Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ እና የማነ ግርማይ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ የሰ.መ.ቁ 246233

የጉዳዩ አመጣጥ ተጠሪ ለግልግል ዳኝነት ጉባኤ በ1ኛ አመልካች ላይ ባቀረበው ክስ በተጠሪ እና በ2ኛ አመልካች(ስር ጣልቃገብ ) መካከል ከወራቤ እስከ በጆበር ያለውን 38.5ኪ.ሜ የመንገድ ስራ ፐሮጀክት ለማከናወን እ.ኤ.አ ሜይ 20 2016 ውል የተፈረመ ሲሆን የውሉም አይነት ስራ ተቋራጩ(2ኛ አመልካች) የዲዛይንና የግንባታ ስራውን በሙሉ በኃላፊነት የሚያከናውንበት ነው፡፡ በውሉ መሰረት ስራ ተቋራጩ የመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና የማቅረብ ግዴታ ስላለበት ይህን ተከትሎ ተቋራጩ የውሉን 10% ይኅውም ለብር 45‚844‚565 እ.ኤ.አ ከሜይ 13 2016 ጀምሮ ለአራት አመት ጸንቶ የሚቆይ የቦንድ ፖሊሲ ቁጥሩ በተገለጸ 1ኛ አመልካች የመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና ሰጥቷል፡፡ በውሉ መሰረት እ.ኤ.አ ጃንዋሪ 26 2017 የተጀመረው የግንባታ ስራ በ1095 ቀናት ተጠናቆ ለግዜያዊ ርክክብ ብቁ መደረግ ሲገባው እና ከአመት በኋላ ጃንዋሪ 2018 አፈጻጸሙ 30.38% መሆን ሲገባው የስራ ተቋራጩ አፈጻጸም የውሉ 8% ላይ ነበር፡፡ በዛን ግዜም ከውሉ መፈጸሚያ ግዜ 33.8% ባክኖ ነበር፡፡ ተጠሪ ለስራ ተቋራጩ በቂ የቅድሚያ ክፍያ ገንዘብ ቢሰጠውም፤ ሶስት የክፍያ ሰርተፍኬቶችም ጸድቀው ገንዘብ ቢከፈለውም፤ የውል ግዴታውን እንዲወጣ ተጠሪና የፕሮጀክቱ አማካሪ ድርጅት ተደጋጋሚ ማሳሰቢያና ማስጠንቀቂያ ቢሰጡትም ይህን ባለመቀበል የግንባታ ቦታውን ጥሎ በመሄድ አይነተኛና መሰረታዊ የውል ጥሰት በመፈጸሙ ተጠሪ በውሉ መሰረት እ.ኤ.አ በ1/3/18 በተጻፈ ደብዳቤ የ2ኛ አመልካችን(ስራ ተቋራጭ) የስራ ውል አቋርጧል፡፡

የስራ ውል መቋረጡን ተከትሎ 1ኛ አመልካች የዋስትናውን ገንዘብ ገቢ እንዲያደርግ ተጠሪ ቢጠይቀውም የተለያዩ ምክንያቶችን በማቅረብ የዋስትና ግዴታውን ለመወጣት ፈቃደኛ ባለመሆኑ 1ኛ አመልካች በመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና መሰረት ብር 45‚844‚565 ክፍያ እንዲፈጽም ከተጠየቀበት ግዜ ከ27/6/2010ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ ህጋዊ ወለድ ጋር እንዲከፍል እንዲወሰንበት በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡መልካም ንባብ…

Previous Article አቶ ዮሀንስ ካሳዬ እና የፍትህ ሚኒስቴር ዓቃቤ ሕግ የሠ/መ/ቁጥር 273594
Next Article አቶ ጉዕሽ ካሳ ደሞዝ እና እነ አቶ አማኑኤል ወልደሊባኖስ ተስፋዬ የሠ/መ/ቁጥር 243564
Print
2595

Documents to download

  • 246233(.pdf, 1.05 MB) - 338 download(s)

«January 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
2930311234
567891011
12131415161718
19202122232425
2627282930311
2345678

ለስትራቴጂካዊ ዕቅድ ዝግጅት የተካሄዱ የትንተና ጥናቶች...

2840

በአማካሪ ድርጅት የሚሰራውን ሶስተኛው የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ዝግጅት ሂደትን እንዲከታተል በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተቋቋመው ዓብይና የቴክኒክ ኮሚቴ አማካሪ ድርጅቱ ለስትራቴጂካዊ ዕቅድ ዝግጅት ባካሄዳቸው የትንተና ጥናቶች ላይ ተጨማሪ ግብዓት ሰጠ፡፡

ፍርድ ቤቶች በዘጠኝ ወሩ ከአንድ መቶ 19 ሺህ በላይ...

2928

የፌደራል ፍርድ ቤቶች በ2013 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ለ119, 413 መዛግብት እልባት መስጠታቸውን የሶስቱ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የተጠቃለለ የዘጠኝ ወር የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አመለከተ፡፡

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሀዋሳ ማዕከል በይፋ...

4986

የፌዴራል ጉዳዮችን በውክልና እንዳይመለከቱ ስልጣናቸው በተነሳባቸው የክልል ፍርድ ቤቶች የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተዘዋዋሪ ችሎት በማደራጀት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

First7071727374757779