Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ ተስፋዬ ደገፋ እና ዶ/ር ትዕዛዙ ተፈራ ፤የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ጽ/ቤት፤የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት የሰ/መ/ቁ 259947

ለዚህ የሰበር ክርክር ምክንያት የሆነዉ ክርክር የተጀመረዉ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን በከፍተኛዉ ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ፣ ተጠሪዎች ደግሞ ተከሳሾች በመሆን መከራከራቸዉን የሥር ፍ/ቤቶች ዉሳኔ ያመለክታል፡፡ ክርክሩ በማህበር በመደራጀት ከተገኘዉ ይዞታ ጋር የተያያዘ ሲሆን አመልካች በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተጠሪዎች ላይ ባቀረቡት  ክስ በ03/08/1990 ዓ/ም ተመዝግቦ በፀደቀዉ የመተዳደሪያ ደንብ መሠረት የተደራጀ ታቦር የመኖሪያ ቤቶች ኅብረት ሥራ ማኅበር አባል በመሆን ተደራጅተዉ ማኅበሩ በሕጋዊ መንገድ ከመንግሥት ካገኘዉ ጠቅላላ ይዞታ ላይ መጠኑ 203.67 ካሬ ሜትር የሆነዉን የክርክሩን ይዞታ   በድርሻ እንደሰጣቸዉና የዚሁ ይዞታ ሕጋዊ ባለመብት ስለመሆናቸዉም በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 281839 በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ኅብረት ሥራ ጽ/ቤትና በኮልፌ  ቀራኒዮ ክለ ከተማ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት ላይ ክስ አቅርበዉ መብታቸዉ ተረጋግጦ ዉሳኔ እንዲያገኝ የሚል ነው፡መልካም ንባብ…

Previous Article ወ/ሮ ሙርሽዳ ሁሴን እና ወ/ሮ አልፊያ ሁሴን (13) ሰዎች የሰ/መ/ቁ 257243
Next Article ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594
Print
5385

Documents to download

  • 259947(.pdf, 828.26 KB) - 685 download(s)

«June 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
25262728293031
1234567
891011121314
15161718192021
22232425262728
293012345

የክብርት ፕሬዝደንቷ ጉብኝት በድሬደዋ ምድብ ችሎቶች

3770

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ የፌዴራል ከፍተኛ እና መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ድሬደዋ ምድብ ችሎቶችን ጎብኝተዋል::

ክብርት ፕሬዝደንቷ በጉብኝታቸው ከሁለቱም ፍርድ ቤቶች ምድብ ችሎቶች የዳኝነት አገልግሎት የሚሰጥበትን ሁኔታ እና የምድብ ችሎቶቹን የችሎት እና የልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎችን አደረጃጀት ተመልክተዋል፡፡ ከፍርድ ቤቶቹ ክቡራን ዳኞች እና የአስተዳደር ሰራተኞች ጋርም ወይይት አካሄደዋል::

በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በተለያየ መደብና ስራ ክፍሎች...

«ቀልጣፋ የአገልግሎት አሰጣጥ ባህል እና አሰራርን ማዳበር» በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሥልጠና ተሰጠ

1880

በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር መመሪያን ተግባራዊ ለማድረግ እንዲረዳ በተለያየ መደብና ስራ ክፍሎች ሲከናወን የነበረውን የሬጅስትራር አገልግሎት ወደ አንድ ማዕከል ሰብሰብ በማድረግ ባለሙያዎች እና ሰራተኞች በቡድን እና በትብብር መርህ ስራቸውን እያከናውኑ እንደሚገኙ ተገለጸ፡፡

ይህን የገለጹት በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፕሬዚደንት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ቦጃ ታደሰ በፍ/ቤቱ የሬጅስትራር አገልግሎትን ለሚያከናውኑ ባለሙያዎች እና ሰራተኞች በጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር መመሪያ ላይ ህዳር 18 ቀን 2014 ዓ.ም በፍ/ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሲሰጡ ነው፡፡

የዓለምአቀፍ የ16 ቀን ፀረ-ጾታዊ ጥቃት እንቅስቃሴ...

2935

ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ዓለምአቀፍ የ16 ቀን ፀረ-ጾታዊ ጥቃት እንቅስቃሴን ለማስጀመር የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ባዘጋጀው መድረክ በተካሄደ መድረክ ላይ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ የመልዕክቱ ሙሉ ይዘት እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

ዳኞች ስራ ላይ ባሉ ህጎችና ፋይዳቸው ላይ የጽሁፍ...

2804

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ሰለሞን አረዳ ዳኞች በስራ ላይ ባሉ ህጎችና ፋይዳቸው ላይ ጥናትና ምርምር በማካሄድ የጽሑፍ ውጤቶችን ማበርከት እንደሚጠበቅባቸው ገለጹ፡፡

አቶ ሰለሞን አረዳ ይህን የገለጹት በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝደንት በሆኑት በክቡር አቶ ተስፋዬ ነዋይ “የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ሕጋዊና ኢኮኖሚያዊ ገጽታ” በሚል ርዕስ የታተመ መጽሐፍ የምረቃና የትችት መርሃ ግብር ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ነው፡፡

First7475767779818283Last