የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ቀበሌ 11/12/08 ሸማቾች ኃ/የተ/ሕ/ሥ/ማ እና አቶ እንኮሳ አመንቴ ሱፋ(9ሰዎች)የሰ.መ.ቁ 249104
የክሱ ይዘት በአጭሩ፡- በየካ አውራጃ ከፍተኛ 16 ቀበሌ 08 የቀድሞው የቀበሌ አመራሮች የተጠሪዎችን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ በማሰብ ከህብረት ሥራ ማህበር ብር 29.000 (ሃያ ዘጠኝ ሺህ ብር) በብድር መልክ ወጪ ተደርጎ ቤት እንድንገነባ ተፈቅዶልን ቤቶቹን በመገንባት የብድር ገንዘብም ተመልሷል፤ ተጠሪዎችን ጨምሮ ሌሎች ነዋሪዎች በራሳችን ገንዘብ ቤቶቹን አፍርሰን እንደሰራን በወቅቱ የነበሩ የአመልካች አመራሮች አረጋግጠው በሰነድ ማስረጃ ሰጥተውናል፤ ተጠሪዎች ከ1982/1983 ጀምሮ በሰነድ አልባ በመኖሪያ ቤቶቹን ገንብተን እየኖርን እያለን ከ20 ዓመታት በኋላ አመልካች ለተጠሪዎች ያሰበ በማስመሰል ከፊሎቹን የተጠሪዎች ቤቶች ለልማት ሊፈርሱ ስለሚችሉ የጋራ መኖሪያ ቤት መንግስት እንዲሰጣችሁ እና ቀበሌው እንዲያውቃችሁ በማለት ከሱ ጋር የቤት ኪራይ ውል እንድንዋዋል ሲጠይቀን ተጠሪዎችም የአመልካች ህብረት ሥራ ማህበር አባላት በመሆናቸን እና መንግስታዊ ተቋም ነው ብለን በማመን ከ2ኛ ተጠሪ በስተቀር ከአመልካች ጋር የቤት ኪራይ ውል ልንፈርም ችለናል፤ተጠሪዎች የይዞታ ማረጋገጫ ለመቀበል በሂደት ላይ እያለን አመልካች ከህግም ሆነ ከውል የመነጨ መብት ሳይኖረው እንዳይፈጸም አድርጓል፤ አመልካች ተጠሪዎችን በማታለል ባስፈረመን የኪራይ ውል መነሻነት ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኪራዩን ከፍለው ቤቱን ያስረክቡኝ በማለት ክስ አቅርቦ ተጠሪዎች ቤቱን እንድናስረክብ ተወስኗል፤ ሆኖም ከመነሻው ቦታው በጎርፍ ምክንያት ለህይወታችን እስጊ በመሆኑ ልዋጭ ቦታ እንዲሰጠን የሚመለከተውን አካል ጠይቀን ሲሰጠን በቦታው ላይ ቀበሌው ቤት መስራት ካልቻለ ነዋሪዎች በራሳችን ወጪ እንድንሰራ በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት በራሳችን ወጪ ቤት ገንብተን በስማችን ውሃ፣ መብራት እና መሰል መሰረታዊ አገልግሎቶችን አስገብተን የምንኖርበት ቤት በመሆኑ ቤቶቹ የተጠሪዎች ናቸው ተብሎ ይወሰንልን በማለት ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡መልካም ንባብ….
4680
Documents to download
-
249104(.pdf, 865.58 KB) - 546 download(s)