Selam Warga / Tuesday, June 17, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation ጨመሬ ቶሎሳ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰ/መ/ቁጥር 267231፣267230 የአሁን አመልካች በምዕራብ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ/መ/ቁ 47863 እና በመ/ቁ በመ/ቁ 47862 በሁለቱም መዝገቦች ላይ 2ኛ ተከሳሽ ሲሆን ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበው የክስ ይዘትም አመልካች የኢትዮጵያ የፌዴራል ቡና እና ሻይ ባለስልጣን ግምቢ ቅርንጫፍ የቡና ላኪ ሸኚ ስምሪት ጣቢያ ላይ ቋሚ ሰራተኛ ሆኖ በባለሙያነት ተቀጥሮ እየሰራ እያለ በቡና ንግድ ውስጥ የማጭበርበር ድርጊት በመፈጸም ለራሱ የማይገባውን ጥቅም ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ በምዕራብ ወለጋ ዞን ግምቢ ከተማ ቀበሌ 05 በኢትዮጵያ ምርት ገበያ ግምቢ ቅርንጫፍ ግቢ ውስጥ ጥቅምት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ለማዕከላዊ ገበያ የሚቀርብ የተቀሸረ ቡና ዓይነቱ እና የሰሌዳ ቁጥሩ 3-A02958 A.A በሆነ ኤፍ.ኤስ፣አር መኪና ከነጆ ከተማ ተጭኖ በፕሎምፕ ታሽጎ የቡናው ፕሎምፕ ቁጥር GM-7 በሚባል የታሸገውን በሚልክበት ጊዜ የቡናውን መጠን አጣርቶ መላክ እያለበት የተቀሸረ 129 ኩንታል ተጭኖ እያለ 100 ኩንታል በሚል እንዲሁም ከአይራ ወረዳ በሲኖ ትራክ 210 ኩንታል ቡና የተጫነ ነዉ ተብሎ የተላከዉን ተቀብሎ በቡናው የይለፍ ወረቀት ላይ ይህንኑ መጠን በማረጋገጥ የይለፍ ወረቀት ከሰጠ በኋላ በዚሁ ቀን የተጠቀሱት መኪናዎች በጊምቢ ከተማ ልዩ ስሙ ሰርጤ ኬላ ቦታ ላይ በቁጥጥር ስር ውለዉ ሲፈተሹ 29 እና 70 ኩንታል ቡና እንደቅደም ተከተላቸዉ ከህግ ውጭ ጥራት በሌለው የማዳበሪያ ከረጢት ተጨምሮ እሱ በይለፍ ወረቀት ላይ ጽፎ ከሰጠው በላይ በተጨማሪ ተጭኖ ስለተገኘ የአዋጅ 1051/2009 አንቀጽ 19/5/ የሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 433/2007 አንቀጽ 41(1)(ቀ) በመተላለፍ የማይገባ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት አስቦ በቡና ንግድ ውስጥ የማጭበርበር ወንጀል ድርጊት ፈጽሟል የሚል ነው፡፡ መልካም ምንባብ… Previous Article አቶ መሀመድ አለሙ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰበር መዝገብ ቁጥር 266395 Next Article ወ/ሮ የማርውሃ ወርቅነህ እና እነ ወ/ሮ ዓለም ወርቅነህ የሰ.መ.ቁ 242314 Print 6916 Documents to download 267231(.pdf, 1.08 MB) - 1412 download(s)
በጠቅላይ ፍርድ ቤት የምርጫ ጉዳዮችን እንዲመለከቱ... በጠቅላይ ፍርድ ቤት የምርጫ ጉዳዮችን እንዲመለከቱ... Friday, April 16, 2021 3727 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ከምርጫ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች የሚታዩባቸው ችሎቶች በጠቅላይ ፍ/ቤት መደራጀታቸውን አፈጻጸማቸውን በተመለከተ ለፕሬዝደንት ጽ/ቤትና ለሬዲስትራሮች የስራ አቅጣጫ ሰጡ፡፡ Read more
የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በ2012 በጀት ዓመት... የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በ2012 በጀት ዓመት... Tuesday, October 27, 2020 3671 ፍርድ ቤቱ ከእያንዳንዱ ምድብ ችሎቶት በባህሪና በመዝገብ አፈጻጸም መልካም ውጤት ያስመዘገበ 1 ዳኛ በመምረጥ በአጠቃላይ ለ11 ዳኞች የእውቅና ምስክር ወረቀት ሰጥቷል፡ Read more
ለፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኮሮና ቫይረስ... ለፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኮሮና ቫይረስ... Tuesday, October 27, 2020 3651 ጥቅምት 5/2013 ዓ.ም የኢትጵያ የሕግ ባለሞያዎች ማህበር ለፌ/መ/ደ/ፈ/ቤት ኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የሚያስችል የተለያዩ የጥንቃቄ ግብአቶች (Personal Protective Equipment) በድጋፍ መልኩ አበርክቷል፡፡ Read more
ፍርድ ቤቶች የሕዝብ አመኔታ እንዲያገኙ ዳኞች በዘርፉ ላሉ... ፍርድ ቤቶች የሕዝብ አመኔታ እንዲያገኙ ዳኞች በዘርፉ ላሉ... Tuesday, October 27, 2020 3602 የፌደራል ፍርድ ቤቶች በአገልግሎት አሰጣጣቸው የሕዝብ አመኔታ ሊያተርፉ የሚችሉት ሥራቸውን የዳኝነት የሥነምግባር ደንቡን እና ዓለም አቀፍ የዳኝነት የሥነምግባር መርሆዎችን መሠረት አድርገው ሲያከናውኑ መሆኑ ተገለጸ፡፡ Read more
10Mar2026 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Tuesday, March 10, 2026 Read more