Selam Warga / Tuesday, June 17, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation ጨመሬ ቶሎሳ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰ/መ/ቁጥር 267231፣267230 የአሁን አመልካች በምዕራብ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ/መ/ቁ 47863 እና በመ/ቁ በመ/ቁ 47862 በሁለቱም መዝገቦች ላይ 2ኛ ተከሳሽ ሲሆን ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበው የክስ ይዘትም አመልካች የኢትዮጵያ የፌዴራል ቡና እና ሻይ ባለስልጣን ግምቢ ቅርንጫፍ የቡና ላኪ ሸኚ ስምሪት ጣቢያ ላይ ቋሚ ሰራተኛ ሆኖ በባለሙያነት ተቀጥሮ እየሰራ እያለ በቡና ንግድ ውስጥ የማጭበርበር ድርጊት በመፈጸም ለራሱ የማይገባውን ጥቅም ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ በምዕራብ ወለጋ ዞን ግምቢ ከተማ ቀበሌ 05 በኢትዮጵያ ምርት ገበያ ግምቢ ቅርንጫፍ ግቢ ውስጥ ጥቅምት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ለማዕከላዊ ገበያ የሚቀርብ የተቀሸረ ቡና ዓይነቱ እና የሰሌዳ ቁጥሩ 3-A02958 A.A በሆነ ኤፍ.ኤስ፣አር መኪና ከነጆ ከተማ ተጭኖ በፕሎምፕ ታሽጎ የቡናው ፕሎምፕ ቁጥር GM-7 በሚባል የታሸገውን በሚልክበት ጊዜ የቡናውን መጠን አጣርቶ መላክ እያለበት የተቀሸረ 129 ኩንታል ተጭኖ እያለ 100 ኩንታል በሚል እንዲሁም ከአይራ ወረዳ በሲኖ ትራክ 210 ኩንታል ቡና የተጫነ ነዉ ተብሎ የተላከዉን ተቀብሎ በቡናው የይለፍ ወረቀት ላይ ይህንኑ መጠን በማረጋገጥ የይለፍ ወረቀት ከሰጠ በኋላ በዚሁ ቀን የተጠቀሱት መኪናዎች በጊምቢ ከተማ ልዩ ስሙ ሰርጤ ኬላ ቦታ ላይ በቁጥጥር ስር ውለዉ ሲፈተሹ 29 እና 70 ኩንታል ቡና እንደቅደም ተከተላቸዉ ከህግ ውጭ ጥራት በሌለው የማዳበሪያ ከረጢት ተጨምሮ እሱ በይለፍ ወረቀት ላይ ጽፎ ከሰጠው በላይ በተጨማሪ ተጭኖ ስለተገኘ የአዋጅ 1051/2009 አንቀጽ 19/5/ የሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 433/2007 አንቀጽ 41(1)(ቀ) በመተላለፍ የማይገባ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት አስቦ በቡና ንግድ ውስጥ የማጭበርበር ወንጀል ድርጊት ፈጽሟል የሚል ነው፡፡ መልካም ምንባብ… Previous Article አቶ መሀመድ አለሙ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰበር መዝገብ ቁጥር 266395 Next Article ወ/ሮ የማርውሃ ወርቅነህ እና እነ ወ/ሮ ዓለም ወርቅነህ የሰ.መ.ቁ 242314 Print 6331 Documents to download 267231(.pdf, 1.08 MB) - 1345 download(s)
በአለምአቀፍ ወንጀሎች ዙሪያ ለፌዴራል ጠቅላይ እና... በአለምአቀፍ ወንጀሎች ዙሪያ ለፌዴራል ጠቅላይ እና... Monday, February 23, 2026 895 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከዳኒሽ ኢንቲትዩት ፎር ሁማን ራይትስ ጋር በመተባበር ከፌዴራል ጠቅላይ እና ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለተውጣጡ ዳኞች በአለምአቀፍ ወንጀሎች ዙሪያ በስድስት የስልጠና ርእሶች በተከታታይነት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና የማጠናቀቂያ መርሐግብር የካቲት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ተካሂዷል። Read more
አዲስ ለተቀጠሩ ህግ ጉዳይ ጸሐፊ I እና የህግ ጉዳይ... አዲስ ለተቀጠሩ ህግ ጉዳይ ጸሐፊ I እና የህግ ጉዳይ... Tuesday, February 17, 2026 1016 አዲስ ለተቀጠሩ ህግ ጉዳይ ጸሐፊ I እና የህግ ጉዳይ ጸሐፊ II በ ቀን 06 እና 09/06/2018 ዓ.ም የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታን እና ከለዉጥ ስራዎች ጋር ለማስተዋወቅ የመግቢያ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ Read more
ሥነ-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥና የጥቅም ግጭት መከላከልና... ሥነ-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥና የጥቅም ግጭት መከላከልና... Monday, February 16, 2026 835 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፌዴራል ሥነ-ምግባርና ፀረ -ሙስናና ኮሚሽን ጋር በመተባበር በሥነ-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥ እና የጥቅም ግጭት መከላከልና ማስተዳደር ላይ ከፍርድ ቤት ዘርፍ ለተውጣጡ የስራ ሃላፊዎች የካቲት 5 እና 6 ቀን 2018 ዓ.ም ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ Read more
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የኢትዮጵያ... የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የኢትዮጵያ... Friday, February 13, 2026 869 የመግባቢያ ስምምነቱን የፈረሙት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት እና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ቢኒያም ኤሮ ናቸው፡፡ Read more
10Mar2026 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Tuesday, March 10, 2026 Read more