Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ ኩማ መልኩ እና አቶ ሰለሞን ዘለቀ የሰበር መ/ቁ/250546

መዝገቡ ለሰበር ችሎት የቀረበዉ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ የህግ ስህተት የለዉም በማለት በመ/ቁ/ 423754 ላይ በቀን 11/09/2015ዓ.ም የሰጠዉ ትእዛዝ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል በዚህ ሰበር ችሎት እንዲታረም በማለት አመልካች ባቀረቡት አቤቱታ መነሻ ነዉ፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ ባጭሩ ሲታይ በስር ፍርድ ቤት አመልካቹ ከሳሽ ሲሆን ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን የተከራከሩ ሲሆን ጉዳዩ እርሻ መሬት ይዞታ የሚመለከት ነዉ፡፡አመልካች ሃምሌ 12 ቀን 2014ዓ.ም በዲጋሉና ጢጆ ወረዳ ፍርድ ቤት ባቀረበው አቤቱታ በዲጋሉ አራቢ ቀበሌ ውስጥ የሚገኘውን አዋሳኞቹ በክሱ የተጠቀሰ መሬት ከአያቴ ከበደ ዋቅጅራ እና ሴት አያቴ ወ/ሮ የሺ ተ/ማሪያም በመ/ቁ/43575 በሆነው በዉርስ ተወስኖልኝ በመ/ቁ 43575 ተፈጽሞልኝ እያለ ተጠሪ ምንም መብት ሳይኖረዉ ስለያዘብኝ እንዲለቅልኝ ሲል የጠየቀ ሲሆን ተጠሪ ጥቅምት 2 ቀን 2015 ዓ.ም ባቀረበው መልስ ይዞታው የአመልካች አያቶች ሳይሆን በቅይይር ከአቶ ታደሰ ከበደ ያገኘሁት የግል ይዞታዬ ነው፤የተቀያየርነውን ይዞታ ሰዎች ተቀብለው የመኖሪያ ቤት የሰሩበት ሲሆን እኔም ይዞታውን እየተጠቀምኩበት ስለሆነ ክሱ ተቀባይነት የለዉም በማለት ተከራክሯል፡፡መልካም ንባብ…..

Previous Article እነ ወ/ሮ ጌጤ ሙለታ(3ሰዎች) እና ወ/ሮ ብርሃኔ ካባ የሰ/መ/ቁ 249367
Next Article እነ ወ/ሮ ዘውዲቱ ድንቁ(2ሰዎች)የቀድሞ አርጋፋ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት (በአሁን አርጋፋ ማዘጋጃ ቤት)የሰ/መ/ቁ፡- 250597
Print
6603

Documents to download

  • 250546(.pdf, 1.07 MB) - 660 download(s)

«September 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
31123456
78910111213
14151617181920
21222324252627
2829301234
567891011

ጾታን መሠረት ባደረጉ የኃይል ጥቃቶች 90 በመቶ ያህል...

3588

በአገራችን ጾታን መሠረት አድርገው ከሚፈጸሙ የኃይል ጥቃቶች መካከል 90 በመቶ ያህል ጥቃት ፈጻሚዎች ለፍትሕ ተቋማት ቀርበው ሕጋዊ ቅጣት እንደማያገኙ ተመለከተ፡፡

ጾታን መሰረት ያደረጉ የኃይል ጥቃቶች የወንጀል ምርመራ ቴክኒኮች፣ ፕሮቶኮል እንዲሁም አሠራሮችን በሚመለከት ለፌደራል ዳኞች እና ሌሎች የዳኝነት አካላት ሕዳር 17 እና 18 ቀን በአዳማ ከረዩ ሪዞርት ሆቴል ሲሰጥ የቆየው ሥልጠና ተጠናቀቀ፡፡

ሪፖርተር ጋዜጣ ከፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚደንት...

3756

Meaza Ashenafi, who is best recognized for her work to empower women, was elected as the Federal Supreme Court’s first female president. She has held this role ever since, leading numerous initiatives to modernize the justice system. It wasn’t an easy task, especially in a nation where the separation between the three branches of government—the Executive, the Legislature, and the Judiciary—is blurred.

የፌደራል ፍርድ ቤቶች ፕሬዚደንቶች፣ አመራሮችና ዳኞች...

3287

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ሰለሞን አረዳ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የክርክር ፍርድ ቤት የግማሽ ጊዜ ዳኛ ሆነው መሾማቸውን ምክንያት በማድረግ የፌደራል ፍርድ ቤቶች ፕሬዚደንቶች፣ ዳኞችና የሥራ ኃላፊዎች ሕዳር 13 ቀን 2015 ዓ.ም በፍርድ ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ የእንኳን ደስ አለዎት መርሐ-ግብር አካሔዱ፡፡

በፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ እና...

3322

የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2015 በጀት ዓመት ዕቅዳቸውን እና የበጀት ዓመቱን የመጀመሪያ ሶስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም የተመለከተ ማብራሪያ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ፣ ፍትሕና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም ማብራሪያ አቀረቡ፡፡

First6869707173757677Last