Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

ሲሲኢሲሲ ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ እና አቶ ቤልሻጽር ሀይለልዑል መ/ጽድቅ የሰ.መ.ቁ.250942

ይህ የስራ ስንብት ክርክር የተጀመረዉ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁን አመልካች የሥር ከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪ የሥር ተከሳሽ ሆኖ ሲከራከሩ ነበር፡፡ ጉዳዩ ለዚህ ሰበር ችሎት ሊቀርብ የቻለዉ አመልካች የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.296508 በ29/10/2015 ዓ.ም የሰጠዉ ፍርድ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲታረምልን በማለት በማመልከቱ ነዉ፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ የአሁን አመልካች በሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረበዉ የክስ አቤቱታ፡ አመልካች በተጠሪ ድርጅት በብሮ ስራ መሃንዲስ የሥራ መደብ ተቀጥሬ በወር 80,000 (ሰማንያ ሺህ) እየተከፈለኝ በአርሲ ሮቤ ዋቤ ሪቨር ፕሮጀክት ሲሰራ የቆየሁ ሲሆን ተጠሪ በ02/12/2014 ዓ.ም በሕገወጥ መንገድ ከሥራዬ ስላሰናበተኝ ተገቢ ክፍያዎችን እንዲከፍለኝ እንዲወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡መለካም ንባብ….

Previous Article እነ አቢብ አብዲ (3) ሰዎች እነ ዓሊ ዮሜ ዩሱፍ የሰ/መ/ቁጥር---250757
Next Article ህብረት ኢንሹራንስ አ.ማ እና ኤም.ኢ.ኤስ.ፒ. አፍሪካ ኃ.የተ.የግ. ማህበር ፤የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጀት የሠ/መ/ቁጥር 251398
Print
5983

Documents to download

  • 250942(.pdf, 865.73 KB) - 810 download(s)

«August 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
272829303112
3456789
10111213141516
17181920212223
24252627282930
31123456

የፍርድ ቤቱን የአስተዳር ሰራተኞች አገልግሎት አሰጣጥ...

3128

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ሰለሞን አረዳ የፍርድ ቤት የአስተዳር ሰራተኞችን አገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት የሚያጎለብቱ ስልጠናዎችን የመስጠት ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገለጹ፡፡

ክቡር አቶ ሰለሞን አረዳ ይህን የገለጹት ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአስተዳደር ዘርፍ የጽ/ቤት ሃላፊዎች፣ ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች በተዘጋጀ ስልጠና ማጠቃለያ ላይ በሰጡት የስራ መመሪያ ነው፡፡

በአስተዳደር ዘርፍ የፍርድ ቤቱን አገልግሎት አሰጣጥ...

3333

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአስተዳደር ዘርፍ የአገልግሎት አሰጣጥን የሚያቀላጥፍ የአቅም ግንባታ ስልጠና 630 ለሚጠጉ የፍርድ ቤቱ የአስተዳደር ሰራተኞች ከግንቦት 04 ቀን 2014 እስከ ግንቦት 21 ቀን 2014 ዓ/ም ቢሾፍቱ በሚገኘዉ የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲቲዩት በአራት ዙር ሰጥቷል፡፡

ሰበር ሰሚ ችሎቱ ሕጋዊነቱ ባልተረጋገጠ ሁኔታ በእስር ላይ...

3476

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 3ተኛ ሰበር ሰሚ ችሎት ዛሬ ግንቦት 16 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት  ከቀረበባቸው ክስ በከፍተኛ ፍርድ ቤት በነጻ ከተሰናበቱ በኋላ ህጋዊነቱ ባልተረጋገጠ ሁኔታ የተያዙና ይህ ውሳኔ እስከተሰጠበት ቀን ድረስ በእስር ላይ የሚገኙትን ኮሎኔል ገመቹ አያና ከእስር እንዲለቀቁ ወስኗል፡፡  ለፌዴራል ፖሊስም ተጠርጣሪውን በዛሬዋ ዕለት እንዲለቅ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የተቀናጀ የጉዳዮች አስተዳደር መረጃ...

4450

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የሚሰጠውን የዳኝነት አገልግሎት በከፍተኛ ደረጃ ራስ-ተግባሪ (Automation) ስርዓት የተደገፈ ለማድረግ የወጠነው ፐሮጀክት በአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት- ፍትህ ተግባራት ኢትዮጵያ (USAID- Justice Activities-Ethiopia) ድጋፍ ስርዓቱን ለማልማት በአለም ዓቀፍ ጨረታ ያሸነፈው ሲነርጂ ኢንተርናሽና ሲስተምስ የተባለ ድርጅት ጽንሰ-ተልዕኮ መርሃ ግብር (Inception Mission Schedule ) ከግንቦት 1 -5 ቀን 2014 ዓ.ም አካሂዷል፡፡

First7071727375777879Last