ሰባት ዳኞች በተሰየሙበት የሰበር ችሎት...

በሐይማኖት ተቋማት ውስጥ አስተዳደራዊ ተግባርን ለማከናወን በተሰማሩ ሰራተኞች የሚነሱ  የስራ ክርክሮችን በተመለከተ ፍርድ ቤቶች የስራ ክርክሩን ተቀብለው አከራክረው ለመወሰን ህጋዊ የዳኝነት ስልጣን ያላቸው ስለመሆኑ ትርጉም... Read more

ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት...

ከ2002 ዓ.ም እስከ 2017 ዓ.ም በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጡ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔዎችን ያጠቃለለ መጽሐፍ በልዮ ዕትም ለንባብ ምቹ ሆኖ ቀርቧል። Read more

ወ/ሮ የማርውሃ ወርቅነህ እና እነ ወ/ሮ...

የጉዳዩ አመጣጥ ባጭሩ ሲታይ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪዎች ከሳሽ አመልካች ደግሞ ጣልቃ ገብ ሆነው ተከራክረዋል፡፡ ተጠሪዎች በቀን 11/09/2013 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት አቤቱታ የእናታቸው ወ/ሮ ሸዋነሽ ስመኝ... Read more

ጨመሬ ቶሎሳ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ...

የአሁን አመልካች በምዕራብ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ/መ/ቁ 47863 እና በመ/ቁ በመ/ቁ 47862 በሁለቱም መዝገቦች ላይ 2ኛ ተከሳሽ ሲሆን ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበው የክስ ይዘትም አመልካች የኢትዮጵያ የፌዴራል ቡና... Read more
12345678910Last
«February 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
2627282930311
2345678
9101112131415
16171819202122
2324252627281
2345678

ፍርድ ቤቱ በስትራቴጂያዊ እና ዓመታዊ ዕቅዱ ላይ ለምክር...

2336

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ ፍትህና የዲሞክራሲ ጉዳዩች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ፍርድ ቤቱ ባዘጋጀው ሶስተኛው ስትራቴጂያዊ ዕቅድ እና ዓመታዊ ዕቅድ ላይ ማብራሪያ ሰጠ፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ በፍርድ ቤቱ በኩል ዕቅዶቹን አስመልክቶ ሰፊ ማብራሪያ ከመቅረቡ በፊት በሰጡት አጭር ገለጻ የዳኝነት ዘርፉ በአማካሪ ድርጅት በመታገዝ ስትራቴጂያዊ ዕቅዱን ማዘጋጀቱን፤ የዕቅዱን ይዘትና አዘገጃጀት ሂደት የሚከታተል በየደረጃ ያሉ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አመራሮች፣ የስራ ክፍል ኃላፊዎችና ባለሙያዎች አባል የሆኑባቸው ዓቢይና ቴክኒክ ኮሚቴ መቋቋማቸውን፤ በረቂቅ ዕቅዱ ላይ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማህበረሰብ እና ባለድርሻ አካላት መወያየታቸውን እና የተገኙ ተጨማሪ ግብዓቶችን በማካተት ተዘጋጅቶ የጸደቀ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የሙስና ወንጀልን በትብብርና በአንድነት መንፈስ መከላከል...

2104

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የፕሬዚደንት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቦጃ ታደሰ የሙስና ወንጀልን በትብብርና በአንድነት መንፈስ መከላከል እንደሚገባ ገለጹ፡፡

አቶ ቦጃ ታደሰ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በዓል አከባበርን አስመልክቶ በተዘጋጀ የገንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መድረክ ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ሙስና ሕዝብ በመንግሥት እና በሕግ የበላይነት ላይ አመኔታ እንዲያጣ የማድረግ ጉልበት ያለው መሆኑን በመጥቀስ፣ ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ልማትን በእጅጉ በማዳከምና በመጉዳት የሞራልና የሥነምግባር ቀውስ እንዲፈጠር የሚያደርገውን የሙስና ወንጀል በትብብርና በአንድነት መንፈስ መከላከል እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የሴቶችና...

1742

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሴቶችና ሕጻናት ዙሪያ የሚኖርን የፍትሕ ተገማችነትን ለማስፋት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ሥርዓተ-ችሎት እንዲዘጋጅ እያደረገ እንደሚገኝ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዚደንት ክቡር አቶ ሰለሞን አረዳ አስታወቁ፡፡

ም/ፕሬዚደንቱ ይህን ያስታወቁት የፌደራል ፍ/ቤቶች ዓለም ዓቀፍ ፀረ-ጾታዊ ጥቃት ቀንን ሕዳር 30 ቀን 2014 ዓ.ም በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት አዳራሽ በፓናል ውይይት ሲከበር ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ነው፡፡

የክብርት ፕሬዝደንቷ ጉብኝት በድሬደዋ ምድብ ችሎቶች

2652

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ የፌዴራል ከፍተኛ እና መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ድሬደዋ ምድብ ችሎቶችን ጎብኝተዋል::

ክብርት ፕሬዝደንቷ በጉብኝታቸው ከሁለቱም ፍርድ ቤቶች ምድብ ችሎቶች የዳኝነት አገልግሎት የሚሰጥበትን ሁኔታ እና የምድብ ችሎቶቹን የችሎት እና የልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎችን አደረጃጀት ተመልክተዋል፡፡ ከፍርድ ቤቶቹ ክቡራን ዳኞች እና የአስተዳደር ሰራተኞች ጋርም ወይይት አካሄደዋል::

First6768697072747576Last