Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ ተገኝ ደምሴ ወንድአፍራሽ እና ወ/ሮ አየለች ደሳለኝ እንዳሻው የሰበር መ/ቁጥር 248810

ጉዳዩ የንብረት መፋለም ክስን የሚመለከት ነው፡፡ የሰበር አቤቱታው የቀረበው የሐረሪ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.13375 በቀን 18/11/2011 ዓ/ም የሰጠውን ውሳኔ የክልሉ  ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችሎት በመ/ቁ. 04927 በቀን 01/04/2012 ዓ/ም የቀረበውን ይግባኝ ቅሬታ ባለመቀበል የሥር ፍርድ ቤትን ውሳኔ በትዕዛዝ በማጽናት የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል አመልካች ሰኔ 09 ቀን 2015ዓ/ም በተጻፈ አቤቱታ ቅሬታ በማቅረባቸው ነው፡፡

 ከሥር ፍርድ ቤቶች የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው በሥር ፍርድ ቤት አመልካች ተከሳሽ  ተጠሪ ከሳሽ ሆነው ተከራክረዋል፡፡ ተጠሪ በ23/03/2008ዓ/ም ጽፈው ባቀረቡት ክስ አዋሳኞቹ በክሱ የተጠቀሰው የቤት ቁጥር 144 የሆነ በ 2921 ካ.ሜ የመሬት ይዞታ ላይ ያረፈ ሰባት ክፍሎች ያሉት ፎቅ ቤትና ሰርቪስ ቤት ሟች እህታችን በግዥ አግኝተው ሲጠቀሙበት ቆይተው በ1962 ዓ/ም በነበረው የሶማሊያ ጦርነት ወጥተው ስላልተመለሱ ተጠሪ ከወንድሜ ሻምቤል ፈለቀ ደሳለኝ ጋር በመሆን የእህታችንን መጥፋት እና ወራሽነት በ1972 ዓ/ም አሳውጀውን ቤቱ በውርስ ለተጠሪ እና ወንድሜ ከተላለፈ በኃላ፤ የተጠሪ ወንድም በ1988 ዓ/ም በውርስ ያገኙትን የአከራካሪውን ቤት ድርሻ በስጦታ ያስተላለፉልኝን ጨምሮ ከጠቅላላ ይዞታ ውስጥ በ1394 ካ/ሜ ላይ ካርታ በስሜ 11/09/1996 ዓ/ም የተሰራልኝ ሲሆን ቀሪው 1527 ካ/ሜ ይዞታ እና ፎቅ ቤት ወደ ፊት ይሰራልሻል ተብዬ ነበር፤ከዚያ በኋላ ሟች እህቴ ያከራየቻቸው የተከሳሽ ቤተሰቦችከ1969 ዓ/ም ጀምሮ በቤት ውስጥ መኖር ቀጠሉ፤ አመልካች ምንም መብት ሳይኖረው በምዕራብ አቅጣጫ የሚገኙትን አምስት ክፍል ቤቶችን ይዞ በማከራየት፤ ከ2001 ዓ/ም እስከ 2004 ዓ/ም ተለጣፊ ቤቶችን በመስራት እየተጠቀሙ በመሆኑና ቤቱንም ለማስረከብ ፈቃደኛ ስላልሆኑ በሕገ-ወጥ መንገድ የሠሩትን ቤት አፍርሰው የቤት ቁጥር 144 እና ይዞታውን ለቀው እንዲያስረክቡ ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ…

Previous Article ቁአቶ ጌታቸው ጎነሞ እና አቶ ፍሰሀ ታምራትየሰ/መ/ቁ249348
Next Article የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገቢዎች ቢሮ ዓቃቤ ሀግ እና ወ/ሮ መዓዛ በልስቲየሠ/መ/ቁጥር 248735
Print
5312

Documents to download

  • 248810(.pdf, 854.77 KB) - 663 download(s)

«August 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
272829303112
3456789
10111213141516
17181920212223
24252627282930
31123456

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የሙስና ተግባራት መከላከያና መቆጣጠሪያ...

3311

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያዘጋጀውን እና በፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ውይይት ተደርጎበትና ቅቡልነት አግኝቶ ለትግበራ ዝግጁ የሆነውን “በዳኝነት አካል ውስጥ የሚታዩ የሙስና ተግባራት መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ስትራቴጂ” የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አመራሮች፣ የምድብ ችሎት ተጠሪ ዳኞች፣ ሰብሳቢ ዳኞች፣ የዳኞች ተወካዮች እና የአስተዳደር ዘርፍ ልዩ ልዩ የስራ ክፍል ሃላፊዎች በተሳተፉበት የውይይት መድረክ ይፋ አድርጓል፡፡

ስትራቴጂው ይፋ የተደረገበት የውይይት መድረክ ለስትራቴጂው አተገባበር የሚገጁ ሃሳቦችን በማንሸራሸር ይሁንታ ለመስጠት የተዘጋጀ ነው፡፡

በፌደራል ፍርድ ቤቶች የተገልጋዮች የእርካታ ደረጃ...

3469

የፌደራል ፍርድ ቤቶች ተገልጋዮች በዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያላቸውን የእርካታ ደረጃ ለማወቅ በገለልተኛ ተቋም በተካሔደ የጥናት ግኝት በአማካይ 78 በመቶ የሚሆኑ ተገልጋዮች በአገልግሎት አሰጣጡ እርካታ እንዳላቸው መግለጻቸውን የጥናቱ ውጤት አመለከተ፡፡

ይህም ውጤት በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ለተገልጋዮች የእርካታ መመዘኛ ነጥብ ከተቀመጠው 75 በመቶ በላይ የተመዘገበበት በመሆኑ ውጤታማ የሚባል የእርካታ ደረጃ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ፍርድ ቤቱ የዩኒቨርሲቲ የሕግ ተማሪዎችን አቅም ለማጎልበት...

2980

የፌደራል ፍርድ ቤቶች በከፍተኛ የትምሕርት ተቋማት ከሚገኙ የሕግ ትምሕርት ቤቶች ጋር በመቀናጀት የሕግ ተማሪዎች በፍርድ ቤቶች የሜንተርሽፕ እና የኢንተርንሽፕ ፕሮግራም እንዲሳተፉ በማድረግ የሚያከናውኑት ተግባር ትውልድን የማነጽ ሥራ መሆኑን የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዚደንት እና የፌደራል ፍርድ ቤቶች ቃል አቀባይ ክቡር አቶ ተስፋዬ ንዋይ ገለጹ፡፡

ፍርድ ቤቱ የዲጂታል የሀብት ማስመዝገብ መርሐ-ግብር አስጀመረ

3499

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የዲጂታል የሀብት ምዝገባና ማሳወቅ መርሐ-ግብር በፌደራል ፍርድ ቤቶች መጀመሩን መጋቢት 8 ቀን 2014 ዓ/ም በፍርድ ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ በተካሔደ ሥነሥርዓት ይፋ አደረጉ፡፡

በፌደራል ፍርድ ቤቶች የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ተግባራዊ የሚደረገውን የዲጂታል የሀብት ምዝገባና ማሳወቅ መርሐ-ግብር የተጀመረው ፍርድ ቤቱ እና የፌደራል የሥነምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በጋራ ባዘጋጁት ሥነሥርዓት ላይ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ሀብታቸውን እንዲያስመዘግቡ በተከናወነ ሥነሥርዓት ነው፡፡

First7172737476787980Last