በአዋጅ ቁጥር 322/1995 መሰረት...

 በአዋጅ ቁጥር 322/1995 መሰረት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተደራጀባቸው ክልሎች ያሉ የክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች በኢፌዲሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 78(2) እና 80(4) ድንጋጌ  በተሰጣቸዉ የፌደራል መጀመሪያ... Read more

ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት...

ከክርክሩ መረዳት እንደሚቻለዉ አመልካች ባቀረቡት ክስ በተጠሪ ተቋም ዉስጥ መምህር ስሆን ከተጠሪ ጋር ህዳር 30 ቀን 2009 ዓ/ም በተደረገ የአገልግሎት ስምምነት ዉል ለአራት ዓመት እስከ ህዳር 30 ቀን 2013 ዓ/ም ድረስ ከስራ... Read more

በአዋጅ ቁጥር 322/1995 መሰረት...

በአዋጅ ቁጥር 322/1995 መሰረት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተደራጀባቸው ክልሎች ያሉ የክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች በኢፌዲሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 78(2) እና 80(4) ድንጋጌ በተሰጣቸዉ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት... Read more

ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት...

ከዚህ በፊት በሰ/መ/ቁጥር 249795 ላይ “ሠራተኛዉ በተከታታይ ከ5 ቀናት በላይ ለሆነ ጊዜ ከሥራ ቢቀር እንኳ ከሥራ ለቀረበት ለእያንዳንዱ ቀን አሠሪዉ ማስጠንቀቂያ (Warning in Writing) ሳይሰጥ የሥራ ዉልን... Read more
12345678910Last
«September 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
31123456
78910111213
14151617181920
21222324252627
2829301234
567891011

ፍርድ ቤቱ ሐሰተኛ የቃለ-መሐላ አቤቱታ ያቀረቡ ባለጉዳይን...

3438

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሶስተኛ ሰበር ችሎት ሐሰተኛ ቃለ-መሐላ አቤቱታ ያቀረቡ ባለጉዳይን በችሎት መድፈር ጥፋተኛ ናቸው በማለት ሐምሌ 27 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት በአንድ ወር ከአስራ አምስት ቀን ቀላል እስራት እንዲቀጡ ወሰነ፡

ፍርድ ቤቱ በእስራት እንዲቀጡ የወሰነባቸው አቶ ኃይለማርያም ወዳጆ በደሀ ደንብ መስቀልኛ የሰበር አቤቱታ ለማቅረብ የዳኝነት ለመክፈል ምንም ሀብት እና ንብረት የሌላቸውና በቀበሌ ቤት የሚኖሩ መሆኑን በቃለ-መሐላ በማረጋገጥ አቤቱታቸውን በሀሰተኛ መንገድ በማቅረባቸው ነው፡፡

ዜና መግለጫ

የፌደራል ፍርድ ቤቶች ከነሐሴ 1-30 ባለው ጊዜ መደበኛ የዳኝነት አገልግሎት መስጠታቸውን ይቀጥላሉ

8643

በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/13 አንቀፅ 38(2) መሰረት የፌደራል ፍርድ ቤቶች ከነሐሴ 1 እስከ መስከረም 30 ባለው ጊዜ ዝግ እንደሚሆኑ ይደነግጋል፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ዳኞች ባላቸው የትርፍ ጊዜ አስቸኳይ የሆኑ ጉዳዮችን ብቻ ሊያስተናግዱ እንደሚገባም አዋጁ ያስቀምጣል፡፡ ዳኞች ዓመቱን ሙሉ እጅግ አድካሚ የሆነ የዳኝነት አግልግሎት ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡ በዚህም አዎንታዊ የሆኑ ውጤቶች ተገኝተዋል፡፡ ይህን ስራ ይበልጥ ለማስቀጠል፣ ወደ 2015 ዓ.ም የሚያልፉ መዝገቦችን ቁጥር ለመቀነስ፣ የበሰሉ መዝገቦችን እልባት ለመስጠት፣ እስረኛ ያለባቸውን መዝገቦች ቅድሚያ ሰጥቶ ለመስራት እንዲያስችል በዳኞች ፈቃደኝነት ላይ በመመስረት የፌዴራል ፍርድ ቤቶቹ ከነሐሴ 1-30/2014 ዓ.ም ባለው ጊዜ መደበኛውን የዳኝነት አገልግሎት መስጠታቸውን የሚቀጥሉ ይሆናል፡፡

«ትልቁ የመሪዎች መለያ አውቃለሁ ባይነት ሳይሆን ለመማር...

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክብርት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ

3387

ክብርት ፕሬዚደንትዋ ይህን የገለጹት የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዚደንትና የፌደራል ፍርድ ቤቶች ቃል አቀባይ የሆኑት ክቡር አቶ ተስፋዬ ንዋይ «የአመራር ክህሎት» በሚል ርዕስ ያሳተሙትን መጽሐፍ ሐምሌ 2 ቀን 2014 ዓ.ም በሐያት ሪጀንሲ ሆቴል ለማስመረቅና ለማስገምገም በተዘጋጀ ሥነሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር ነው፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ሆነ የዳኞች አስተዳደር...

3952

የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ በአዋጅ ቁጥር 1233/2013 በተሰጠው ስልጣን መሰረት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር መመሪያን ለመተግበር ያስችለው ዘንድ የተከማቹ መዛግብትን በቅድሚያ ማጥራት አስፈላጊ መሆኑን ገልጾ ጊዜያዊ ዳኞች እንዲመደቡለት ያቀረበውን ጥያቄ አቅርቧል፡፡

ይህንን ተከትሎ ጉባዔው በፌዴራል ዳኝት አስተዳደር አዋጅ  ቁጥር 1233/2013 አንቀጽ 26 (2) ከአንድ ፍርድ ቤት ወደ ሌላ የፍርድ ቤት ደረጃ በጊዜያዊነት ዳኞችን መድቦ የማሰራት ስልጣኑን ተጠቅሞ የጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ሸክምን ይወጣሉ ያላቸውን አራት የከፍተኛ ፍርድ  ቤት ዳኞች ከሰኔ 2014 ዓ.ም እስከ ህዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ብቻ የመዝገብ ክምችት እንዲያጠሩ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ 

First7071727375777879Last