Anonym
/ Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation

አቶ ኢሳያስ አድማሱ አለማየሁ እና ወ-ሮ አልማዝ ተድላ ደስታ የ-ሰ-መ-ቁ 183547

 ጉዳዩ ለሰበር ችሎቱ ሊቀርብ የቻለው አመልካች የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት መናገሻ ምድብ 2ኛ ፍ/ብሄር ችሎት በኮ.መ.ቁ 62214 በ13/3/11ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ፤ የፌ/ከ/ፍ/ቤት በመ.ቁ 230102 በ28/10/11ዓ.ም በሰጠው ትእዛዝ ቅር በመሰኘት በ7/1/12ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ ስላቀረቡ ነው፡፡የጉዳዩ አመጣጥ አመልካች በስር የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በተጠሪዎች ላይ ባቀረቡት ክስ ሟች አባቴ አቶ አድማሱ አለማየሁ በ29/10/03ዓ.ም ያደረጉት ኑዛዜ አመልካችን ከወራሽነት የነቀለ እና የወራሽነት ድርሻ የሌለኝ ያደረገ ስለሆነ ይህ ኑዛዜ ተሰርዞ በፍ/ብ/ህ/ቁ 842(1) መሰረት ከሌሎች ወራሾች እኩል ድርሻ ያለኝ መሆኑ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀው 1ኛ ተጠሪ ባቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የሟች ህጋዊ ሚስት ስሆን ወራሽ ባልሆን ከሚስት እና ከባለቤቴ ንብረት ድርሻ ግማሹ(50%) የኔ መሆኑ እስከታወቀ ከሌሎች ወራሾች ጋር መከሰስ የሌለብኝ በመሆኑ፤ አመልካችም ከ1ኛ ተጠሪ የሚፈልገው መብት እና ጥቅም ስለሌለ ክሱ በ1ኛ ተጠሪ ላይ መቅረቡ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 33 መሰረት ተቀባይነት የለውም የሚል ሲሆን፤ ተጠሪዎች በጋራ ባቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሟች አቶ አድማሱ አለማየሁ ግንቦት 29 ቀን 2003ዓ.ም ያደረጉት ኑዛዜ በአርባ ቀን መታሰቢያው የካቲት 5 ቀን 2009ዓ.ም ሲነበብ አመልካችም በአካል ተገኝቶ የሰማ በመሆኑ ይህን ደግሞ መቃወም የሚችለው በፍ/ብ/ህ/ቁ 973(2) በ15 ቀን ውስጥ ብቻ ሲሆን አመልካችም ለሽምግልና ዳኞች ይህን ያላደረገ በመሆኑ፤ በአንቀጽ 973(2)(3) መሰረትም እስከ 3 ወር ግዜ ውስጥ ያላቀረበ በመሆኑ ክሱ በፍ/ብ/ህጉ እና በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 244(2)(ለ) መሰረት በይርጋ ቀሪ ነው በማለት የተከራከሩ ሲሆን፤ ፍ/ቤቱም በመቃወሚያዎቹ ላይ ክሱን ከሰማ እና የግራቀኙን ምስክሮች ቃል ከሰማ በኋላ አመልካች ኑዛዜው ሲነበብ ሰምተዋል ወይስ አልሰሙም? ያልሰሙ ከሆነ የአመልካች ክስ በይርጋ የሚታገድ ነው ወይስ አይደለም? የሚሉትን ጭብጦች በመያዝ ጉዳዩን መርምሮ የአመልካች ምስክሮች በሰጡት ቃል አመልካች ኑዛዜው ሲነበብ በቦታው እንዳልነበሩ እና በእለቱም አብረው መዋላቸውን ገልጸዋል ይሁን እንጂ የአመልካች እናት አመልካች የ40 ቀን መታሰቢያው ቦታ እንዲሄድ በምስክሮች በኩል ያደረጉ ቢሆንም አመልካች ግን ሳይሄድ እንደቀረ መስክረዋል፤ የተጠሪዎች ምስክሮች በበኩላቸው አመልካች የሟች አባቱ የ40 ቀን መታሰቢያ ቀን የካቲት 5 2009ዓ.ም እዛ እንደነበር ፤ የኑዛዜው ኮፒ ለአመልካች እንደተሰጠ እና ስሙም በሄኖክ አድማሱ በሚባል ተራ ቁጥር 13 ላይ የሰፈረ ነው፤ የአመልካች ስም በሄኖክ አድማሱ ስም እንደሚታወቅ ለዚህም ማሳያ የአመልካች እናት የአመልካች ስም ሄኖክ ነው ማለታቸውን 1ኛ ምስክር መስክረዋል፤ አመልካች ጠዋት 1 ሰአት ጀምሮ እዛ እንደነበር እና የኑዛዜው ድርሻ አንሶኛል ያለውም ከ1 ወር በኋላ ነው በማለት በመመስከራቸው ከግራቀኙ ምስክሮች ቃል አመልካች ኑዛዜው በሚነበብበት ወቅት ቦታው የነበረ መሆኑን የተጠሪዎች ምስክሮች ከአመልካች ምስክሮች በበለጠ እና በአሳማኝ መልኩ በመግለጻቸው የፍ/ብሄር ህግ አንቀጽ 973(2) (3) ከደነገገው አንጻር ኑዛዜው የተነበበው የካቲት 5 ቀን 2009ዓ.ም ሲሆን የአመልካች ክስ የቀረበው በ22/12/09ዓ.ም በመሆኑ ይህም ሲቆጠር ከ15(አስራ አምስት) ቀናት በኋላ ብሎም ከ3(ሶስት) ወር በኋላ በመሆኑ ፤ አመልካችም በኑዛዜው ላይ ስማቸው እስከሰፈረ ድረስ የፍ/ብ/ህ/ቁ 939 ከደነገገው እና የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 36604 እና 53223(ቅጽ 8 እና 12) ከሰጣቸው አስገዳጅ ውሳኔዎች አንጻር ከኑዛዜው ተነቅያለሁ የሚባልበት አግባብ የለም ስለሆነም ክሱ በፍ/ብ/ህ/ቁ 973(1) እና 244(2) (ረ) መሰረት በይርጋ ይታገዳል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፌ/ከ/ፍ/ቤት አቅርበው ፍ/ቤቱም በሰጠው ትእዛዝ ይግባኙን ሰርዞታል፡፡……….

Previous Article ወ-ሮ ገነት ገሠሰ ቸኮል እና የአ.አ ከተማ የየካ ክ-ከተማ አሰ-ዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ-ቤት፣ የአ.አ ከተማ የየካ ክ-ከተማ አስተዳደር የትምህርት ፅ-ቤት የሰ-መ-ቁ 180001
Next Article አቶ ወንድማገኝ መንግስቱ ማሞ እና የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰ-መ-ቁ 191629
Print
17887
«August 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
272829303112
3456789
10111213141516
17181920212223
24252627282930
31123456

ለስትራቴጂካዊ ዕቅድ ዝግጅት የተካሄዱ የትንተና ጥናቶች...

4219

በአማካሪ ድርጅት የሚሰራውን ሶስተኛው የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ዝግጅት ሂደትን እንዲከታተል በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተቋቋመው ዓብይና የቴክኒክ ኮሚቴ አማካሪ ድርጅቱ ለስትራቴጂካዊ ዕቅድ ዝግጅት ባካሄዳቸው የትንተና ጥናቶች ላይ ተጨማሪ ግብዓት ሰጠ፡፡

ፍርድ ቤቶች በዘጠኝ ወሩ ከአንድ መቶ 19 ሺህ በላይ...

4582

የፌደራል ፍርድ ቤቶች በ2013 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ለ119, 413 መዛግብት እልባት መስጠታቸውን የሶስቱ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የተጠቃለለ የዘጠኝ ወር የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አመለከተ፡፡

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሀዋሳ ማዕከል በይፋ...

6760

የፌዴራል ጉዳዮችን በውክልና እንዳይመለከቱ ስልጣናቸው በተነሳባቸው የክልል ፍርድ ቤቶች የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተዘዋዋሪ ችሎት በማደራጀት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

First8283848586878991