Selam Warga / Tuesday, June 17, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation የፌደራል ዐቃቤ ህግ እና አቶ አበበ ወንድሙ ኤጋ የሰ/መ/ቁጥር 251759 አመልካች በስር ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ ባቀረበው ክስ ተጠሪ የወ/ህ/ቁ.539(1)(ሀ) ን ተላልፈው ሰው ለመግደል አስቀድሞ በነበረው ሀሳብ ጨካኝነቱንና ነውረኝነቱን በሚያሳይ ሁኔታ ወንድሙን ሟች ጀንበሩ ወንድሙን ከአሁን በፊት ሰድቦኛል እንዲሁም በሚያሽከረክረው መኪና ሊገጨኝ ሞክሯል በማለት በቂም በቀል በመነሳት ሽጉጥ ተኩሶ ማጅራቱን ሲመታው ሲወድቅ በተደጋጋሚ ሶስት ጊዜ ተኩሶ ግንባሩን በቀኝ በኩል አንገቱንና በግራ በኩል አንገቱን በመምታት የጥይት እርሳስ ጉዳት በራስ ቅሉ የኋለኛው ክፍል፤የክብ ቅርፅ ያለው ጥይት እርሳስ የገባበት ቁስል በራስ ቅሉ የኋለኛው ክፍል፤ሳተላይት ቅርጽ ያለው የጥይት እርሳስ የወጣበት ቁስል፤በግራ ግንባሩ የፊተኛው ክፍል ላይ የአጥንት መሰበር ጉዳት፤በራስ ቅሉ ፊተኛው የታችኛው ክፍል ላይ እንዲደርስበት፤የመበሳት ጉዳት በአንገቱ ላይ እንዲደርስበት ፤በአንጎሉ የላይኛው ሽፋን ክፍል የተሰራጨ የደም መፍሰስ እንዲሁም የአየር ባንቧው የመበለዝ ጉዳት እና በዙሪያው ከፍተኛ ደረጃ ያለው የውስጥ ደም መፍሰስ ጉዳት እንዲደርሰበት እና ህይወቱ እንዲያልፍ አድርጓ በዚህም ከባድ የሆነ የሰው ግድያ ወንጀል ፈፅሟል በማለት ከሷል፡፡መልካም ንባብ…. Previous Article ህብረት ኢንሹራንስ አ.ማ እና ኤም.ኢ.ኤስ.ፒ. አፍሪካ ኃ.የተ.የግ. ማህበር ፤የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጀት የሠ/መ/ቁጥር 251398 Next Article አቶ ኃይለ ጊዮርግስ ይልማ ወልደአብ እና እነ አቶ አዲስ እሸቱ (4) ሰዎች የሰ/መ/ቁ 252056 Print 4634 Documents to download 251759(.docx, 142.83 KB) - 578 download(s)
በአለምአቀፍ ወንጀሎች ዙሪያ ለፌዴራል ጠቅላይ እና... በአለምአቀፍ ወንጀሎች ዙሪያ ለፌዴራል ጠቅላይ እና... Monday, February 23, 2026 840 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከዳኒሽ ኢንቲትዩት ፎር ሁማን ራይትስ ጋር በመተባበር ከፌዴራል ጠቅላይ እና ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለተውጣጡ ዳኞች በአለምአቀፍ ወንጀሎች ዙሪያ በስድስት የስልጠና ርእሶች በተከታታይነት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና የማጠናቀቂያ መርሐግብር የካቲት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ተካሂዷል። Read more
አዲስ ለተቀጠሩ ህግ ጉዳይ ጸሐፊ I እና የህግ ጉዳይ... አዲስ ለተቀጠሩ ህግ ጉዳይ ጸሐፊ I እና የህግ ጉዳይ... Tuesday, February 17, 2026 897 አዲስ ለተቀጠሩ ህግ ጉዳይ ጸሐፊ I እና የህግ ጉዳይ ጸሐፊ II በ ቀን 06 እና 09/06/2018 ዓ.ም የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታን እና ከለዉጥ ስራዎች ጋር ለማስተዋወቅ የመግቢያ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ Read more
ሥነ-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥና የጥቅም ግጭት መከላከልና... ሥነ-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥና የጥቅም ግጭት መከላከልና... Monday, February 16, 2026 697 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፌዴራል ሥነ-ምግባርና ፀረ -ሙስናና ኮሚሽን ጋር በመተባበር በሥነ-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥ እና የጥቅም ግጭት መከላከልና ማስተዳደር ላይ ከፍርድ ቤት ዘርፍ ለተውጣጡ የስራ ሃላፊዎች የካቲት 5 እና 6 ቀን 2018 ዓ.ም ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ Read more
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የኢትዮጵያ... የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የኢትዮጵያ... Friday, February 13, 2026 776 የመግባቢያ ስምምነቱን የፈረሙት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት እና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ቢኒያም ኤሮ ናቸው፡፡ Read more
10Mar2026 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Tuesday, March 10, 2026 Read more