Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ ሳሙኤል ድረስ ደመቀ እና ዳሽን ባንክ አ.ማ የሰ/መ/ቁ 259234

ጉዳዩ የስራ ክርክርን የሚመለከት ሆኖ ክርክሩ የተጀመረው በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው፡፡በስር ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ ሆነው ተከራክረዋል፡፡

አመልካች መጋቢት 20 ቀን 2015 ዓ.ም በተጻፈ ክስ በተጠሪ ባንክ ዉስጥ በምክትል ሥራ አስኪያጂነት የስራ መደብ ከሚያዝያ 24 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ በራሴ ፍቃድ የስራ ዉሉን እስካቋረጥኩበት ታህሳስ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ጠቅላላ ብር 46,191.01(አርባ ስድስት ሺ አንድ መቶ ዘጠና አንድ ከ01/100) እየተከፈለኝ በቋሚነት ተቀጥሬ እሰራ የነበረ ሲሆን ስራዉን በገዛ ፍቃዴ ስለቅ ተጠሪ ሊከፍለኝ የሚገባዉን የተጠራቀመ ፕሮፊደንት ፈንድ፣ የአገልግሎት ክፍያ፣ የተጠራቀመ የአመት ፍቃድ፣ ጠቅላላ ብር 541,422.78(አምስት መቶ አርባ አንድ ሺ አራት መቶ ሃያ ሁለት ከ78/100) ሊከፍለኝ ስላልቻል ይህን ክፍያ እንዲከፍለኝ እንዲሁም ክፍያዉ ለዘገየበት የካሳ ክፍያ፣ ያለስራ ለተቀመጥኩበት የሶስት ወር ደመወዝ ካሳ እና የስራ ልምድ ከእዳ ነፃ ተብሎ እንዲሰጠኝ ይወሰንልኝ በማለት ክስ አቅርበዋል፡፡መልካም ንባብ…    

Previous Article አቶ መንገሻ መሮ እና እነ መ/ር መስፍን መንገሻ (2ሰዎች) የሰ/መ/ቁጥር 258429
Next Article አቶ አሸናፊ ተስፋዬ እና የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት የሰ/መ/ቁ 259817
Print
5978

Documents to download

  • 259234(.pdf, 852.85 KB) - 697 download(s)

«August 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
272829303112
3456789
10111213141516
17181920212223
24252627282930
31123456

በፍትሃ ብሔር ፍርደ አፋጻጸም በሚታዩ ተግዳሮቶች እና...

3413

ሰኔ 6 ቀን 2013 ዓ.ም/ ቢሸፍቱ/ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በፍትሃ ብሔር ጉዳዮች ላይ የሚሰጧቸውን ውሳኔዎችና ትእዛዞችን በማስፈጸም ሂደት በሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችና ሊወሰዱ በሚገቡ የማስትካከያ እርምጃዎች ላይ ከባልድርሻ እካላት ጋር ምክክር አደረገ።

በረቂቅ የስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ የአስተዳደር ሰራተኞች...

3863

በረቂቅ የስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ የአስተዳደር ሰራተኞች ግብአት የሚሰጡበት ሁኔታ መመቻቸቱ  ሰራተኞች በፍርድ ቤቶች የማሻሻያ ስራዎች ላይ ያላቸውን ተሳትፎ እንዲሚያሰፋው ተገለጸ፡፡

 

ከፌዴራል ፍርድ ቤቶች የተውጣጡ የአስተዳደር ሰራተኞች በአማካሪ ድርጅቱ በመዘጋጀት ላይ ባለው ረቂቅ የስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ ተጨማሪ ግብአት እንዲሰጡ ሁኔታዎች መመቻቸታቸው የአስተደደር ሰራተኞች በፍርድ ቤቶች በመተግበር ላይ ባለው የማሻሻያ ስራዎች ላይ ያላቸውን ተሳትፎ እንደሚያሰፋ ገለጹ፡፡

የፌደራል ፍርድ ቤቶች የአስተዳደር ሠራተኞች ረቂቅ...

5022

የፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 መጽደቁን ተከትሎ በፍርድ ቤቶች ከዳኞች ውጭ ያሉ የአስተዳር ሠራተኞች የሚተዳደሩበት ረቂቅ መተዳደሪያ ደንብ ላይ የግብአት ማሰባሰቢያ ውይይት ተካሔደ፡፡

ለ68 ዓመታት በሥራ ላይ የቆየውን የዳኝነት ክፍያ...

4047

ከ1945 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ላይ የቆየውን የፌደራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ክፍያ እና የአከፋፈል ሥርዓት ለማሻሻል ተዘጋጅቶ በቀረበ ረቂቅ ደንብ ላይ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ግንቦት 21 ቀን 2013 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል የግማሽ ቀን ውይይት ተካሔደ፡፡

First8283848587899091