Selam Warga / Friday, March 13, 2026 / Categories: CASSATION, Cassation ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጠ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔ: መዝገብ ቁጥር 244308 ጉዳዩ በከተማ ክልል የሚገኝ መሬት ይዞታ መብት ለማስከበር የቀረበ ክስ የሚመለከት ነው፡፡ የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው በሥር ፍርድ ቤት አመልካች ተከሳሽ ሲሆን ተጠሪ ከሳሽ ነበሩ፡፡ ተጠሪ በ14/11/2013 ዓ/ም ጽፈው ባቀረቡት ክስ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ልዩ ስሙ ፊጋ በሚባል ሰፈር አዋሳኞቹ በክስ የተገለፀውን ግምቱ 2000 ካ.ሜ የሆነ የእርሻ መሬት ከደርግ መንግስት ጀምሮ ተገቢውን የመሬት ግብር በመክፈል ስጠቀምበት የቆየሁትን የእርሻ መሬት ለ11 ዓመት ውጭ ሀገር ቆይቼ ግንቦት 2012 ዓ.ም ወደ ሀገር ቤት ስመለስ ይዞታዬን እንዲያስተዳድሩልኝ ተወካይ አስቀምጬ እያለ አመልካች ምንም ህጋዊ መብት እና የውል ግንኙነት ሳይኖረው ግምቱ ብር 60,000 (ስልሳ ሺህ) የሆነውን ያጠርኩትን አጥር ሰኔ ወር 2011 ዓ.ም በማፍረስ ተወካዬንም ከይዞታው በማባረር ግንብ አጥር በማጠር ቤት ሰርቶ በሕገወጥ መንገድ ይዞታዬን የያዘብኝ በመሆኑ ያለፈቃዴ የገነባውን ቤትና አጥር አፍርሶ በፍ/ሕ/ቁ 1206 መሰረት ይዞታዬን ለቆ ያስረክበኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ Previous Article ሰባት ዳኞች በተሰየሙበት የሰበር ችሎት የተሰጠ የህግ ትርጉም Next Article ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጠ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔ: መዝገብ ቁጥር 271726 Print 4492 Documents to download ሰበር መዝገብ 244308 (1)(.pdf, 551.03 KB) - 967 download(s)
አዲስ ለተቀጠሩ ህግ ጉዳይ ጸሐፊ I እና የህግ ጉዳይ... አዲስ ለተቀጠሩ ህግ ጉዳይ ጸሐፊ I እና የህግ ጉዳይ... Tuesday, February 17, 2026 1398 አዲስ ለተቀጠሩ ህግ ጉዳይ ጸሐፊ I እና የህግ ጉዳይ ጸሐፊ II በ ቀን 06 እና 09/06/2018 ዓ.ም የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታን እና ከለዉጥ ስራዎች ጋር ለማስተዋወቅ የመግቢያ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ Read more
ሥነ-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥና የጥቅም ግጭት መከላከልና... ሥነ-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥና የጥቅም ግጭት መከላከልና... Monday, February 16, 2026 1561 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፌዴራል ሥነ-ምግባርና ፀረ -ሙስናና ኮሚሽን ጋር በመተባበር በሥነ-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥ እና የጥቅም ግጭት መከላከልና ማስተዳደር ላይ ከፍርድ ቤት ዘርፍ ለተውጣጡ የስራ ሃላፊዎች የካቲት 5 እና 6 ቀን 2018 ዓ.ም ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ Read more
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የኢትዮጵያ... የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የኢትዮጵያ... Friday, February 13, 2026 1158 የመግባቢያ ስምምነቱን የፈረሙት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት እና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ቢኒያም ኤሮ ናቸው፡፡ Read more
በዳኝነት ስርአቱ ውስጥ ለህጻናት ተስማሚ የፍትህ ስርአትን... በዳኝነት ስርአቱ ውስጥ ለህጻናት ተስማሚ የፍትህ ስርአትን... Wednesday, February 11, 2026 913 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት በዳኝነት ስርአት ውስጥ ለህጻናት ተስማሚ የፍትህ ስርአትን ለማጎልበት ከአጋር ድርጅቶች ጋር የጋራ ውይይት መድረክ በቀን 03/06/2018 ዓ.ም ተካሂዷል። Read more
10Mar2026 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Tuesday, March 10, 2026 Read more