Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

ሲሲኢሲሲ ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ እና አቶ ቤልሻጽር ሀይለልዑል መ/ጽድቅ የሰ.መ.ቁ.250942

ይህ የስራ ስንብት ክርክር የተጀመረዉ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁን አመልካች የሥር ከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪ የሥር ተከሳሽ ሆኖ ሲከራከሩ ነበር፡፡ ጉዳዩ ለዚህ ሰበር ችሎት ሊቀርብ የቻለዉ አመልካች የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.296508 በ29/10/2015 ዓ.ም የሰጠዉ ፍርድ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲታረምልን በማለት በማመልከቱ ነዉ፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ የአሁን አመልካች በሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረበዉ የክስ አቤቱታ፡ አመልካች በተጠሪ ድርጅት በብሮ ስራ መሃንዲስ የሥራ መደብ ተቀጥሬ በወር 80,000 (ሰማንያ ሺህ) እየተከፈለኝ በአርሲ ሮቤ ዋቤ ሪቨር ፕሮጀክት ሲሰራ የቆየሁ ሲሆን ተጠሪ በ02/12/2014 ዓ.ም በሕገወጥ መንገድ ከሥራዬ ስላሰናበተኝ ተገቢ ክፍያዎችን እንዲከፍለኝ እንዲወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡መለካም ንባብ….

Previous Article እነ አቢብ አብዲ (3) ሰዎች እነ ዓሊ ዮሜ ዩሱፍ የሰ/መ/ቁጥር---250757
Next Article ህብረት ኢንሹራንስ አ.ማ እና ኤም.ኢ.ኤስ.ፒ. አፍሪካ ኃ.የተ.የግ. ማህበር ፤የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጀት የሠ/መ/ቁጥር 251398
Print
6334

Documents to download

  • 250942(.pdf, 865.73 KB) - 847 download(s)

«September 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
31123456
78910111213
14151617181920
21222324252627
2829301234
567891011

በፌደራል ፍ/ቤቶች የአምስት ዓመት ስትራትጅክ ዕቅድ ላይ...

3344

በፌደራል ፍርድ ቤቶች ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ዓመታት ተግባራዊ እየተደረገ በሚገኘው ስትራቴጅክ ዕቅድ ላይ ከተቀመጡ ስድስት ቁልፍ የውጤት መስኮች አንዱ ተቋማዊ ለውጥ ማምጣት መሆኑንና በዚህ ውስጥ የሴቶችን ተሳትፎ ማሳደግ እንደግብ ተይዞ በዚህ ዙሪያ የተለያዩ ተግባራት በመከናወን ላይ መሆናቸውን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደት ክብርት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ ገለጹ፡፡

ፍርድ ቤቱ ከጾታዊ ጥቃት ነጻ የሆነ ማህበረሰብ የመገንባት...

3430

ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከጾታዊ ጥቃት ነጻ የሆነ ማህበረሰብ የመገንባት ዓላማ ያለው መሆኑን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ሰለሞን አረዳ ገለጹ፡፡

«ጾታን መሰረት አድርገዉ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ከመከላከል አንጻር የአመራሮች ሚና» በሚል ርዕስ ለፌደራል ፍርድ ቤቶች አመራሮችና ሰብሳቢ ዳኞች በቢሾፍቱ ከተማ አዱላላ ሪዞርትና ስፓ ታሕሳስ 25 ቀን 2015 ዓ.ም የተዘጋጀ የስልጠና መርሐ-ግብር ተሒዷል፡፡

ለፍርድ ቤቱ የአስተዳደር ሠራተኞች በንቃተ-ሕግ እንዲሁም...

2967

ከፌደራል ፍርድ ቤቶች ለተውጣጡ ሬጅስትራሮችና የአስተዳደር ሠራተኞች በንቃተ ሕግና የሴቶች ሰብዓዊ መብቶች በዓለም አቀፍና በኢትየጵያ ሕግ ላይ እንዲሁም ጾታን መሠረት ካደረገ ጉዳት ጋር በተያያዘ በሥነልቦናዊና ማሕበራዊ ድጋፎችና መርሆዎች ላይ ያተኮረ ሥልጠና ተሰጠ፡፡

ኢትዮጵያ ያፀደቀቻቸው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች...

3613

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መቋቋሙን ተከትሎ የሰብዓዊ መብቶችን በሀገራት ለማስረጽና የሕግ ማዕቀፍ ለማበጀት የተለያዩ ሰብዓዊ መብት ስምምነቶችን በማርቀቅ በአባል አገራቱ እንዲጸድቅ ማድረጉንና ኢትዮጵያ ያፀደቀቻቸው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ስምምነቶች በአገራችን ላይ ስምምነቶቹን የማክበር፣ የማስከበር እና ሰብአዊ መብቶችን የማሟላት ግዴታ እንደሚጥሉባት ተጠቆመ፡፡

First6768697072747576Last