንግስታዊ ተቋም ነው ብለን በማመን ከ2ኛ ተጠሪ በስተቀር ከአመልካች ጋር የቤት ኪራይ ውል ልንፈርም ችለናል፤ተጠሪዎች የይዞታ ማረጋገጫ ለመቀበል በሂደት ላይ እያለን አመልካች ከህግም ሆነ ከውል የመነጨ መብት ሳይኖረው እንዳይፈጸም አድርጓል፤ አመልካች ተጠሪዎችን በማታለል ባስፈረመን የኪራይ ውል መነሻነት ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኪራዩን ከፍለው ቤቱን ያስረክቡኝ በማለት ክስ አቅርቦ ተጠሪዎች ቤቱን እንድናስረክብ ተወስኗል፤ ሆኖም ከመነሻው ቦታው በጎርፍ ምክንያት ለህይወታችን እስጊ በመሆኑ ልዋጭ ቦታ እንዲሰጠን የሚመለከተውን አካል ጠይቀን ሲሰጠን በቦታው ላይ ቀበሌው ቤት መስራት ካልቻለ ነዋሪዎች በራሳችን ወጪ እንድንሰራ በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት በራሳችን ወጪ ቤት ገንብተን በስማችን ውሃ፣ መብራት እና መሰል መሰረታዊ አገልግሎቶችን አስገብተን የምንኖርበት ቤት በመሆኑ ቤቶቹ የተጠሪዎች ናቸው ተብሎ ይወሰንልን በማለት ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡መልካም ንባብ…. Previous Article አቶ ታዬ ከተማ ደጋጋ እናእነ አቶ ሙሉጌታ ታደሰ (3ሰዎች) የሰ/መ/ቁጥር---244417 Next Article እስጢፋኖስ /ዩቡና/ ዲራጎ እና የሲዳማ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሠ/መ/ቁጥር 251519 Print 4680 Documents to download 249104(.pdf, 865.58 KB) - 546 download(s)
የዳኝነትና የዴሞክራሲ ተቋማት እምርታ፤ ለሀገረ መንግስት... የዳኝነትና የዴሞክራሲ ተቋማት እምርታ፤ ለሀገረ መንግስት... Wednesday, March 4, 2026 895 የካቲት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ''የዳኝነትና የዴሞክራሲ ተቋማት እምርታ ለተሳካ ሀገረ መንግሥት ግንባታ" በሚል መሪ ቃል በዳኝነትና የዴሞክራሲ ተቋማት የለውጥ ስራዎች ላይ በማተኮር ሲካሄድ የቆየው የምክክር መድረክ ተጠናቋል። Read more
ከምርጫ ጉዳዮች ጋር በተያያዙ ቅሬታዎች እና አፈታት ላይ... ከምርጫ ጉዳዮች ጋር በተያያዙ ቅሬታዎች እና አፈታት ላይ... Friday, February 27, 2026 942 ከምርጫ ጉዳዮች ጋር በተያያዙ ቅሬታዎች እና አፈታት ላይ ለፌዴራል እና ለክልል ዳኞች ከቀን 09/06/2018 ዓ.ም ጀምሮ በ3 ዙር ለ9 ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና በቀን18/5/2018 ዓ.ም ተጠናቀቀ፡፡ Read more
በአለምአቀፍ ወንጀሎች ዙሪያ ለፌዴራል ጠቅላይ እና... በአለምአቀፍ ወንጀሎች ዙሪያ ለፌዴራል ጠቅላይ እና... Monday, February 23, 2026 1045 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከዳኒሽ ኢንቲትዩት ፎር ሁማን ራይትስ ጋር በመተባበር ከፌዴራል ጠቅላይ እና ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለተውጣጡ ዳኞች በአለምአቀፍ ወንጀሎች ዙሪያ በስድስት የስልጠና ርእሶች በተከታታይነት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና የማጠናቀቂያ መርሐግብር የካቲት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ተካሂዷል። Read more
አዲስ ለተቀጠሩ ህግ ጉዳይ ጸሐፊ I እና የህግ ጉዳይ... አዲስ ለተቀጠሩ ህግ ጉዳይ ጸሐፊ I እና የህግ ጉዳይ... Tuesday, February 17, 2026 1298 አዲስ ለተቀጠሩ ህግ ጉዳይ ጸሐፊ I እና የህግ ጉዳይ ጸሐፊ II በ ቀን 06 እና 09/06/2018 ዓ.ም የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታን እና ከለዉጥ ስራዎች ጋር ለማስተዋወቅ የመግቢያ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ Read more
10Mar2026 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Tuesday, March 10, 2026 Read more