Selam Warga / Monday, April 27, 2026 / Categories: CASSATION, Cassation ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጠ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔ: መዝገብ ቁጥር 271726 ከዚህ በፊት በሰ/መ/ቁጥር 249795 ላይ “ሠራተኛዉ በተከታታይ ከ5 ቀናት በላይ ለሆነ ጊዜ ከሥራ ቢቀር እንኳ ከሥራ ለቀረበት ለእያንዳንዱ ቀን አሠሪዉ ማስጠንቀቂያ (Warning in Writing) ሳይሰጥ የሥራ ዉልን ለማቋረጥ እንደማይችል” ተገልጾ የተሰጠው የህግ ትርጉም ተለውጦ “የአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 27(1)(ለ) ድንጋጌ ሠራተኛዉ በዚሁ አዋጅ ከተመለከቱ እረፍቶችና ልዩ ልዩ ፈቃዶች ዉጭ ለአምስት ተከታታይ የሥራ ቀናትና ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ ከሥራ ላይ ከቀረ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ (Warning in Writing) መስጠት ሳያስፈልግ የሥራ ዉልን ያለ ማስጠንቀቂያ ማቋረጥ ይቻላል” በሚል ተተርጉሟል፡፡ Previous Article ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጠ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔ: መዝገብ ቁጥር 244308 Print 2033 Documents to download 271726(.pdf, 281.52 KB) - 409 download(s)
የዳኝነትና የዴሞክራሲ ተቋማት እምርታ፤ ለሀገረ መንግስት... የዳኝነትና የዴሞክራሲ ተቋማት እምርታ፤ ለሀገረ መንግስት... Wednesday, March 4, 2026 895 የካቲት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ''የዳኝነትና የዴሞክራሲ ተቋማት እምርታ ለተሳካ ሀገረ መንግሥት ግንባታ" በሚል መሪ ቃል በዳኝነትና የዴሞክራሲ ተቋማት የለውጥ ስራዎች ላይ በማተኮር ሲካሄድ የቆየው የምክክር መድረክ ተጠናቋል። Read more
ከምርጫ ጉዳዮች ጋር በተያያዙ ቅሬታዎች እና አፈታት ላይ... ከምርጫ ጉዳዮች ጋር በተያያዙ ቅሬታዎች እና አፈታት ላይ... Friday, February 27, 2026 942 ከምርጫ ጉዳዮች ጋር በተያያዙ ቅሬታዎች እና አፈታት ላይ ለፌዴራል እና ለክልል ዳኞች ከቀን 09/06/2018 ዓ.ም ጀምሮ በ3 ዙር ለ9 ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና በቀን18/5/2018 ዓ.ም ተጠናቀቀ፡፡ Read more
በአለምአቀፍ ወንጀሎች ዙሪያ ለፌዴራል ጠቅላይ እና... በአለምአቀፍ ወንጀሎች ዙሪያ ለፌዴራል ጠቅላይ እና... Monday, February 23, 2026 1045 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከዳኒሽ ኢንቲትዩት ፎር ሁማን ራይትስ ጋር በመተባበር ከፌዴራል ጠቅላይ እና ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለተውጣጡ ዳኞች በአለምአቀፍ ወንጀሎች ዙሪያ በስድስት የስልጠና ርእሶች በተከታታይነት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና የማጠናቀቂያ መርሐግብር የካቲት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ተካሂዷል። Read more
አዲስ ለተቀጠሩ ህግ ጉዳይ ጸሐፊ I እና የህግ ጉዳይ... አዲስ ለተቀጠሩ ህግ ጉዳይ ጸሐፊ I እና የህግ ጉዳይ... Tuesday, February 17, 2026 1298 አዲስ ለተቀጠሩ ህግ ጉዳይ ጸሐፊ I እና የህግ ጉዳይ ጸሐፊ II በ ቀን 06 እና 09/06/2018 ዓ.ም የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታን እና ከለዉጥ ስራዎች ጋር ለማስተዋወቅ የመግቢያ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ Read more
10Mar2026 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Tuesday, March 10, 2026 Read more