Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ መሀመድ አለሙ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰበር መዝገብ ቁጥር 266395

ጉዳዩ የቀረበው የኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች 1ኛ ተከሳሽ አሁን የክርክሩ አካል ያልሆነው የትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ 2ኛ ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበው 1ኛ ክስ የወ/ህግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)፣ 34(1) እና 693(1) በመተላለፍ በትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ ውስጥ የፋብሪካው ኃላፊ እና ባለንብረት ሆኖ በሚሰሩበት ጊዜ ለግል ተበዳይ አቶ ሸምሱ አወል የብር አምስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የሚመነዘር ቼክ ሰጥቶ የግል ተበዳይ ገንዘቡን ለማውጣት ወደ ባንክ ሲሄድ በቂ ገንዘብ የለውም በመባሉ ገንዘቡን ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ስለዚህ በቂ ስንቅ ሳይኖር ቼክ በመስጠት ወንጀል ተከሷል የሚል ነው፡፡ አመልካች የወንጀሉን ድርጊት አልፈፀምኩም ብሎ ክዶ በመከራከሩ ተጠሪ የሰውና የሰነድ ማስረጃ አቅርቦ እንደ ክስ አቀራረቡ አስረድቷል፡፡ አመልካች እንዲከላከል ታዞ መከላከያ ማስረጃ ያቀረበ ሲሆን የአመልካች መከላከያ ምስክሮች ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቼክ መጥፋቱን አስረድተዋል፡፡መልካም ንባብ…. 

Previous Article ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594
Next Article ጨመሬ ቶሎሳ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰ/መ/ቁጥር 267231፣267230
Print
8092

Documents to download

  • 266395(.pdf, 849.74 KB) - 1023 download(s)

«August 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
272829303112
3456789
10111213141516
17181920212223
24252627282930
31123456

የዳኝነት ስርዓቱን ለማሻሻል በሚደረገው ጥረት ፍርድ ቤቱ...

4048

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ስርዓቱን ለማሻሻል በሚደረገው ጥረት በቅርቡ ከተቋቋመው የኢትዮጵያ የፌዴራል ጠበቆች ማህበር ጋር አብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ሰለሞን አረዳ ገለጹ፡፡

ክቡር አቶ ሰለሞን ይህን የገለጹት በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነው በአዲሱ የፌደራል የጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥ እና አስተዳደር አዋጅ መሰረት ለተቋቋመው የጠበቆች ማህበር ስራ ማስጀመሪያ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ በእንግድነት ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ነው፡፡

ክቡር አቶ ሰለሞን አረዳ በሰጡት የማጠቃለያ አስተያየት...

2822

ክቡር አቶ ሰለሞን አረዳ (የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዚደንት) ጥር 9 ቀን 2014 ዓ.ም «ፍርድ ቤቶች እና የሽግግር ፍትሕ፤ ግጭቶች ሲከሰቱ ወይም ከግት በኋላ» በሚል ርዕስ በተዘጋጀው ሲምፖዚየም ላይ ከተሳታፊዎች የቀረቡ አስተያየቶችንና ጥያቄዎችን መሠረት በማድረግ በሰጡት የማጠቃለያ አስተያየት ካነሷቸው ነጥቦች መካከል ዋና ዋናዎቹ፡-

• ሲምፖዚየሙን ማዘጋጀት ያስፈለገው አሁን አገራችን ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ የዳኝነት ተቋሙ ሊኖረው ከሚችለው የዳኝነት ሚና ጋር ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡

በፌዴራል ፍ/ቤት ተዘዋዋሪ ችሎት 204 ፋይሎች ታይተው...

3401

በፌዴራል ፍ/ቤት ተዘዋዋሪ ችሎት 204 ፋይሎች ታይተው 68 ፋይሎች እልባት ማግኘታቸው ተገለጸ

በተለያየ የሃራችን ክፍሎች የተፈጠሩ ግጭቶች ጋር በተገናኘ በፌዴራል ፍ/ቤት ተዘዋዋሪ ችሎት 204 ፋይሎች ታይተው 68 ፋይሎች እልባት አግኝተዋል፡፡

በእያንዳንዱ ፋይል የተከሳሾች ቁጥር በአማካይ ከ 50 – 200 እንደሚድረስ የገለጹት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ ጉዳዩቹ ደግሞ እጅግ ውስብስብ ናቸው ብለዋል፡፡

ክብርት ፕሬዚደንትዋ «ፍርድ ቤቶች እና የሽግግር ፍትሕ፤ ግጭቶች ሲከሰቱ ወይም ከግጭት በኋላ » በሚል ርዕስ በስካይ ላይት ሆቴል ጥር 9 ቀን 2014 ዓ.ም በተዘጋጀ ሲምፖዚየም መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር በሀገራችን በተከሰቱ ግጭቶች ሕግንና ሞራልን የጣሱ በርካታ ተግባሮች እንደተከናወኑ ገልጸው በሴቶች እና ሕጻናት ላይ የተፈጸመው ወንጀል ደግሞ ሊታለፉ ከማይገባቸው ወንጀሎች የሚመደብ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ክስ የተቋረጠባቸው ሶስት የክስ መዝገቦች የስነ-ስርዓት...

4366

ባለፈው ሶስት ዓመት ተኩል የፌደራል ፍ/ቤቶች በሕገ መንግስቱ የተሰጣቸውን ሃላፊነት በተገቢው ደረጃ ለማከናወን በርካታ የለውጥ ተግባራትን ሲያከናውኑ ቆይተዋል፡፡ እነዚህ የለውጥ እርምጃዎች ትኩረት ያደረጉት በተቋማዊ እና በግለሰብ ዳኞች ደረጃ የፍ/ቤቱን ነጻነት እና ገለልተኝነት ማስከበር ነው፡፡ በተጓዳኝም ለተጠያቂነት ተቋማዊ ስርዓቶች ተዘርግተዋል፡፡ በፍ/ቤቱ አመራሮች እና ዳኞች በኩል ሲደረግ የነበረው ጥረት ዋናው ግብ የሚሰጠው የዳኝነት ዘርፍ ቀልጣፋ፣ ተገማች እና ተደራሽ በማድረግ በፍ/ቤቱ አገልግሎት ላይ የሕዝብ አመኔታ እንዲጨምር ነው፡፡

በዚህ ወር መጨረሻ በሚዘጋጀው “የፍ/ቤቱ አሁናዊ ሁኔታ” ጉባዔ እንደሚገልጸው በተለያየ ደረጃ የፍ/ቤቱ አገልግሎትም ሆነ ተደራሽነት እያደገ የመጣ ለመሆኑ ፍ/ቤቱ በገለልተኛ የጥናት ተቋም የሰራው የሕዝብ አስተያየት ሰርቬይ  “public perception survey” አመልክቷል፡፡

First7475767779818283Last