Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ መሀመድ አለሙ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰበር መዝገብ ቁጥር 266395

ጉዳዩ የቀረበው የኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች 1ኛ ተከሳሽ አሁን የክርክሩ አካል ያልሆነው የትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ 2ኛ ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበው 1ኛ ክስ የወ/ህግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)፣ 34(1) እና 693(1) በመተላለፍ በትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ ውስጥ የፋብሪካው ኃላፊ እና ባለንብረት ሆኖ በሚሰሩበት ጊዜ ለግል ተበዳይ አቶ ሸምሱ አወል የብር አምስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የሚመነዘር ቼክ ሰጥቶ የግል ተበዳይ ገንዘቡን ለማውጣት ወደ ባንክ ሲሄድ በቂ ገንዘብ የለውም በመባሉ ገንዘቡን ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ስለዚህ በቂ ስንቅ ሳይኖር ቼክ በመስጠት ወንጀል ተከሷል የሚል ነው፡፡ አመልካች የወንጀሉን ድርጊት አልፈፀምኩም ብሎ ክዶ በመከራከሩ ተጠሪ የሰውና የሰነድ ማስረጃ አቅርቦ እንደ ክስ አቀራረቡ አስረድቷል፡፡ አመልካች እንዲከላከል ታዞ መከላከያ ማስረጃ ያቀረበ ሲሆን የአመልካች መከላከያ ምስክሮች ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቼክ መጥፋቱን አስረድተዋል፡፡መልካም ንባብ…. 

Previous Article ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594
Next Article ጨመሬ ቶሎሳ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰ/መ/ቁጥር 267231፣267230
Print
8092

Documents to download

  • 266395(.pdf, 849.74 KB) - 1023 download(s)

«August 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
272829303112
3456789
10111213141516
17181920212223
24252627282930
31123456

ፍርድ ቤቱ ለአራት ክልሎች ጠቅላይ ፍ/ቤቶች የቁሳቁስ...

3273

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አራት የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶችን ለማጠናከር ዛሬ የካቲት 9 ቀን 2014 ዓ.ም የሰባት ሚሊዮን ብር ግምት ያለው የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡

የቁሳቁስ ድጋፍ የተደረገላቸው በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት ለደረሰባቸው ለአማራ እና ለአፋር ክልሎች ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች እንዲሁም በቅርቡ በአዲስ መልክ በክልልነት የተቋቋሙትን የሲዳማ እና የደቡብ ምዕራብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶችን ለማጠናከር ነው፡፡

የፌደራል ፍርድ ቤቶችን የዳኝነት ነጻነት፣ ገለልተኝነት...

3312

የፌደራል ፍርድ ቤቶችን የዳኝነት ነጻነት፣ ገለልተኝነት እና ተጠያቂነትን ለማጠናከር የተወሰዱ እርምጃዎች

የካቲት 6 ቀን 2014 ዓ.ም «የፌደራል ፍርድ ቤቶች አሁናዊ ሁኔታ» ዓመታዊ ጉባኤ ላይ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ባቀረቡት ሪፖርት በ2013-2014 በጀት ዓመት አጋማሽ በፍርድ ቤቱ የሪፎርም ሥራዎች ዙሪያ የተከናወኑ ተግባራትን ዳስሰዋል፡፡ ክብርት ፕሬዚደንትዋ ዛሬም ሙሉ በሙሉ ተቀርፏል ባይባልም የፌደራል ፍርድ ቤቶችን የዳኝነት ነጻነት፣ ገለልተኝነት እና ተጠያቂነትን ለማጠናከር የተለያዩ እርምጃዎች የተወሰዱ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ይህ የገለልተኝነት እና የነጻነት ጉዳይ ዳኞች ከውጭም ሆነ ከውስጥ ጣልቃ ገብነት ተጽዕኖ ሳይደርስባቸው ሕግን ብቻ ተከትለው ውሳኔ እንዲሰጡ አስፈላጊ ሁኔታዎችን ማመቻቸትን ይጠይቅ ነበር ብለዋል፡፡ የዳኝነት ነጻነት የዳኞች ነጻነት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ፍ/ቤቱም እንደተቋም ለማንኛውም የፖለቲካም ሆነ ማህበራዊ ጫናዎች የተጋለጠ እንዳይሆን አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እና እርምጃዎችንም መውሰድ ይጠይቅ እንደነበር ሳይጠቅሱ አላለፉም፡፡ እንደተከናወኑ ከጠቀሷቸው ተግባራት መካከል፡-

«የፌደራል ፍርድ ቤቶች አሁናዊ ሁኔታ እና የወደፊት...

3753

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና በፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ «የፌደራል ፍርድ ቤቶች አሁናዊ ሁኔታ እና የወደፊት ዕይታ /State of the Judiciary/» በሚል ርዕስ ለሁለተኛ ጊዜ የተዘጋጀ ጉባዔ በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል የስብሰባ አዳራሽ የካቲት 6 ቀን 2014 ዓ.ም ተካሔደ፡፡

የመጀመሪያው ጉባዔ በ2012 የተካሔደ ሲሆን መድረኩ በኮቪድ 19 ምክንያት ተቋርጦ ከቆየ በኋላ ሁለተኛው ጉባዔ በፌደራል ፍርድ ቤቶች በ2013 በጀት ዓመት እና በ2014 ግማሽ በጀት ዓመት በተገኙ ዋና ዋና ውጤቶች ላይ ትኩረት በማድረግ ተከናውኗል፡፡

የቅድመ መዋቅር ነባራዊ ሁኔታ ትንተና  እና ረቂቅ ተቋማዊ...

3712

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ተቋማዊ መዋቅርን እንዲሰራ በአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት - በፍትህ ፕሮጀክት የተቀጠረ እማካሪ ድርጅት ያካሄደውን የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ነባራዊ ሁኔት ትንተና ውጤት በፍርድ ቤቱ በኩል ስራውን እንዲከታተል ለተቋቋመ አብይ ኮሚቴ አቀረበ።

አማካሪ ድርጅቱ ( HST) ቀደም ሲል እያካሄደ ያለውን ጥናት በተደጋጋሚ ለዐብይ ኮሚቴው በማቅረብና የጥናት ስልት፣ ሂደት፣ ይዘት እና ወስን ላይ የማዳበሪያ እና አቅጣጫ ጠቋሚ ሃሳቦችን ሰብስቧል።

First7374757678808182Last