Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና አቶ መጣልኝ መላኩ የሰ.መ.ቁ.252953

የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ ከሳሽ (የአሁን ተጠሪ) በሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረበዉ የክስ አቤቱታ፡ ከሳሽ በ2005 ዓ.ም የ40/60 የመኖሪያ ቤት መርሃ ግብር ተመዝግቤ በአሁኑ ወቅቱ ባጠቃላይ 430000 ማለትም መቶ ፐርሰንት የቆጠብኩኝ በመሆኑ በዉሉና በመመሪያዉ መሰረት ቅድሚያ ዕጣ እንዲወጣልኝ መደረግ ሲገባዉ ከመመሪያዉ ዉጭ አርባ ፐርሰንት የቆጠቡ ሰዎች ተካተዉ እጣ እንዲወጣ በመደረጉ መብቴን አጣቧል፡፡ ከሳሽ ከ1ኛ ተከሳሽ ጋር ባደረግነዉ ዉል ቤቱን ሊያስገኝ የሚያስችል ዉል የተዋዋልንና ግዴታዬን የተወጣሁ ቢሆንም ሌሎች ተከሳሾችም በመመሪያ ቁጥር 21/2005 መሰረት የሚጠበቅባቸዉን አስተዳደራዊ ኃላፊነታቸዉን በመወጣት ቤቱን ሊያስረክቡኝ አልቻሉም፡፡ 1ኛ ተከሳሽ ከ3ኛ ተከሳሽ ጋር ባደረገዉ ሰነድ መሰረት ተገንብተዉ የተጠናቀቁትን ቤቶች ከቢሮዉ ተረክቦ በዉሉ መሰረት ቅድሚያ ማስረከብ ሲገባዉ ይህን ያላደረገ በመሆኑ፣ ሌሎች ተከሳሾችም ኃላፊነታቸዉን ያልተወጡ በመሆናቸዉ፣ በመመሪያዉና በዉሉ መሰረት ተገንብተዉ ከተጠናቀቁ ቤቶች ላይ ከአንዱ ሳይት እንዲወስድ ተከሳሾች በአንድነትና በነጠላ ኃላፊነት አለባቸዉ ተብሎ እንዲወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡መልካም ንባብ….

Previous Article አቶ ኃይለ ጊዮርግስ ይልማ ወልደአብ እና እነ አቶ አዲስ እሸቱ (4) ሰዎች የሰ/መ/ቁ 252056
Next Article ኤልያስ ዳሪ እና እነ ወ/ሮ ሰናይት አብርሃ (6) ሰዎች የሰ/መ/ቁ. 253783
Print
2616

Documents to download

  • 252953(.pdf, 861.73 KB) - 327 download(s)

«January 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
2930311234
567891011
12131415161718
19202122232425
2627282930311
2345678

በአገልግሎት አሰጣጥና የደንበኞች አያያዝ ላይ ሲሰጥ...

523

የፌደራል የህግና የፍትሕ ኢንስቲትዩት ለተከታታይ ሦስት ሳምንታት በሶስት ዙር ከፌዴራል ፍርድ ቤቶች፣ከፍትሕ ሚኒስቴር እንዲሁም ከፌዴራል የሕግና የፍትሕ ኢንስቲትዩት ለተውጣጡ 170 የአስተዳደር ሰራተኞች ከጥቅምት 21 ቀን እስከ ህዳር 6ቀን 2018 ዓ.ም በፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቋል፡፡

የተግባር ልምምድ (ስልጠና) በዲጂታል የዳኝነት አገልግሎት...

470

በዲጂታል የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ከቀን 06-07/03/2018 ዓ.ም ለሁለት ቀናት የሚቆይ የተግባር ልምምድ (ስልጠና) ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች እየተሰጠ ይገኛል።

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሪሶርስ ኢንሪቺንግ አፍሪካን...

372

ሪሶርስ ኢንሪቺንግ አፍሪካን ላይቭስ በመባል የሚጠራ ግብረ ሰናይ ድርጅት ቡክስ ፎር አፍሪካና ቶምሰን ሪዉተርስ ከሚባሉ ለጋሽ ድርጅቶች ለትምህርት ቤቶች እና ለፍትህ ተቋማት የሚያገለግሉ መጻሃፍቶችን በማሰባሰብ ወደ አገር ውስጥ እንዲገባ አድርጓል፡፡

በአስማሚነት ክህሎት ዙሪያ ሲሰጥ የነበረዉ የተግባር...

557

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ህፃናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት ከጥቅምት 24 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 27 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ 4 ቀናት በተግባር ሲሰጥ የነበረዉ የአስማሚነት ክህሎት ስልጠና ተጠናቋል፡፡

First2345791011Last