Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ ኃይለ ጊዮርግስ ይልማ ወልደአብ እና እነ አቶ አዲስ እሸቱ (4) ሰዎች የሰ/መ/ቁ 252056

ለዚህ የሰበር አቤቱታ ምክንያት የሆነዉ ክርክር የተጀመረዉ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ጣርማ በር ወረዳ ፍርድ ቤት ሲሆን በወረዳዉ ፍርድ ቤት 1ኛ ተጠሪ ከሳሽ የአመልካች አዉራሽ ሟች አቶ ይልማ ወልደአብና ከ2ኛ እስከ 4ኛ ተጠሪዎች ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ 1ኛ ተጠሪ በጣርማ በር ወረዳ ፍርድ ቤት ከ2ኛ እስከ 4ኛ ተራ ቁጥር ላይ በተጠቀሱት ተጠሪዎችና በአመልካች አባት በሟች አቶ ይልማ ወልደአብ ላይ ባቀረቡት ክስ በክሱ ላይ አዋሳኞቹ የተመለከተዉን 400 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈዉን  የመኖሪያ ቤት ከነሰርቪስ  ቤቶቹ ጭምር የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ/ም በተፈረመ የሽያጭ ዉል ከ2ኛ እስከ 4ኛ ተጠሪዎች (ከሥር 1ኛ እስከ 3ኛ ተከሳሾች) በብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ገዝተዉ ካርታ በስማቸዉ የተሰጣቸዉ ቢሆንም በይዞታዉ ላይ ካሉ ቤቶች መካከል አንዱን የአመልካች ወላጅ አባት (የሥር 4ኛ ተከሳሽ) ይዘዉ ለመልቀቅ ፈቃደኛ አለመሆናቸዉን ገልፀዉ ከ2ኛ እስከ 4ኛ ተጠሪዎች (የሥር 1ኛ እስከ 3ኛ ተከሳሾች) የሸጡላቸዉን ቤት ከአመልካች አባት (የሥር 4ኛ ተከሳሽ) አስለቅቀዉ እንዲያስረክቡና የአመልካች አባትም (የሥር 4ኛ ተከሳሽም) መብት ሳይኖራቸዉ የያዙትን የ1ኛ ተጠሪን (የሥር ከሳሽን) ቤት ለቀዉ እንዲወጡ እንዲወሰንላቸዉ ዳኝነት በመጠየቅ ክስ አቅርበዋል፡፡መልካም ንባብ….

Previous Article የፌደራል ዐቃቤ ህግ እና አቶ አበበ ወንድሙ ኤጋ የሰ/መ/ቁጥር 251759
Next Article የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና አቶ መጣልኝ መላኩ የሰ.መ.ቁ.252953
Print
5561

Documents to download

  • 252056(.pdf, 838.15 KB) - 630 download(s)

«July 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
293012345
6789101112
13141516171819
20212223242526
272829303112
3456789

የፍ/ቤቱ ዳኞች በጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር እና በመዛግብት...

ፍርድ ቤቱ 20 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ከመንግስት ማግኘቱም ተጠቁሟል

4241

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች በ2014 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የፍትሐብሔር ጉዳዮች ፍሰት አስተዳደርን ተግባራዊ በማድረግ እና በመዛግብት አፈጻጸም ያስመዘገቡት ውጤት አበረታች በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባው የፍርድ ቤቱ ፕሬዚደንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ገለጹ፡፡

ክብርት ፕሬዚደንትዋ ይህን የገለጹት የፍርድ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ ዳኞች እና ረዳት ዳኞች በተሳተፉበትና በፌደራል ፍ/ቤቶች የአምስት ዓመታት (2014-2018 ዓ.ም) ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ዋና ዋና ይዘት እና በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የችሎቶችና ዳኞች የ2014 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የመዛግብት አፈጻጸም ላይ መጋቢት 3 ቀን 2014 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል የተደረገውን ውይይት ሲያጠቃልሉ ባደረጉት ንግግር ነው፡፡

የፌደራል ፍርድ ቤቶች ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በፓናል...

2962

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ111ኛ ጊዜ፣ በአገራችን ደግሞ ለ46ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች 8) የፌደራል ፍርድ ቤቶች የካቲት 29 ቀን 2014 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል በፓናል ውይይት አከበሩ፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የፓናል ውይይቱን በንግግር ሲከፍቱ ባደረጉት ንግግር የሴቶች የሲቪልም ሆነ የፖለቲካ መብት እና ተሳትፎ ከኢኮኖሚ መብት ጋር ተያያዥ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ለዚህም ማሳያው የግል ገቢ የሌላት ሴት ከሚበድላት ባል ጋር ለመኖር እንደምትገደድና አማራጭ የሥራ ዕድል የሌላት ሴትም የመጥፎ አለቃን እብሪትና ትንኮሳ ችላ ለመኖር የምትገደድ መሆንዋ ትስስሩን እንደሚያሳይ አስረድተዋል፡፡

ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ አገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ...

2522

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሹመታቸውን ያጸደቀላቸው የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን አመራሮች የቃለመሀላ ሥነ-ሥርዓት ዛሬ የካቲት 14 ቀን 2014 ዓ.ም አስፈጽመዋል፡፡

ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ስራ ውጤታማ የሚሆነው ከባለድርሻ አካላት እና ከሕብረተሰቡ አስፈላጊው ትብብርና ድጋፍ ሲሰጠው መሆኑን በቲውተር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

ክብርት ፕሬዝደንቷ ከምክክር ኮሚሽኑ ብዙ ይጠበቃልም ብለዋል::

የፍርድ ቤቱ አስተዳደር ዘርፍ አፈጻጸም ከፍተኛ መሻሻል...

3182

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአስተዳደር ዘርፍ የስራ ክፍሎች አፈጻጸም ከፍተኛ መሻሻል ያሳየ መሆኑን የ2014 መጀመሪያ መንፈቅ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ገምገማ ውጤት ማመልከቱ ተገለጸ፡፡ 

በዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ማጠቃለያ መድረኩ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ የተገኙ ሲሆን የቀረበውን የማጠቃለያ ሪፖርት መሰረት በማድረግ በሰጡት አስተያየት በአስተዳደር ዘርፉ እየተመዘገበ ያለው አመርቂ አፈጻጸም በፍርድ ቤቶች እየተከናወኑ ያሉ የማሻሻያ ስራዎች ፍሬ እያፈሩ ስለመምጣታቸው ያላቸውን እርግጠኝነት ከፍ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

First7071727375777879Last