Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ ሳሙኤል ድረስ ደመቀ እና ዳሽን ባንክ አ.ማ የሰ/መ/ቁ 259234

ጉዳዩ የስራ ክርክርን የሚመለከት ሆኖ ክርክሩ የተጀመረው በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው፡፡በስር ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ ሆነው ተከራክረዋል፡፡

አመልካች መጋቢት 20 ቀን 2015 ዓ.ም በተጻፈ ክስ በተጠሪ ባንክ ዉስጥ በምክትል ሥራ አስኪያጂነት የስራ መደብ ከሚያዝያ 24 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ በራሴ ፍቃድ የስራ ዉሉን እስካቋረጥኩበት ታህሳስ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ጠቅላላ ብር 46,191.01(አርባ ስድስት ሺ አንድ መቶ ዘጠና አንድ ከ01/100) እየተከፈለኝ በቋሚነት ተቀጥሬ እሰራ የነበረ ሲሆን ስራዉን በገዛ ፍቃዴ ስለቅ ተጠሪ ሊከፍለኝ የሚገባዉን የተጠራቀመ ፕሮፊደንት ፈንድ፣ የአገልግሎት ክፍያ፣ የተጠራቀመ የአመት ፍቃድ፣ ጠቅላላ ብር 541,422.78(አምስት መቶ አርባ አንድ ሺ አራት መቶ ሃያ ሁለት ከ78/100) ሊከፍለኝ ስላልቻል ይህን ክፍያ እንዲከፍለኝ እንዲሁም ክፍያዉ ለዘገየበት የካሳ ክፍያ፣ ያለስራ ለተቀመጥኩበት የሶስት ወር ደመወዝ ካሳ እና የስራ ልምድ ከእዳ ነፃ ተብሎ እንዲሰጠኝ ይወሰንልኝ በማለት ክስ አቅርበዋል፡፡መልካም ንባብ…    

Previous Article አቶ መንገሻ መሮ እና እነ መ/ር መስፍን መንገሻ (2ሰዎች) የሰ/መ/ቁጥር 258429
Next Article አቶ አሸናፊ ተስፋዬ እና የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት የሰ/መ/ቁ 259817
Print
5978

Documents to download

  • 259234(.pdf, 852.85 KB) - 697 download(s)

«August 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
272829303112
3456789
10111213141516
17181920212223
24252627282930
31123456

የዓለምአቀፍ የ16 ቀን ፀረ-ጾታዊ ጥቃት እንቅስቃሴ...

3569

ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ዓለምአቀፍ የ16 ቀን ፀረ-ጾታዊ ጥቃት እንቅስቃሴን ለማስጀመር የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ባዘጋጀው መድረክ በተካሄደ መድረክ ላይ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ የመልዕክቱ ሙሉ ይዘት እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

ዳኞች ስራ ላይ ባሉ ህጎችና ፋይዳቸው ላይ የጽሁፍ...

3311

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ሰለሞን አረዳ ዳኞች በስራ ላይ ባሉ ህጎችና ፋይዳቸው ላይ ጥናትና ምርምር በማካሄድ የጽሑፍ ውጤቶችን ማበርከት እንደሚጠበቅባቸው ገለጹ፡፡

አቶ ሰለሞን አረዳ ይህን የገለጹት በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝደንት በሆኑት በክቡር አቶ ተስፋዬ ነዋይ “የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ሕጋዊና ኢኮኖሚያዊ ገጽታ” በሚል ርዕስ የታተመ መጽሐፍ የምረቃና የትችት መርሃ ግብር ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ነው፡፡

ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ አሰባሰብ...

4201

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመተባበር የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ አሰባሰብ ስርዓቱን አዘምኗል፡፡ 

ፍርድ ቤቱ ማንኛውንም የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ በሚከፈለው ብር መጠን ሳይገድብ፣ ባለጉዳዮች ወደ ባንክ መሄድ እና ጥሬ ገንዘብ ማቅረብ ሳያስፈልጋቸው ክፍያ መፈፀም የሚችሉበት የአሰራር ማሻሻያ አድርጓል፡፡  በዚህ የክፍያ አፈጻጸም ማሻሻያ ስርዓት፡-

First7778798082848586Last