Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ ሳሙኤል ድረስ ደመቀ እና ዳሽን ባንክ አ.ማ የሰ/መ/ቁ 259234

ጉዳዩ የስራ ክርክርን የሚመለከት ሆኖ ክርክሩ የተጀመረው በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው፡፡በስር ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ ሆነው ተከራክረዋል፡፡

አመልካች መጋቢት 20 ቀን 2015 ዓ.ም በተጻፈ ክስ በተጠሪ ባንክ ዉስጥ በምክትል ሥራ አስኪያጂነት የስራ መደብ ከሚያዝያ 24 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ በራሴ ፍቃድ የስራ ዉሉን እስካቋረጥኩበት ታህሳስ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ጠቅላላ ብር 46,191.01(አርባ ስድስት ሺ አንድ መቶ ዘጠና አንድ ከ01/100) እየተከፈለኝ በቋሚነት ተቀጥሬ እሰራ የነበረ ሲሆን ስራዉን በገዛ ፍቃዴ ስለቅ ተጠሪ ሊከፍለኝ የሚገባዉን የተጠራቀመ ፕሮፊደንት ፈንድ፣ የአገልግሎት ክፍያ፣ የተጠራቀመ የአመት ፍቃድ፣ ጠቅላላ ብር 541,422.78(አምስት መቶ አርባ አንድ ሺ አራት መቶ ሃያ ሁለት ከ78/100) ሊከፍለኝ ስላልቻል ይህን ክፍያ እንዲከፍለኝ እንዲሁም ክፍያዉ ለዘገየበት የካሳ ክፍያ፣ ያለስራ ለተቀመጥኩበት የሶስት ወር ደመወዝ ካሳ እና የስራ ልምድ ከእዳ ነፃ ተብሎ እንዲሰጠኝ ይወሰንልኝ በማለት ክስ አቅርበዋል፡፡መልካም ንባብ…    

Previous Article አቶ መንገሻ መሮ እና እነ መ/ር መስፍን መንገሻ (2ሰዎች) የሰ/መ/ቁጥር 258429
Next Article አቶ አሸናፊ ተስፋዬ እና የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት የሰ/መ/ቁ 259817
Print
5978

Documents to download

  • 259234(.pdf, 852.85 KB) - 697 download(s)

«August 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
272829303112
3456789
10111213141516
17181920212223
24252627282930
31123456

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ተቋማዊ መዋቅር ላይ ምክክር ተካሄደ

4458

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አመራሮችና የመዋቅር ስራ ክትትልና ቁጥጥር ኮሚቴ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የህገመንግስቱ መጽደቅን ተከትሎ በያዙት አደረጃጀት ተቋማቂ ተልዕኮአቸውን ለመወጣት እንዲያስችላቸው ተግባራዊ በተደረጉ ሶስት ተቋማዊ መዋቅር ላይ ምክክር አካሄዱ፡፡

በቅርቡ የፀደቁ የፍርድ ቤቱን አዋጆች ተግባራዊ ለማድረግ...

3440

ማሻሻያ ተደርጎባቸው በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የፀደቁትን የፌደራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1234/2013 እና የፌደራል ዳኝነት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1233/2013 ተፈጻሚ ለማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ ደንቦችና መመሪያዎች ዝግጅት እየተፋጠነ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡

በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የፍትሐ ብሔር ጉዳዮች...

4132

በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የፍትሐ ብሔር ጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር መመሪያ ትግበራ ማስጀመሪያ ውይይት ተካሄደ

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍርድ ቤቶችን አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል የሚረዳ የፍትሃ ብሔር ጉዳዩች ፍሰት አስተዳደር መመሪያ በሚያዚያ ወር 2013 ዓ.ም ማውጣቱን ተከትሎ የመመሪያውን ትግበራ በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለማስጀመር የሚያስችል ውይይት ሰኔ 19 ቀን 2013 ተካሄደ፡፡

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ...

3810

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ በሚካሄድበት ዕለት በከፊል ክፍት ሆነው ይውላሉ፣

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ በሚካሄድበት ዕለት ሰኞ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ከምርጫ ጋር የተያያዙ እና አጣዳፊ የፍርድ ቤት ውሳኔ የሚጠይቁ ጉዳዮችን ለማስተናገድ በከፊል ክፍት  እንደሚሆኑ ተገለጸ።

First8182838486888990Last