Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

ሲሲኢሲሲ ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ እና አቶ ቤልሻጽር ሀይለልዑል መ/ጽድቅ የሰ.መ.ቁ.250942

ይህ የስራ ስንብት ክርክር የተጀመረዉ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁን አመልካች የሥር ከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪ የሥር ተከሳሽ ሆኖ ሲከራከሩ ነበር፡፡ ጉዳዩ ለዚህ ሰበር ችሎት ሊቀርብ የቻለዉ አመልካች የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.296508 በ29/10/2015 ዓ.ም የሰጠዉ ፍርድ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲታረምልን በማለት በማመልከቱ ነዉ፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ የአሁን አመልካች በሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረበዉ የክስ አቤቱታ፡ አመልካች በተጠሪ ድርጅት በብሮ ስራ መሃንዲስ የሥራ መደብ ተቀጥሬ በወር 80,000 (ሰማንያ ሺህ) እየተከፈለኝ በአርሲ ሮቤ ዋቤ ሪቨር ፕሮጀክት ሲሰራ የቆየሁ ሲሆን ተጠሪ በ02/12/2014 ዓ.ም በሕገወጥ መንገድ ከሥራዬ ስላሰናበተኝ ተገቢ ክፍያዎችን እንዲከፍለኝ እንዲወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡መለካም ንባብ….

Previous Article እነ አቢብ አብዲ (3) ሰዎች እነ ዓሊ ዮሜ ዩሱፍ የሰ/መ/ቁጥር---250757
Next Article ህብረት ኢንሹራንስ አ.ማ እና ኤም.ኢ.ኤስ.ፒ. አፍሪካ ኃ.የተ.የግ. ማህበር ፤የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጀት የሠ/መ/ቁጥር 251398
Print
5494

Documents to download

  • 250942(.pdf, 865.73 KB) - 771 download(s)

«July 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
293012345
6789101112
13141516171819
20212223242526
272829303112
3456789

የዳኞች ሥልጠና ፍትሐዊና ተጠያቂነት ያለባቸው ፍርድ...

3097

በፌደራል በጠቅላይ ፍርድ ቤት እና በዩ.ኤን.ዲፒ (UNDP) መካካል እየተተገበረ ባለው የፍርድ ቤቶች ማሻሻያ ፕሮጀክት አማካኝነት እየተካሄደ በሚገኘው የዳኞች ስልጠና ሥርዓት የዳሰሳ ጥናት ላይ የግብአት ማሰባሰቢያ የውይይት መድረክ ሐምሌ 30 ቀን 2013 ዓ.ም በቤስት ዌስተርን ሆቴል ተካሔደ፡፡

የዳኞችን ዕውቀት እና ክሕሎት በማጎልበት የዳኝነት...

3141

የፌደራል የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓትን ለመደንገግ በወጣው አዋጅ ቁጥር 1183/2012 ላይ ከፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ከፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለተውጣጡ ዳኞች የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ከሐምሌ 24-25 ቀን 2013 ዓ.ም በራዲሰን ብሉ ሆቴል ተሰጠ፡፡

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ዳኞችና የአስተዳደር ዘርፍ ክፍል...

3648

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች እና የአስተዳደር ዘርፍ ከፍል ሃላፊዎች በሃገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ባለው “ኢትዮጵያን እናልብስ” ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ላይ በመሳተፍ የሃገራችንን የደን ሽፋን የማሳደግና የአየር ንብረትን የመጠበቅ ኃላፊነታችውን ለመወጣት በጉለሌ ዕጽዋት ማዕከል 600 ሃገር በቀል የዛፍ ችግኞችን ተክለዋል፡፡

የፌዴራል ዳኞች የጉባዔ ተወካዮቻቸውን መረጡ

3514

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች በፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ የሚወክሏቸውን 3 ዳኞች መረጡ፡፡ የቀድሞውን የዳኞች አስተዳድር ጉባዔ አዋጅ 684/2002ን ለማሻሻል የወጣው የፌዴራል ዳኝነት አስተዳደር አዋጅ 1233/2013 አስራ አምስት ዓባላት ያሉት የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ያቋቋመ ሲሆን በአዋጁ እንቀጽ 6(1/ቀ) መሰረት ከሶስቱም ፌዴራል ፍርድ ቤቶች በዳኞች ጠቅላላ ስብሰባ የተመረጡ አንድ ወንድ እና ሁለት ሴት ዳኞች በድምሩ ሶስት ዳኞች አባል እንዲሆኑ ይደነግጋል፡፡

First7879808183858687Last