Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ መሀመድ አለሙ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰበር መዝገብ ቁጥር 266395

ጉዳዩ የቀረበው የኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች 1ኛ ተከሳሽ አሁን የክርክሩ አካል ያልሆነው የትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ 2ኛ ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበው 1ኛ ክስ የወ/ህግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)፣ 34(1) እና 693(1) በመተላለፍ በትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ ውስጥ የፋብሪካው ኃላፊ እና ባለንብረት ሆኖ በሚሰሩበት ጊዜ ለግል ተበዳይ አቶ ሸምሱ አወል የብር አምስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የሚመነዘር ቼክ ሰጥቶ የግል ተበዳይ ገንዘቡን ለማውጣት ወደ ባንክ ሲሄድ በቂ ገንዘብ የለውም በመባሉ ገንዘቡን ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ስለዚህ በቂ ስንቅ ሳይኖር ቼክ በመስጠት ወንጀል ተከሷል የሚል ነው፡፡ አመልካች የወንጀሉን ድርጊት አልፈፀምኩም ብሎ ክዶ በመከራከሩ ተጠሪ የሰውና የሰነድ ማስረጃ አቅርቦ እንደ ክስ አቀራረቡ አስረድቷል፡፡ አመልካች እንዲከላከል ታዞ መከላከያ ማስረጃ ያቀረበ ሲሆን የአመልካች መከላከያ ምስክሮች ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቼክ መጥፋቱን አስረድተዋል፡፡መልካም ንባብ…. 

Previous Article ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594
Next Article ጨመሬ ቶሎሳ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰ/መ/ቁጥር 267231፣267230
Print
6759

Documents to download

  • 266395(.pdf, 849.74 KB) - 909 download(s)

«June 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
25262728293031
1234567
891011121314
15161718192021
22232425262728
293012345

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ሆነ የዳኞች አስተዳደር...

3059

የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ በአዋጅ ቁጥር 1233/2013 በተሰጠው ስልጣን መሰረት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር መመሪያን ለመተግበር ያስችለው ዘንድ የተከማቹ መዛግብትን በቅድሚያ ማጥራት አስፈላጊ መሆኑን ገልጾ ጊዜያዊ ዳኞች እንዲመደቡለት ያቀረበውን ጥያቄ አቅርቧል፡፡

ይህንን ተከትሎ ጉባዔው በፌዴራል ዳኝት አስተዳደር አዋጅ  ቁጥር 1233/2013 አንቀጽ 26 (2) ከአንድ ፍርድ ቤት ወደ ሌላ የፍርድ ቤት ደረጃ በጊዜያዊነት ዳኞችን መድቦ የማሰራት ስልጣኑን ተጠቅሞ የጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ሸክምን ይወጣሉ ያላቸውን አራት የከፍተኛ ፍርድ  ቤት ዳኞች ከሰኔ 2014 ዓ.ም እስከ ህዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ብቻ የመዝገብ ክምችት እንዲያጠሩ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ 

በሃገራችን የሰብዓዊ መብትን ለመጠበቅም ሆነ ለማስከበር...

3071

 “ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች አተገባበር በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች” በሚል ርዕስ  ለፌዴራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች እና የህግ ባለሙያዎች የአንድ ቀን ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

የስልጠናው ዋና ዓላማ የህዝብ ጥቅም የሚነኩ ክርክሮች ጽንሰ ሃሳባዊ ማዕቀፎችን፣ በኢትዮጵያ ሃገራዊ የዳኝነት ስልጣን ወሰን የሰብዓዊ መብቶችን የተመለከቱ ክርክሮችን ለመዳኘት የሚያግዙ በስራ ላይ ያሉ የህግ ማዕቀፎች እንዲሁም መሰረታዊ መብቶችንና ነጻነቶችን ለመተግበር የሚረዱ የህግ ማዕቀፎችን በስልጠናው ለተሳተፉ ዳኞችና ህግ ባለሙያዎች ማስገንዘብ እና የጋራ መረዳት መፍጠር ነው፡፡

የፍርድ ቤቱን የአስተዳር ሰራተኞች አገልግሎት አሰጣጥ...

2525

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ሰለሞን አረዳ የፍርድ ቤት የአስተዳር ሰራተኞችን አገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት የሚያጎለብቱ ስልጠናዎችን የመስጠት ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገለጹ፡፡

ክቡር አቶ ሰለሞን አረዳ ይህን የገለጹት ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአስተዳደር ዘርፍ የጽ/ቤት ሃላፊዎች፣ ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች በተዘጋጀ ስልጠና ማጠቃለያ ላይ በሰጡት የስራ መመሪያ ነው፡፡

በአስተዳደር ዘርፍ የፍርድ ቤቱን አገልግሎት አሰጣጥ...

2776

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአስተዳደር ዘርፍ የአገልግሎት አሰጣጥን የሚያቀላጥፍ የአቅም ግንባታ ስልጠና 630 ለሚጠጉ የፍርድ ቤቱ የአስተዳደር ሰራተኞች ከግንቦት 04 ቀን 2014 እስከ ግንቦት 21 ቀን 2014 ዓ/ም ቢሾፍቱ በሚገኘዉ የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲቲዩት በአራት ዙር ሰጥቷል፡፡

First6768697072747576Last