ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት...

ከዚህ በፊት በሰ/መ/ቁጥር 249795 ላይ “ሠራተኛዉ በተከታታይ ከ5 ቀናት በላይ ለሆነ ጊዜ ከሥራ ቢቀር እንኳ ከሥራ ለቀረበት ለእያንዳንዱ ቀን አሠሪዉ ማስጠንቀቂያ (Warning in Writing) ሳይሰጥ የሥራ ዉልን... Read more

ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት...

ጉዳዩ በከተማ ክልል የሚገኝ መሬት ይዞታ መብት ለማስከበር የቀረበ ክስ የሚመለከት ነው፡፡ የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን... Read more

ሰባት ዳኞች በተሰየሙበት የሰበር ችሎት...

በሐይማኖት ተቋማት ውስጥ አስተዳደራዊ ተግባርን ለማከናወን በተሰማሩ ሰራተኞች የሚነሱ  የስራ ክርክሮችን በተመለከተ ፍርድ ቤቶች የስራ ክርክሩን ተቀብለው አከራክረው ለመወሰን ህጋዊ የዳኝነት ስልጣን ያላቸው ስለመሆኑ ትርጉም... Read more

ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት...

ከ2002 ዓ.ም እስከ 2017 ዓ.ም በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጡ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔዎችን ያጠቃለለ መጽሐፍ በልዮ ዕትም ለንባብ ምቹ ሆኖ ቀርቧል። Read more
1345678910Last
«June 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
25262728293031
1234567
891011121314
15161718192021
22232425262728
293012345

ፍርድ ቤቱ የዩኒቨርሲቲ የሕግ ተማሪዎችን አቅም ለማጎልበት...

2463

የፌደራል ፍርድ ቤቶች በከፍተኛ የትምሕርት ተቋማት ከሚገኙ የሕግ ትምሕርት ቤቶች ጋር በመቀናጀት የሕግ ተማሪዎች በፍርድ ቤቶች የሜንተርሽፕ እና የኢንተርንሽፕ ፕሮግራም እንዲሳተፉ በማድረግ የሚያከናውኑት ተግባር ትውልድን የማነጽ ሥራ መሆኑን የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዚደንት እና የፌደራል ፍርድ ቤቶች ቃል አቀባይ ክቡር አቶ ተስፋዬ ንዋይ ገለጹ፡፡

ፍርድ ቤቱ የዲጂታል የሀብት ማስመዝገብ መርሐ-ግብር አስጀመረ

3104

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የዲጂታል የሀብት ምዝገባና ማሳወቅ መርሐ-ግብር በፌደራል ፍርድ ቤቶች መጀመሩን መጋቢት 8 ቀን 2014 ዓ/ም በፍርድ ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ በተካሔደ ሥነሥርዓት ይፋ አደረጉ፡፡

በፌደራል ፍርድ ቤቶች የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ተግባራዊ የሚደረገውን የዲጂታል የሀብት ምዝገባና ማሳወቅ መርሐ-ግብር የተጀመረው ፍርድ ቤቱ እና የፌደራል የሥነምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በጋራ ባዘጋጁት ሥነሥርዓት ላይ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ሀብታቸውን እንዲያስመዘግቡ በተከናወነ ሥነሥርዓት ነው፡፡

የፍ/ቤቱ ዳኞች በጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር እና በመዛግብት...

ፍርድ ቤቱ 20 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ከመንግስት ማግኘቱም ተጠቁሟል

3927

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች በ2014 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የፍትሐብሔር ጉዳዮች ፍሰት አስተዳደርን ተግባራዊ በማድረግ እና በመዛግብት አፈጻጸም ያስመዘገቡት ውጤት አበረታች በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባው የፍርድ ቤቱ ፕሬዚደንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ገለጹ፡፡

ክብርት ፕሬዚደንትዋ ይህን የገለጹት የፍርድ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ ዳኞች እና ረዳት ዳኞች በተሳተፉበትና በፌደራል ፍ/ቤቶች የአምስት ዓመታት (2014-2018 ዓ.ም) ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ዋና ዋና ይዘት እና በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የችሎቶችና ዳኞች የ2014 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የመዛግብት አፈጻጸም ላይ መጋቢት 3 ቀን 2014 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል የተደረገውን ውይይት ሲያጠቃልሉ ባደረጉት ንግግር ነው፡፡

የፌደራል ፍርድ ቤቶች ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በፓናል...

2704

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ111ኛ ጊዜ፣ በአገራችን ደግሞ ለ46ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች 8) የፌደራል ፍርድ ቤቶች የካቲት 29 ቀን 2014 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል በፓናል ውይይት አከበሩ፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የፓናል ውይይቱን በንግግር ሲከፍቱ ባደረጉት ንግግር የሴቶች የሲቪልም ሆነ የፖለቲካ መብት እና ተሳትፎ ከኢኮኖሚ መብት ጋር ተያያዥ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ለዚህም ማሳያው የግል ገቢ የሌላት ሴት ከሚበድላት ባል ጋር ለመኖር እንደምትገደድና አማራጭ የሥራ ዕድል የሌላት ሴትም የመጥፎ አለቃን እብሪትና ትንኮሳ ችላ ለመኖር የምትገደድ መሆንዋ ትስስሩን እንደሚያሳይ አስረድተዋል፡፡

First6970717274767778Last