Selam Warga / Wednesday, June 4, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation አቶ ዮሀንስ ካሳዬ እና የፍትህ ሚኒስቴር ዓቃቤ ሕግ የሠ/መ/ቁጥር 273594 ጉዳዩ የዋስትና መብት አተገባበር የሚመለከት ነው፡፡ክርክሩ የተጀመረው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን ተጠሪ በአመልካች ላይ በመሰረተዉ ክስ አመልካች በኢፌዲሪ ወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1/ሀ) እና 590(1/ሀ እና 2/ሐ) ስር የተደነገገዉን በመተላለፍ በዋና ወንጀል አድራጊነት በሚፈፀም የሰው ማገት(መጥለፍ) ወንጀል በመፈጸሙ ተከሷል የሚል ነው፡፡ ይህንን ተከትሎ አመልካች የዋስትና መብቱ እንዲከበርለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡ፍርድ ቤቱም የዋስትና መብት ጥያቄውን በተመለከተ በሰጠው ትዕዛዝ አመልካች የተከሰሰበት ክስ በመርህ ደረጃ ዋስትና የማያስከለክል ቢሆንም እንጂ በክሱ ላይ የተጠቀሰውን ድርጊት አፈፃፀም በተመለከተ አመልካች የመከላከያ ሰራዊት የደንብ ልብስ ለብሰው እና የጦር መሳሪያ ይዘው ፈፀመ ተብሎ በክስ ዝርዝር ላይ ባይገለፅም ድርጊቱን ፈፅሞ ከሆነ ተሳትፎዉ ወደ ፊት ማስረጃ በመስማት ጊዜ የሚታይ ሆኖ በአጠቃላይ ከክሱ ዝርዝር ፍርድ ቤቱ የወንጀሉ አፈፃፀሙ ከባድ ሆኖ ስለአገኘዉ አመልካች ምን አልባት ወደፊት የወንጀል ድርጊቱን መፈፀሙ ተረጋግጦ ጥፋተኛ የሚባል ከሆነ ሊጣልበት የሚችለው ቅጣት ከባድ ሊባል የሚችል በመሆኑ ይህን ፈርቶ ቀጠሮ አክብሮ ይመጣል የሚል እምነት የለንም በማለት የአመልካችን የዋስትና መብት ጥያቄ ዉድቅ አድርጓል፡፡መልካም ንባብ….. Previous Article አቶ ሰለሞን አርአያ እናእነ ህፃን ዳንኤል ቴውድሮስ ሞግዚት ወ/ሮ የሺ መንግስቱ(5ሰዎች)የሰ/መ/ቁጥር፡- 255592 Next Article አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ እና የማነ ግርማይ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ የሰ.መ.ቁ 246233 Print 5455 Documents to download 273594(.pdf, 1.05 MB) - 872 download(s)
በጠቅላይ ፍርድ ቤት የምርጫ ጉዳዮችን እንዲመለከቱ... በጠቅላይ ፍርድ ቤት የምርጫ ጉዳዮችን እንዲመለከቱ... Friday, April 16, 2021 3727 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ከምርጫ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች የሚታዩባቸው ችሎቶች በጠቅላይ ፍ/ቤት መደራጀታቸውን አፈጻጸማቸውን በተመለከተ ለፕሬዝደንት ጽ/ቤትና ለሬዲስትራሮች የስራ አቅጣጫ ሰጡ፡፡ Read more
የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በ2012 በጀት ዓመት... የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በ2012 በጀት ዓመት... Tuesday, October 27, 2020 3671 ፍርድ ቤቱ ከእያንዳንዱ ምድብ ችሎቶት በባህሪና በመዝገብ አፈጻጸም መልካም ውጤት ያስመዘገበ 1 ዳኛ በመምረጥ በአጠቃላይ ለ11 ዳኞች የእውቅና ምስክር ወረቀት ሰጥቷል፡ Read more
ለፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኮሮና ቫይረስ... ለፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኮሮና ቫይረስ... Tuesday, October 27, 2020 3651 ጥቅምት 5/2013 ዓ.ም የኢትጵያ የሕግ ባለሞያዎች ማህበር ለፌ/መ/ደ/ፈ/ቤት ኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የሚያስችል የተለያዩ የጥንቃቄ ግብአቶች (Personal Protective Equipment) በድጋፍ መልኩ አበርክቷል፡፡ Read more
ፍርድ ቤቶች የሕዝብ አመኔታ እንዲያገኙ ዳኞች በዘርፉ ላሉ... ፍርድ ቤቶች የሕዝብ አመኔታ እንዲያገኙ ዳኞች በዘርፉ ላሉ... Tuesday, October 27, 2020 3602 የፌደራል ፍርድ ቤቶች በአገልግሎት አሰጣጣቸው የሕዝብ አመኔታ ሊያተርፉ የሚችሉት ሥራቸውን የዳኝነት የሥነምግባር ደንቡን እና ዓለም አቀፍ የዳኝነት የሥነምግባር መርሆዎችን መሠረት አድርገው ሲያከናውኑ መሆኑ ተገለጸ፡፡ Read more
10Mar2026 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Tuesday, March 10, 2026 Read more