Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጠ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔ: መዝገብ ቁጥር 271726

ከዚህ በፊት በሰ/መ/ቁጥር 249795 ላይ “ሠራተኛዉ በተከታታይ ከ5 ቀናት በላይ ለሆነ ጊዜ ከሥራ ቢቀር እንኳ ከሥራ ለቀረበት ለእያንዳንዱ ቀን አሠሪዉ ማስጠንቀቂያ (Warning in Writing) ሳይሰጥ የሥራ ዉልን ለማቋረጥ እንደማይችል” ተገልጾ የተሰጠው የህግ ትርጉም ተለውጦ “የአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 27(1)(ለ) ድንጋጌ ሠራተኛዉ በዚሁ አዋጅ ከተመለከቱ እረፍቶችና ልዩ ልዩ ፈቃዶች ዉጭ ለአምስት ተከታታይ የሥራ ቀናትና ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ ከሥራ ላይ ከቀረ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ (Warning in Writing) መስጠት ሳያስፈልግ የሥራ ዉልን ያለ ማስጠንቀቂያ ማቋረጥ ይቻላል” በሚል ተተርጉሟል፡፡ 

Previous Article ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጠ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔ: መዝገብ ቁጥር 244308
Print
2033

Documents to download

  • 271726(.pdf, 281.52 KB) - 409 download(s)

«July 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
293012345
6789101112
13141516171819
20212223242526
272829303112
3456789

ሥነ-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥና የጥቅም ግጭት መከላከልና...

1384

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፌዴራል ሥነ-ምግባርና ፀረ -ሙስናና ኮሚሽን ጋር በመተባበር በሥነ-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥ እና የጥቅም ግጭት መከላከልና ማስተዳደር ላይ ከፍርድ ቤት ዘርፍ ለተውጣጡ የስራ ሃላፊዎች የካቲት 5 እና 6 ቀን 2018 ዓ.ም ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የኢትዮጵያ...

1102

የመግባቢያ ስምምነቱን የፈረሙት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት እና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ቢኒያም ኤሮ ናቸው፡፡

በዳኝነት ስርአቱ ውስጥ ለህጻናት ተስማሚ የፍትህ ስርአትን...

859

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት በዳኝነት ስርአት ውስጥ ለህጻናት ተስማሚ የፍትህ ስርአትን ለማጎልበት ከአጋር ድርጅቶች ጋር የጋራ ውይይት መድረክ በቀን 03/06/2018 ዓ.ም ተካሂዷል።

ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንቶች ...

1055

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አዲስ ተሿሚ ምክትል ፕሬዚዳንቶች ክቡር አቶ ልዑል ካህሳይን እና ክቡር አቶ ምትኩ ማዳን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ከፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመራሮች እና የስራ ሃላፊዎች ጋር በቀን 02/06/2018 ዓ.ም ትውውቅ እና የስራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

በቆይታቸውም የፌደራል ፍርድ ቤቶች የሪፎርም ተግባራት ላይ ገለጻ እና የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶች ላይ ማብራሪያ የቀረበላቸው ሲሆን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚገኙ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችንም ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

First34568101112Last